Get Mystery Box with random crypto!

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ▣ | የፍቅር ጎጆ

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_36


ደራሲ:- ቤዛዊት ፋንታዬ



... "ጊዲዮን ትኩርት እንዲስጠው የሚፈልግ ሰው ነው። ስለዚህ
የፈለገውን አረግለታለው ብዬ አልተልፈሰፈሰም። አሁኑኑ
እሄድለታለው። ግን ቦታውን አላውቀውም ፣ምን ብዬ የት ብዬስ
እሄዳለሁ ቁጭስ ብዬ እንዴት ያሰችለኛል። አምላኬ ሆይ እርዳኝ"
አለ በልቡ አዳም።
፨ሄዋን ጋር ተመልሶ ቁጭ አለ ከእዛ ብድግ አለ አይኑ
ፈጠጠ።ፊቱ በጣም ተቀያይሯል ፋራቻ፣ሀዘን እና ጭንቀት
ይታይበታል ሄዋን የአዳምን ሁኔታ አስተዋለች። "ምን ሆነካል?
አዳም አለችው ደንገጥ ብሎ "አይአይ ምንም አልሆንኩም" አለና
ትንፋሽ ወሰደ። ዲና መጥፎ ነገር እንደተፈጠረ ቢገባትም ግን ምን
አንደሆነ ጉዳዩ አልታውቅም።
አዳም በእጁ የያዘውን ስልኩን አበራና ዲና ጋር ደወለ።
በሶስተኛው ጥሪ አነሳችው።አዳም "ኡፍፍፍፍፍ ዲና" አለ። ዲናም
"እ አዳምዬ ምነው በረዥሙ ተነፈስክ" አለችው።አዳምም
አይደለም አይ አይ ምንም አሁኑኑ ወደቤት ተመለሱ
ጊዲዮን እየተከተላቹ ነው የት ነው ያላችውት ግን?" አላት።
ዲና "ቆይ መልሼ ልደውልልክ" ብላ ዘጋችው። አዳም ወደ ሄዋን
ተመለስና ቁጭ አለ። ከዛም ደሞ ብድግ አለ። ትግስት አጣ
በረንዳ ላይ ወጥቶ መንጎራደድ ጀመረ። በጣም ጨነቀው 5 ደቂቃ
ከቆየች በኋላ ዲና ደወለች። አዳም ፈጠን ብሎ አነሳው።
አነሳው።" የት ናቹ ? አሁኑኑ ነይ ወደቤት ተመለሽ እባክሽ ቶሎ ኑ
በፍጥነት። ጊዲዮን እናንተ አከባቢ ነው። ያለው በጣም ጨንቆኛል
ኑ አሁኑኑ አላት።
ዲና በፍጥነት "እሺ እሺ መጣን" ብላ ስልኩን ዘግታ ወደ ቦስ
እየተጣደፈች ሄደችነና "ቦስዬ ፍጠን አሁኑኑ ቤት መሄድ
አለብን"አለችው። ቦስ ግራ ተጋብቶት "እሺ ግን ለምን ገና
መምጣታችን እኮ ነው" አላት። ዲና ኡፍፍ ፈጠን እነግርሀለው
አለችው እሺ በቃ ብሎ ተነስተው ሄዱ።
መኪና ውስጥ ለምን እንዲ እያጣደፈች እንዳስቀመጣቸው
ቢጠይቃትም ዲና ግን "በኋላ አስርዳካለው አሁን በሰላም ቤት
እንድንደስ ፀልይ" ከማለት ውጪ ምንም መልስ
አልሰጠችውም።እንድትነግርው በጣም ጨቀጨቃት ግን እሷ
ልንዳበት እባክህ አትጨቅጭቀኝ ብላ ዝም አለች። ቁጣዋን አይቶ
ደንግጦ ዝም አለ።
የአዳም ስልክ ጮከ ጌዲዮን ነበር።አነሳው ጌዲዮን "ስማ
ጠበቃ አዳም ያቺ አጨብጫቢክ በፍጥነት ካለችበት ያንን አብሯት
ፉዞ አብራ ይዛ የከነፈችው እንዳየዋት ነግርካት ነው። ከጠበቃነት
ባሻገር ማቃጠር ይዋጣልካል ልበል" አለው።
አዳም ክትክት ብሎ "አዎ አዎ አቃጣሪ ነኝ።እና ምን ይሁቆይ አንተ
እርጉም ትስማኛለክ እኔ ግን እንዳንተ አቃጣሪ አደለሁም ያንተ
ማቃጠር በጣም በዛ መጀመሪያ ደውለክ ያቃጠርከው አንተ አደለክ
እንዴ?"አለው።ጊዲዮን ተናደደ።
"አንተ ደደብ አንተ አቦራ እኔ ጌዲዮን ነኝ ሰማከኝ አደል?"አለው።
አዳም ሳቀና ትስማኛለክ ሰው ስድብ የሚያበዛው ሲያብድ ነው
አንተ ደሞ እብድ ነክ እኔ አንተን አልፈራክም አንተ ማለት ለእኔ
ምንም ነክ። አንተ ማለት ለእኔ ተራ ስው ነክ ተራ ምክንያቱም እኔ
ጠንካራ ነኝ፣ ምክንያቱም እኔ ካንተ በጣም የተሻሸሽኩኝ ነኝ፣
ምክንያቱም አንተ በሰው እንጂ በራስክ ሀይል አትንቀሳቀስም
ምክንያቱም" ሲል። ጊዲዮን እርር ብሎ በቃ በቃ ይበቃካል
ትስማኛለክ ብታከብረኝ ይሻልካል ያለ በለዚያ እኔ ነኝ መጨርሻክ"
አለው።
አዳም አይ ተሳስተካል መጀመሪያዬም መጨርሻዬም የፈጠረኝ
ፈጣሪ ነው። ገዳይ ሲያርፈፍድ ማች ይገሰግሳል አሉ። ሲለው
ጊዲዩን ተናዶ ስልኩን ጃሮ ላይ ጠርቀመው። ወዲያው ዲና ደውላ
አዳምዬ እቤት ልንደርስ ነው በር አስከፍትልን አለችና ስልኩን
ዘጋችው።አዳም ዘበኛውን ጠረቶ በር ክፈት ወዳጄ አለውና እቤቱ
ገባ። ቤት ሲገባ ሄዋን ሶፋው ላይ ተኝታለች። እንደ ድሮ ቢሆንማ
እቅፍ አድርጎ ወደ መኝታ ክፍሏ ወስዶ ባስተኛት ነበር።
አዳም አሁን ማርግ የሚችለው ነገር ሄዋን ላይ ፎጣ ነገር ጣል
ማድርግ ብቻ ነው። እናም መኝታ ቤት ገብቶ ፎጣ አምጥቶ
አለበሳት ። ትኩር ብሎ እያያት ትውስታዋን ሳታጣ በፊት
ስላሳለፉት ነገር እያሰበ በሀሳብ ተጓዘ።
ለእርፍት ወደ እሱ ቤት ስትመጣ ስራተኞችን እና ዘበኛውን
እርፍት በሚል ሰበብ ወደሚፈልጉት ለ 3 ወይም ለ4 ቀን
ይለቃቸዋል። ከዛም ከሄዋን ጋር በጋራ ምግብ ሲበሉ ፣ቤት
ሲያፀዱ ፣ አትክልት ሲኮተኩቱ፣ ውሀ እየተርጫጩ ሲጫወቱ፣
ሲላፉ፣ እሱ መፀሀፍ እያነበበላት እሷ ደሞ ደርቱ ላይ ልጥፍ ብላ
ስትስማው።
በድንገት ዲና መጥታ ጀርባውን መታ አድርጋ ከሀሳብ
አነቃችው።አዳም ዲናን አያት "መጣቹ ኡፍፍፍፍ ተመስገን ቦስስ" አላት። ዲና በፉገራ ፊት እያሳየችው "ጊዲዮን ወሰደው" ብላ ሶፉ ላይ ዘፍ አለች። አዳም
በረገገ "ምን ምን ምን እያልሽ ነው ቆይ የምትይውን ታውቂዋለሽ?"
አላት። ዲና ፈገግ ብላ አንተ ኧረ ተው ቀልድ ይግባክ አሁን ቦስን
ቢወስደው እኔ እንዲ ተርጋግቼ እቀመጣለው። ተርጋጋ ስንመጣ
አንተ ፈገግ ብለክ ሀሳብ ውስጥ ነክ ብንጠራክንም ስላልስማክ
ቦስ ልብሱን ሊቀይር ክፍሉ ገባ"።አለችው። ከዛ ዝምታ
በመካከላቸው ሰፍኖ ነገሰ።ሁለቱም በተለያየ መንገድ በአንድ
አይነት ሀሳብተመሙ።
ቦስ ከሳሎኑ ደርጃ እየውርደ "ሄ ጋይስ አር ዩ ኦኬ"ሲል ሄዋን
ከተኛችበት ተነሳች። ወደ ቦስ እያየች "እንዴ መቼ መጣቹ?"
አለችው። ቦስ ትንሽ ቆየን ገና ገብቼ ለልብሴን መቀየሬ ነው
አላት። ሄዋን ወደ ዲና እያየች እና እንዴት ነበር አለች። ቦስ
ሊመልስላት ሲል ዝም እንዲል ምልክት ሰጠችው። ዲና
አላስተዋለችም ዲና ተክዛ አንገቶን አቀርቅራ ሀሳብ ውስጥ ገብታለች፣ አዳምን
አየችው እሱም በበኩሉ አንገቱን አንጋጦ በሀሳብ ተጠምዶል።
ሄዋን ብሶጭት ብላ እናንተ አለቻቸው በርግገው ከ ሀሳባቸው
ነቁ።ዲና አቤት እህቴ ተነሳሽ ፤እንዴ መቼ ተነሳሽ ፤ ቆየሽ ከተነሳሽ
እያለች የጥያቄ ናዳ አወርደችባት። አዳምም አቤት ሄዋን ምነው
አናገርሽኝ አለ።
ሄዋን በሸቀች "ምነው ግን እናንተ መዳፋቹ ላይ ቁጭ አርጋችሁ
እርሳችሁን ምንድነው ችግራቹ። ትንሾካሾካለቹ ከዛ ትስቃላቹ፣ከዛ
ትተክዛላቹ ከዛ ታኮርፋለቹ
እ ተናገሩዋ አሁን ለምጠይቃቹ ጥያቄ መልስ እፈልጋለው ስለ እኔ
ትክክለኛ ማንነት ዛሬ አሁኑኑ ትነግሩኛለቹ በሉ ጀምሩ...

ይቀጥላል...


.............. ••● ●•..............

☛ በ 𝚈𝙾𝚄𝚃𝚄𝙱𝙴 ይከታተሉን

https://bit.ly/2XS2ecv

☛ በ 𝙵𝙰𝙲𝙴𝙱𝙾𝙾𝙺 ይከታተሉን

https://bit.ly/3ja9o3O

☛ በ 𝙸𝙽𝚂𝚃𝙰𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን

https://bit.ly/3rM2yop

☛ በ 𝚃𝙴𝙻𝙴𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን

https://bit.ly/3mDyzfx

◎◦#ሼር◦◎
◎◦#ሼር◦◎

@Yefiker_Gojo || @AbenaG
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━