Get Mystery Box with random crypto!

#እኔ ጠላሻለሁ፣ እንደ ጫማ ሽታ ልክ እንደ በሽታ ጌታ በባርያው ላይ እንደ ሚበረታ እኔ ጠላ | የፍቅር ጎጆ

#እኔ ጠላሻለሁ፣


እንደ ጫማ ሽታ
ልክ እንደ በሽታ
ጌታ በባርያው ላይ እንደ ሚበረታ

እኔ ጠላሻለሁ፣

እንደ ረጅም መንገድ
ላብታም እንደ መስገድ
ከጠጡ በኃላ እንደ መንገዳገድ

እኔ ጠላሻለሁ

ገንዘብ እንደ ማጣት
ዳገት እንደ መውጣት
ከያዘ እንደ ማይለቅ እንደ ጨካኝ ቅጣት

እኔ ጠላሻለሁ...(ወዘተ)...

ግን አሁን ፈራሁኝ ጀመርኩኝ መብሰልሰል
ጠላሁሽ ያበዛው ወድጄሽ ነው መሰል።

Daniel Mak



,,,,,,,,,,,, ,,,,,,,,,,,
••●◉Join us share◉●••

@Yefiker_Gojo ,,,,,, @AbenaG
━━━━━━✦ ✿ ✦━━━━━━