Get Mystery Box with random crypto!

ም ኞት ክፍል 48 ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . ሚኪ ከአዳማ እንደመጣ ወደ ቤቱ ሳይገባ | የፍቅር ጎጆ

ም ኞት

ክፍል 48

ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
.
ሚኪ ከአዳማ እንደመጣ ወደ ቤቱ ሳይገባ ቀጥታ ወደ መጠጥ
ቤት ስልኩን አጥፍቶ ሲጠጣ አመሸ ። ከምሽቱ ሶስት ስአት
አከባቢ ሞቅ እንዳለው ስልኩን አውጥቶ በመክፈት ፅናት ላይ
ደወለ።
በብሩክ አማካሪበት በቀየረው አዲሱ ሲን ካርድ ነበርና የደወለው
ፅናት አላነሳችውም።
"እባክሽ አንሺው ፅናቴ ዛሬ ታስፈልጊኛለሽ እኔ ያንቺው ወንድም
ሚኪ ፅናቴ እህቴ ከጎኔ ሆና አይዞህ እንድትለኝ እሻለሁ ከፍቶኛል
ፅናቴ ከፍቶኛል! አለም በሙሉ የጠላኝ ይመስለኛል? ቢሆንም አንቺ
ምንም ጥሩ ባልሆን እንደማትጨክኝብኝ አውቃለሁ።" ብሎ
መልክት ላከላት። ፅናት መልክቱን አንብባ መልሳ ለመደወል
ሰከንዶች ብቻ ነበሩ ያስፈለጓት።
"ሚኪዬ በህይወት አለህ ግን ቆይ ምን አድርጌህ ነው እሄን ያክል
ቀን ስልክህን አጥፍተህ የጠፋኽብኝ•••
አንቺ ደሞ ምን ታጠፊያለሽ ህይወቴ በሙሉ በጥፋት እና በፀፀት
የታጠርኩት እኔ ምንም አላጠፋሽም ፅናቴ ግን ልክ ነሽ ጠፍቻለሁ
በዚህ ሰአት እንኳን አንቺን ለምን እንደጠፋሁ አስረድቼ
የማሳምንበት የተፈጠረውን ነገር አምኜ መቀበል ያቃተኝ ደካማ
ሰው ኾኛለሁና ጥዬቄሽ ሳይሆን ድጋፍሽ ብቻ ነው የሚያስፈልገኝ
ፅኑዬ ባንቺ ውስጥ የድሮውን ሚኪ ማየት እፈልጋለሁ ሚኪ
ጠፍቶብኛል ፅናቴ! ሚኪን አጥቼዋለሁ። ቅጣቴ በዛና የድሮውን
ደስተኛ እና ሳቂታ ዉን ሚኪ አጥፍቶ ሌላ ሰው አደረገኝ ። እኼንን
ሚኪ አላውቀውም ፅናት እህቴ እባክሽ ወደራሴ እንድመለስ
እርጅኝ•••"
እሺ ሚኪዬ እባክህ ከዚህ በላይ ያንተን ጉዳት የመስማት አቅሙም
የለኝም አሁኑኑ እመጣለሁ የት እንዳለህ ንገረኝ!"
ሚኪ እና ፅናት ሲያወሩ ጆሮዋን ደቅና ስታዳምጥ የነበረችው
ሰራተኛ ስልኳን ወዳስቀመጠችበት ክፍሏ ተንደረደረች።
እነፅናት ቤት ውስጥ ካሉት ሶስት ቋሚ ሰራተኛች መሀል አንዷ
ስትሆን ብርኬ አጥምዶ በመተዋወቅ በገንዘብ ሀይል የፅኑን
እንቅስቃሴ እየተከታተለች መረጃ እንድታቀብለው በገዛ ቤታቸው
ቃል አቀባይ አድርጎ የሾማት ተባባሪው ነች።
ስልኳን አንስታ ደወለች ። የብርኬ ስልክ በሚጠጣበት ግሮሰሪ
ውስጥ ስታቃጭል ድምጿን ግሮሰሪው ውስጥ የተለቀቀው ሙዚቃ
ቢውጠውም ብርዃኗን አይቶ አነሳት •••
"ሄሎ አዲስ ነገር አለ እንዴ?
በደንብ እንጂ ልትወጣ እየለባበሰችልህ ነው!
ወዴት እንደምትኼድ አጣርተሻል?
ወደ ሚኪ!
ሚኪ! መጣ እንዴ ?ብሎ ጮኸና ብርጭቆው ውስጥ ያለውን
ውስኪ ጨለጠው።
ብምንድን ነው የምትኼደው ግቢ ውስጥ መኪናዋ አለ እንዴ?
ምናልባት የጋሽዬን ይዛ ከወጣች እንጂ የሷን ወንድሟ የሱ ገራዥ
ስለገባች ይዞባት ወጥቷል።አለችው ቃል አቀባዩ የነ ፅናት የቤት
ሰራተኛ።
" በይ አሁኑኑ ከቻልሽ የመኪናውን ጎማ አተንፍሺው ካልሆነ•••ብቻ
እሷ ቶሎ እንዳትወጣ የሆነ ነገር አድርጊ ብሎ መልሼ ደውላለሁ
ከስልክሽ እንዳትርቂ ብሎ ስልኩን በመዝጋት እንዴት ሳይነግረኝ
መጣ ብሎ እየተብከነከነ ወደ ሚኪ ደወለ።ሚኪ ስልኩ ሲጠራ ገና
እንደተመለከተው•••
"አቦ ወደዛ ተፋታኝ አንተ ምክረ ደረቅ የሆንክ ሰውዬ እስካሁን ባንተ
ምክር ኼጄ የቀናኝ ነገር የለም! አሁን ለምን እንዲህ አታረግም?
እንዲህ ማድረግ እኮ አልነበረብህም እያለ ቁስሌን የሚያመረቅዝ
ሳይሆን ቁስሌን የሚያክም የሚያድን ሱው ነው ማግኘት
የምፈልገው ወደ እራሴ እስክመለስ ተወኝ አትደውልብኝ !"
አለ ስልኩን ሳያነሳው በብስጭት እጁን እያወናጨፈ ።
ብሩኬ ሚኪ ስልኩን ባለማንሳት በገነ! ተቁነጠነጠ። ወደ ፅናት
ስልክ ደወለ ። እሷም አታነሳም። በንዴት እየተወናጨፈ ግሮሰሪው
አከባቢ ወደ አቆማት መኪናው ገባ።
ትንሽ እንደኼደ ወደ ሰራተኛዋ ደወለ•••
አነሳች። 'ወጣች እንዴ? ኧረ አልወጣችም። እንዴት እስካሁን
ለባብሳ አልጨረሰችም ወይስ እንዳልኩሽ ጎማውን አስተነፈሽላት።
እእእ ጋሽዬ ሲገቡ የመኪናውን ቁልፍ የት እንዳስቀመጡት አይቼ
ስለነበር አንስቼ የወደቀ እንዲመስል ወደ አንድ ጥግ
አሽቀነጠርኩላት።
እኼው እቤትውስጥ አንዴ ወደ ላይ አንዴ ወደ ታች
እየተመነቃቀረች በመፈልግ ላይ ነች።
አይ አንቺ ስማርት (smart) እኮ ነሽ ። በቃ ቀረብ ስል ሚስኮል
አረግልሻለሁ ያኔ ቁልፉን አገኘሁልሽ ብለሽ ትሰጫታለሽ ሌላው
ደግሞ ባለፈው የተነጋገርነውን እቅድ ሁለትን ነገ እንጀምራለን ምን
ማረግ እንዳለብሽ የነገርኩሽን አረሳሽውም አደል?
አረሳሁትም።
እስቲ ንገሪኝ?
እንዴ የሱ ምኛት የላከችለት ደብዳቤ ላይ ሊገኛት የሚችልበትን
ስልክ አስቀምጣ እንደነበር ብሩኬ ስለማይመቸው ደብዳቤውን
ላንተ እንትሰጥህ ለፅናት ሲሰጣት ስልኩ የተፃፈበትን ሌላኛውን ገፅ
በማውጣት አጣሁት እራስህ ስጠው ብላ ለብሩኬ
እንደምትመልስለት ከወንድሟ ስትማከር መስማቴን ። ከዛ ምኛት
ጋር ደውለው ስራ እናስገባሽ ብለው በወንድሟ ሀሳብ አመንጪነት
ፅናትና እና ወንድሟ አንድ ክፍል ውስጥ አግተው እንዳስቀመጧት
ምግብ የማደርስላት እኔ እንደሆንኩና ታሪኳን ስታጫውተኝ
አሳዝናኝ ለሱ እንደደወልኩለት የዚህ ሴራ ዋና ተግባሪ የፅናት
ወንድም እንደሆነ ከነገርከኝ ታሪክ እያጣቀስኩ እግተዋለው"
በቃ የኔ ቆንጆ ነብሴን አስደሰትሻት በቃ አሁን ትንሽ ቆይቼ ሚስኮል
ሳረግ ቁልፉን ስጫት።
ጥዋት ሚስኮል ሳደረግልሽ ደሞ ሚኪ ጋር ደውለሽ ጋችው
ካካካካ። ባለፈው በሰጠሁሽ ስልክ ላይ ቻው ቻው።"
እነፅናት ሰፈር ደርሶ የመኪናውን መብራት አጠፋፍቶ አንድ ጥግ
አቆመና ለሰራተኛዋ ሚስ ኮል አደረገላት።
ወድያው ቀልፉን አገኘሁት ብላ ስትሰጣት ከእጇ ላይ መንትፋ
ሮጠች ። በሰከንዶች ውስጥ የነፅናት የውጪ በር ወደ ጎን
ተንሸራቶ ተበረገደ። የአባቷን ቪ ስምንት(V-8) መኪና ከግቢ ይዛ
በመውጣት ቁልቁል ተፈተለከች።
ብሩኬ የያዛትን ቪትስ(vitz) አስነስቶ የፅኑን መኪና እንድትከተል
ሲያስጨንቃት ሳቋ መጣባት ሲበዛባት ተናደደች የምታወጣው
ድምፅ ያቅሜን እየኼድኩ ነው እንግዲህ ከዚህ በላይ ልፈንዳልህ
እንዴ? የሚል መልክት ያዘለ ይመስላል።
በቅርብ ርቀት እንዳይከተላት በመሀል እየገቡ እንቅፋት
የሚሆኑበትን እየተሳደበ እሱም እየተሰደበ እስቴድየም አከባቢ
ሲደርሱ በሱና በፅናት መኪና መካከል ከአራት ያላነሱ መኪናዎች
አሉ።
ቀና ብሎ ከፊት ለፊቱ ያለውን የትራፊክ መብራት ደቂቃ
ሲመለከተው ቄሌው ተገፈፈ። የትራፊክ መብራቱ ፅናትን ካሳለፈ
ቡኻላ እሱን ካስቆመው ፅናት ልታመልጠው ነው። ያ ከሆነ ደግሞ
ምን ያኽል እንደሚበሳጭና ምን አይነት አዳር እንደሚያድር
ያውቀዋል።
አይሆንም•••አይሄንም እያለ እየቶሽለከለከ ከአቅማ በላይ ጋለባት
ፅኑ የትራፊክ መብራቱን አለፈች ። ከፅኑ ጀርባ ያለው ሌላኛው
መኪና እንዳለፈ ደቂቃው አበቃ። ቀዩ መብራት ቦግ አለ። ከብሩክ
ፊት የነበረው መኪና ለማለፍ ከነበረው ፍጥነት ባንዴ ሲጢጢጢ
አርጎ ፍሬን በመያዝ ቀጥ አለ። ብሩኬ ከውኻላ መጥቶ ተላተመ።
በአከባቢው የነበሩ እግረኛች እየጮኩ ወደ ብሩኬ መኪና
ተሯሯጡ። ከጀርባዋ ምን እንደተፈጠረ ያላወቀችው ፅናት ለሚኪ
ልትደርስ ከአከባቢው ተሰወረች....

.............ይቀጥላል............

150 ከገባ#ክፍል 49 ዛሬ ይለቀቃል