Get Mystery Box with random crypto!

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ ▣ | የፍቅር ጎጆ

​​. ​ ◉●◦ አለሜ ነሽ ◦◉

ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ

አንብበው ሲጨርሱ ሼር ያርጉ

#ክፍል_35


ደራሲ:- ቤዛዊት ፋንታዬ



... ዲና ሄዋን ጋር ሄዳ ስትቀመጥ "እህቴ አለቻት" ሄዋን ፈገግ ብላ።
ዲናም በተራዋ "ወዬ ወዷ እህቴ" አለቻት። ሄዋን የሚያንቦርቅ
ድምጿን ቀነስ አድርጋ "ስሚ ከ እዛ ስውዬ ጋር አይንሽን መንቀል
አልቻልሽም ምነው በሰላም ነው?። አለቻት በአገጯ ወደ ደርጃው
የሚወጣውን ቦስ እየጠቆመች።ዲና "ፍቅር ያዘኝ መሰለኝ"
አለቻት። ሄዋን ፈገግ ብላ "የምርሽን ነው? ለነገሩ እሱም ያፈቀርሽ
ይመስለኛል" አለቻት። ዲና "ያርግለኝ" አለችና ተሳሳቁ። ከዛ ዲና
"አሁን ሀገሩን አስጓብኝቼው ልመጣ ነው አንቆይም እሺ አዳም
ካንቺ ጋር ይቆያል" አለቻት ሄዋን "በለው እሺ እሺ ውዴ ቻው"
አለቻት።
ቦስ ለባብሶ አምሮበት መጣ። ዲና "ዋው ቆንጅዬ ሆነካል እኔም
መጣው ለባብሼ" ብላ ክፍሏ ሄዳ እሷም ዘንጣ መጣች። ቦስ እና
ዲና ተያይዘው ወጡ። አዳም "ሄዋኔ" አላት።ሄዋን "አቤት"
አለችው።"ሲሻልሽ እኛም እንወጣለን እሽ ብዙ ቦታ አዝናናሻለው"
ሲላት። "በእውነት ማልልኝ ቃል ግባ" አለችው። አዳም ፈገግ
ብሎ "ገብቻለው" አላት።
ሄዋን ደስ አላት። ከዛ አዳም "ፊልም እንይ?"አላት። ዲና "ደስ
ይለኛል ግን ከእዚህ በፊት የምጠይቅህ ነገር አለ። የመጀመሪያው
ለምን በስስት አይን ታየኛለክ
፤ሁለተኛው ደሞ ባለፈው ሀኪም ቤት አለሜ ብለክ ለምን
ጠራከኝ፤ የሆነ ነገር ስሆንስ ለምን በሀይለኛው ትደነግጣለክ፤ እኔስ አንተ ከጓኔ ስትሆን በጣም ደስስ ይለኛል እነዚህን መልስልኝ
አለችው።
አዳም ፊቱ ቀላ ምን እንደሚላት ግራ ገባው። ሄዋን በጉጉት
እንዲነግራት
አይን አይኑን እያየችው ነው።አዳም በተርበተበተ ድምጽ ዲና እንደ
ነገርችሽ ነው አላት።
የአዳም ስልክ ጠራ ሄዋንን መጣው ብሏት አነሳው በርንዳ ላይ
ወጥቶ "ሄሎ" አለ። አዳም ደርቆ ቀር የጌዲዮን ድምጽ ነበር።
"እንኳን ደስ አለክ አቶ አዳም ፍቅርኛክ ከሆስፒታል መውጣቷን
ሰማው። እኔ ደሞ ይህንን ቀን ባይገርምክ በጣም ስጠብቀው
ነበር። መርዶ በጠዋት ነው ብዬ ነው እንደስማው ማታ
ያላረዳውክ በል አሁን ፍቅራችንን እንቀጥላለን ናፍቀከኝ ነበር። ደሞ ያቺ አጭር
አሸርጋጅክ ፊት ለፊቴ ከጓደኛህ ጋር እየተዝናኑ ነው። ሄዋን የወጣች ለት ነው
የመጣው አሉ ሀሀሀሀሀሀ" ሲል አዳም በብስጭት 'ትሰማለክ
ጫፍቸውን እንዳትካቸው" አለው። ጊዲዮን ግን ሳቁን እየለቀቀው
ስልኩን አዳም ጆሮ ላይ ዘጋው ለዲና ደወለ ስልኳ አይነሳም ቦስ
ስልክ ገና አልያዘም አዳም ጨነቀው። ወደ እነሱ እንዳሄድ ሄዋንን
ቢወስድብኝስ ብሎ ፈራ በሁለት ሀሳብ ተጠመደ። ሊያብድም ደረሰ...

ይቀጥላል...



.............. ••● ●•..............

☛ በ 𝚈𝙾𝚄𝚃𝚄𝙱𝙴 ይከታተሉን

https://bit.ly/2XS2ecv

☛ በ 𝙵𝙰𝙲𝙴𝙱𝙾𝙾𝙺 ይከታተሉን

https://bit.ly/3ja9o3O

☛ በ 𝙸𝙽𝚂𝚃𝙰𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን

https://bit.ly/3rM2yop

☛ በ 𝚃𝙴𝙻𝙴𝙶𝚁𝙰𝙼 ይከታተሉን

https://bit.ly/3mDyzfx

◎◦#ሼር◦◎
◎◦#ሼር◦◎

@Yefiker_Gojo || @AbenaG
━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━