Get Mystery Box with random crypto!

ምኞት ክፍል 46 ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . ምኛት ከዋሌቱ ያወጣችውን ፎቶ ወደ ዋሌቱ | የፍቅር ጎጆ

ምኞት

ክፍል 46

ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
.
ምኛት ከዋሌቱ ያወጣችውን ፎቶ ወደ ዋሌቱ መልሳ ከመሳይ እጅ
ላይ የወሰደቻትን የናርዶስን ጉርድ ፎቶ ደግሞ ከተኛው መሳይ
አጠገብ እዛው ፍራሹ ላይ አስቀምጣለት ወደ መደበቂያዋ ወደ
እቃ ቤቷ በመግባት መሳይ ከእንቅልፉ ሳይነቃ ሰርታ ለመጨረስ
ስለፈለገች ምግቧን ቶሎ ቶሎ መስራት ጀመረች።
ከቀኑ 11:30 ሆኗል ። መሳይ ግን እስካሁን አልነቃም። "እሄ ልጅ
ግን በሰላም ነው ሀይ ምነው እንቅልፍ አበዛ?"አለች መሳይ
ሳይነቃ ረዘም ላለ ሰአት በመተኛቱ ሀሳብ ገብቷት።
ስለሱ እያሰበች ጋደም ባለችበት እሷንም እንቅልፍ ይዟት ሄደ።
ማታ ከምሽቱ ሶስት ሰአት ቡሀላ ዙርያ ገባው ፀጥታ እየሰፈነበት
ሲመጣ የመሳይና የራድዮኑ ድምፅ ይበልጥ ጎልቶ መሰማት
ስለጀመረ ምኛትን ከእንቅልፏ ቀሰቀሳት።
ተነስታ ቁጭ አለችና የመሳይን ወሬ ማዳመጥ ጀመረች።
መሳይ አጠገቡ ያለ ከሚመስለውና ለሱ ብቻ ከሚታየው መንፈስ
ጋር ናርዶስ ዛሬ ትመጣለች አትመጣም በሚል ሞቅ ያለ ክርክር
ውስጥ ነው።
አሳዘኗት ተነስታ የእቃቤቱን በር በቀስታ ከፈተችና በድፍረት ቀጥ
ብላ መሳይ ወዳለበት አመራች።
መሳይ ልክ እንዳያት ወደ ጎን ዘወር አለና " አየኳት የኔን ንግስት
አንተ ግልፍጥ ትመጣለች አላልኩህም "አለው።መጠጋት
ብትፈራም
ሁኔታው እና ስፍስፍ ማለቱ ምኛትን በሱ ላይ ለመጨከን አቅም
አሳጥቷታል ።
ትንሽ አጨዋውታው መዳኒቱን ካዋጠችው ቡሀላ እስኪተኛ
አብራው ቆየችና ሲተኛ ገብታ ያቋረጠችውን እንቅልፍ ቀጠለች።
የመሳይ እህት ትንቢተ እና አባቷ በጥዋት ነበር መሳይ እና ምኛት
ሳይወዱ ሳይፈቅዱ ወደተጣሉበት ኮንደምንየም የመጡት።
አንድ ሌላ ሰው አብሯቸው አለ።
በሩን ከፍተው ሲገቡ ምኛት በርጋ
ተነሳች ።
ትንቢተ ወንድሟ መሰይን ልትቀሰቅሰው ወደተኛበት ስትጠጋ አባቷ
" እንዳይረብሸን በተኛበት ብትወጋው አይሻልም ዶክተር?" አለ
አጠገቡ ወደ አለው ሰው እየተመለከተ።
አባ! እንደዛማ አይሆንም ።አይረብሽም። ቆይ ልቀስቅሰ። አለችና
ዶክተሩ መሳይ በተኛበት እንዲወጋው ስላልፈለገች በፍጥነት
ትከሻውን ይዛ እያወዛወዘች ቀሰቀሰችው።
መሳይ ከእንቅልፉ እንደነቃ ቀና ብሎ ተቀመጠና ሶስቱንም በየተራ
ተመለክቷቸው •••
"ወደዛ ኖርዶስ ወደ ሌለችበት ኦና ቤታችሁ ልትወስዱኝ ከሆነ
የመጣችሁት አልሄድም! ተውኝ በቃ! እህቴ ይዘሻቸው ውጪ!እዚህ
እኮ ናርዶስ ትመጣለች ማታም መጥታ ነበር። ዛሬም
እንደምትመጣ ነግራኛለች። ሂዱ እዛ አስቀያሚ ቤታችሁ ውስጥ
እናንተው ኑሩበት ። ፍቅር የሌለበት ቤት ውስጥ መኖር
አልፈልግም! ፍቅሬ ዛሬ ማታ ትመጣለች መጥታ እንዳታጣኝ
ይዘሽልኝ ውጪ እህት አለም•••እያለ ሲጮህ ዶክተሩ ጠጋ ብሎ
መርፌውን ክንድ ላይ ሻጠው። መሳይም ዝም አለ።
ምኛት አንጀታ ተንሰፈሰፈ ቆማ ማዳመጥ አቃታት። ሁለት እጆቿን
ሆዷ ላይ አነባብራ እግሮቿ ላይ ቁጢጥ ለማለት ስታጎነብስ
አይኖቿ ላይ የተንጠለጠሉት የንባ ዘለላዎች ቁልቁል እየተወረወሩ
ወለሉ ላይ ሲበተኑ አየቻቸው።
እባትየው ከተወጋ ቡሀላ የተዝለፈለፈውን መሳይ ደገፍ አድርጎ
ይዞት ሲወጣ ትንቢተና ዶክተር ተብየው ከውዃላ ተከተሉት። ቤቱ
ጭር አለ ምኞት ሌላ አዲስ የብቸኝነት ስሜት ወረራት ።ቤቱ
አስጠላት።
ለሶስት ቀን በድብርት ውስጥ ሆና ነበር ያሳለፈችው ልክ
በአራተኛው ቀን ቀኑን ሙሉ ስትተኛ ውላ ስትነቃ መሽቷል ዝናቡ
ችፍ ችፍ ይላል ።
ከቆይታ ቡሀላ ዝናቡ ለቀቅ እንዳደረገው ከኮንደሚንየሙ በረንዳ
ላይ የሆነ የታፈነና የሚልጎመጎም የሰው ድምፅ የሰማች መሰላት።
መጀመርያ ጆሬዬ ነው ባላ አለፈችው። እየቆየ እየቆየ ሲደጋገም
ግን ፍርሀት ወረራት። በረንዳው ላይ ካለው ከዎናው የመብራት
ቆጣሪ በተጨማሪ እሳ ክፍል ውስጥ ባለው የመብራት
መቆጣጠሪያ (ብሬከር) የቤቱን መብራት በሙሉ ተራ በተራ
ቃ፣ቃ፣ቃ እያደረገች አጠፋችው። የቤቱ መብራት መጥፋቱን
ያስተዋለው በረንዳ ላይ የተቀመጠው ሰው•••
" ናርዶስዬ ሳትመጣ መብራቱን አጠፉት እንኳን ደስ አለህ !"
በማለት ሲጮህ መሳይ መሆኑን አወቀች። እራሱ ነው ! ጠፍቶ
መሆን አለበት የመጣው! ግን እንዴት አወቀው ቤቱን? እያለች
መብራቱን ሳታበራ ሻማ ለኩሳ ሳሎን መሀል ላይ አደረገችና በሩን
ከፍታለት ከበሩ ጀርባ ቆመች ።
ልክ ነበረች ።መሳይ ነው። በሩ መከፈቱን ሲሰማ ብድግ ብሎ
ዝናብ ባበሰበሰው ልብሱ ውስጥ በብርድ እየተንቀጠቀጠ ሳሎን
ውስጥ ወዳለው ፍራሽ ሲያመራ ከጀርባ በሻማው ብርሀን
እያየችው ነበር።
መሳይ ጠፍቶ ነበር የመጣው ስለዚህ የት እንዳለ የማታውቀው
እህቱ ትንቢተ ምግብ ይዛለት ልትመጣ አትችልም ።
ምኛት ቀን በጭራሽ አትታየውም። እሱም ቀን ቀን ትመጣለች
ብሎ አይጠብቅም።
ማታ ማታ አብራው ታመሻለች ሲተኛ ከሰራችው ምግብ ላይ ነገ
ቀን የሚበላውን አጠገቡ አስቀምጣለት ወደ መደበቂያ ክፍሏ
ገብታ ትትኛለች።
ከቀናቶች ቡሀላ ምኛት እንደልማዷ መሳይን እስኪተኛ እንደናርዶስ
ሆና አውርታው ሲተኛ ነገ ሲነቃ የሚበላውን ምግብ አጠገቡ
አስቀምጣለት ወደ ክፍሏ ገብታ ተኛች።
ጥዋት ስትነቃ ግን እንደሁሌው በዛች መደበቂያ እቃ ቤቷ ውስጥ
ብቻዋን አልነበረችም።
ፍራሿ አጠገብ ተቀምጦ ቁልቁል ሲመለከታት እንዳየችው
በተኛችበት ውሃ ሆነች።
"እኔ •••እኔ•••እኔ ባንቺ ምክንያት የዳንኩት መሳይ ነኝ። አንቺ
ማነሽ ?!" አላት...

.............ይቀጥላል............

150 ከገባ#ክፍል 47ዛሬ ይለቀቃል