Get Mystery Box with random crypto!

የካምፓስ ህይወት_MAHIR

የቴሌግራም ቻናል አርማ yecampas_hiwet — የካምፓስ ህይወት_MAHIR
የቴሌግራም ቻናል አርማ yecampas_hiwet — የካምፓስ ህይወት_MAHIR
የሰርጥ አድራሻ: @yecampas_hiwet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.59K
የሰርጥ መግለጫ

*በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ
# የካምፓስ ህይወት
# ፍቅር
# ምርጥ ምርጥ ታሪኮች
# ቀልዶች
# ቁም ነገሮችን ያገኙበታል
ይዝናኑበታል ....ይቀላቀሉን
አስተያየት ካለዎት ለቡቱ ከሆነ👉 @Abdumah_bot or
በዚህ ደግሞ 👉 @mahmahi_bot
በዚህ ደግሞ 👉 @mahmahi_bot
መስጠት ይቻላል

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-14 23:50:06 ...┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ ).
.╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝

በ @tibebislam_nw የቀረበ
ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

ክፍል ሁለት (❷)
❃•❃ ════ ❁

አይኑን ወደአንድ ቦታ ተክሎ እየተመለከተ ይንሰቀሰቅ ጀመር። ምክንያቱን ባታውቀውም የሱ ለቅሶ ተጋብቶባት አብራው አለቀሰች። ምላሹን እየፈለገች አይኗን የአልይ አይን ላይ አንከራተተች። ትንሽ ካለቀሰ በኋላ
<< እማ...እማ ናፈቀችኝ! >> አለ እንባ በተናነቀው ድምፅ።

ሀዩ አሁን ይባስ ደነገጠች።
<< እንዴት ዛሬ ትዝ አለችህ ? >> የሷን ስሜት እሱም መጋራቱ አስገርሟታል።
<< በህልሜ አየዋት ..>> አለ። አሁንም ለቅሶውን አላቆመም። እልቅሻው ልቧን ነካው። የታደፈነውን ቁስሏን ሲነካው ተሰማት። አቅፋ ወደራሳ ካስጠጋችው በኋላ አብራው አነባች።

ዛሬ ውሎዋ በትዝታ ጀመረ። አልይን ካረጋጋችው በኋላ ሱብሂ ሰላትን ለመስገድ ስትነሳ እሱም አብሯት ተነሳ። ከሰላት በፊት የሚደረገውን ትጥበት ( ኦዱ ) አብረው ካደረጉ በኋላ አንድ ላይ ሰገዱ። እሱም ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ሰላት ውስጥ ስለሚባለው ነገር በትንሹም ቢሆን ያውቃል። አብሯት ጎንበስ ቀና እያለ የሱብሂን ሰላት ሰግደው ጨረሱ።

በስስት አይን እያየች ግንባሩን ሳመችው። ነገ እሱ ከፊት ሆኖ እንደሚያሰግዳት ታምናለች። ቁርስ ለማዘጋጀት ኩሽና ውስጥ ጉድ ጉድ ስትል እሱም ከኋላ ቀሚሷን ይዞ ይከተላታል። አልፎ አልፎ እቃ ያቀብላታል። አልይ ለሀያት ልዩ ፍቅር አለው። እሷም ልክ እንደእናት ሆና ነው የምታሳድገው።

ወፎች መንጫጫት ፣ ጎህ መቅደድ ሲጀምር የሀዩ ታናናሽ እህቶቿና አባቷ ከእንቅልፋቸው ተነሱ። መርየምና አባቷ ለመስገድ ሲሄዱ ፈቲያ ወደሀዩ ጋር መጣች።

<< ምነው አትሰግጂም እንዴ ፈቲ..>> አለቻት። ስራ ልታግዛት የመጣች ስለመሰላት...
<< አይ ሰላት የለኝም እህቴ ...>> አለች በሀፍረት አንገቷን እየደፋች። ሰላት የላኝም ማለት ሀይድ ላይ ወይም የወርአበባ ላይ ናት ማለት ነው። በዚ ጊዜ ሰላት ሰለማይሰግዱ
<< ሰላት የለኝም >> በሚለው ቋንቋ ነው የሚግባቡት። አሪፍ መግባቢያ ነው...

ከፈቲያ ጋር ሆነው ቆንጆ ቁርስ ካዘጋጁ በኋላ ተሰብስበው በሉ። ሀዩ አልይን እያጎረሰችው ለራሷ አልበላችም ማለት ይቻላል። እነሱ ሲጠግቡ ነው እሷም የምትጠግበው። አጁብ ፍቅር!

አባታቸው እንደልማዱ ትንሽ ገንዘብ አስቀምጦላቸው ወጣ። ዛሬ እሁድ ነው። ትምህርት ስለሌለ ከምትወዳቸው ወንድምና እህቶቿ ጋር ቀኑን ስለምታሳልፍ ደስ ብሏታል። ከፈቲያ ጋር እስከ 4 ሰአት ድረስ የቤቱን ስራ ሰርተው ጨረሱ። ከዛ ሰብሰብ ብለው ቁጭ አሉ። ቆንጆ ጊዜ ለማሳለፍ...

ልክ እንደሌላው ቀን መጀመሪያ የሁሉንም ደብተር check ካደረገችላቸው በኋላ የቤት ስራቸውን አሰራቻቸው። የዛሬን አያርገውና ያኔ ተማሪ እያለች ክፍል ውስጥ የሚፎካከራት ተማሪ አልነበረም። ታድያ ወንድምና እህቶቿም ከዲናቸው ቀጥሎ በትምህርታቸውም ቀልድ እንዳያውቁ አድርጋ ነው እያነፀቻቸው ያለችው።

የቤት ስራቸውን ከጨረሱ በኋላ የተለያዩ ጨዋታዎችን በመጫወት ጊዜውን ማሳለፍ ጀመሩ።

ፍቅራቸው በጣም ያስቀናል። ሀዩ እነሱን ለማሳቅ ፣ ለማዝናናት የምታደርጋቸው ነገሮች ለነሱ ያላት ፍቅር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ነው። ሀዩ ለነሱ እንጂ ለራሷ እንደማትኖር በአንድ ቀን ያያት ሰው ራሱ መገመት ይችላል።

ከዙሁር ሰላት በኋላ 8 ሰአት አከባቢ ሀዩ አልይንና መርየምን አስተኝታ ከፈቲያ ጋር ቁጭ ብላ እየተጨዋወተች ባለችበት ሰአት የቤታቸው የግቢ በር ተንኳኳ። ሀዩም በሩን ለመክፈት ተነስታ ወጣች። የግቢው በር ጋር ደርሳ ከውስጥ ወደውጪ በሚያሳይ ትንሽዬ ቀዳዳ የሰውዬውን ማንነት ለማወቅ አጮለቀች።

ሀሰን ነበር በሩን እያንኳኳ ያለው። ሀሰን ማለት ትምህርት ቤት እያለች እንደወንድም ትቀርበው የነበረ ልጅ ነው። ሀሰን በጣም ዝምተኛና ከሰዎች ጋር ብዙ የማይቀራረብ አይነት ልጅ ነው። ከሀዩ ጋርም አንድ ጊዜ አማርኛ መምህራቸው በሰጣቸው የቡድን ስራ ምክንያት ነው መግባባት የቻሉት። ሀሰን አይደለም እንደዛሬ ሴት ቤት ሊመጣ ቀርቶ ሴት እንኳን ቀና ብሎ ለማየት በጣም የሚያፍር ልጅ ነበር።

ዛሬ ግን ሀዩን ፍለጋ ቤቷ መጥቷል። ምናልባት ከትምህርት ቤት መቅረቷ አሳስቦት ይሆናል። ሀዩ ልክ ስታየው በጣም ደነገጠች። ከተማሪዎች ጋር መገናኘት አትፈልግም። ደሞ እንደወንድም የምትቀርበው ሀሰን የሷ መቅረት አስጨንቆት እፍረቱን ለሷ ሰውቶ ሊጠይቃት በመምጣቱ አሳዘናት። ልክፈት ወይስ አልከፈት በሚል ሁለት አሳብ ውስጥ ገብታ መታገል ጀመረች።

#ክፍል_ሶስት..⓷.....ይቀጥላል....
1.9K viewsIYI , 20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 23:33:10 ​​ .┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ ).
.╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝

በ @tibebislam_nw የቀረበ
ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

ክፍል አንድ ( ⓵ )
❃•❃ ════ ❁

ሀዩ በትዝታ ማዕበል ውስጥ ሰምጣ በአሮጌው የእንጨት መስኮታቸው በኩል አሻግራ ወደውጪ ትመለከታለች። የእናቷ ነገር ትዝ ቢላት፣ የናፍቆት ጅራፍ ክፉኛ ቢወግራት ከነዛ ውብ ክብ አይኖቿ መሀል የእንባ ዘለላዎች መንጠባጠብ ጀመሩ። ትናንት ልክ እንደዛሬ ሳይሆን በፊት ጠዋት 12 ሰአት ላይ ከእናቷ ቀድማ ተነስታ ኩሽና ውስጥ ትንጎዳጎድ ነበር። ትናንት እናቷ በስራ እንዳትደክም በደንብ ታግዛት ነበር። ትናንት በዚ መስኮት አሻግራ ስትመለከት እናቷ ከኋላ መጥታ ትኮረኩራትና እየተሳሳቁ ይጫወቱ ነበር።

ግን ትናንት ነው። ነበር ተብሎ የሚወራ ከልብ እንጂ ከእይታ የጠፋ ታሪክ። የማይመለስ ትውስታ... ሀያት ገና 16 አመቷ እያለች ነበር እናቷ ወደአኼራ የሄደችው። ከ3 ታናናሽ ውንድምና እህቶቿ እንዲሁም ከአባቷ ጋር ጥላቸው ላትመለስ ካሸለበች ድፍን ሁለት አመት ተቆጠረ።

ይሀው ዛሬም የሱብሂ ሰላትን ለመስገድና በዛውም የቤት ውስጥ ስራዎችን በጊዜ ለመጀመር ስትነሳ የእናቷ ትዝታ ገረፍ አርጓት ነው ከዚ መስኮት የከተመችው። ድምፅዋ እንዳይሰማ እጇን በአፏ ይዛ ተነሰቀሰቀች!!

እናቷ ሰፈር ውስጥ በጣም ተግባቢ ፣ ሁሉም ሰው የሚወዳትና ለሰዎች በጣም አዛኝ ሴት ነበረች። በእናቷ ምክንያት ሀዩም ሰፈር ውስጥ ብዙ ሰው ያውቃታል። ታድያ እናቷን የሚያውቁ ሁላ እሷ ከሞተች ውዲ ትምህርት ቤት አለመሄዷና ቤት ውስጥ እንደሰራተኛ ሆኗ መቀመጧ ያሳሰባቸው ይመስላል። ለዚም ነው ሁሉም << አግቢ አግቢ >> እያሉ የሚጨቀጭቋት። << ሀብታም ወንድ አግብተሽ ታናናሾችሽንም ትረጃለሽ >> ይሏታል። እሷ ግን << እነሱን ጥዬ የትም አልሄድም።የኔ ህልም እናቴ የሰጠችኝን አማና ( አደራ ) መወጣት፣ ታናናሾቼን አስተምሬ ለወግ ለማዕረግ ማብቃት ነው! የኔ ቀስ ብሎ ይደርሳል።>> ብላ አሻፈረኝ ብላለች።

አባቷ አይደለም ዛሬ ሚስቱ ሞታ ድሮውንም ፀባዩ አስቸጋሪ ነበር። ግን ቢያንስ እሷ ስትኖር አደብ ይገዛ ነበር። አሁን ግን በሷ ሞት አሳቦ ቤተሰቡን ከረሳ ሰንበትበት ብሏል። አዎ ጠዋት ወጥቶ ማታ ከመመለስና አልፎ አልፎ ለአስቤዛ ብሎ ከሚሰጣቸው ጥቂት ገንዘብ ውጪ እንደድሮ ለነሱ መሳሳቱ ፣ አብሮ መጫወቱ ፣ ሁሉም ቀርቷል። የአባትነትን ፍቅር ያኔ እናታቸው ስትቀበር አብሮ ተቀብሯል።

ሀያትም ከቀን ወደ ቀን ውበቷ እየቀነሰ ፣ ሰውነቷ እየመነመነና ተስፋዋ እየተሟጠጠ መቷል። የሰዎች << አግቢ >> የሚለው ጭቅጨቃና የጓደኞቿ << ለምን ትምህርት ቤት አትመጪም? >> የሚሉ ጥያቄዎች ስለሰለቿት ከሰዎች እራቃ ከታናናሾቿ ጋር ብቻ ማሰላፍ ጀምራለች።

<< ሀዩ..ሀዩ...>> አለ የ7 አመቱና የቤቱ የመጨረሻው ልጅ አልይ... ከእንቅልፉ ቀድሞ መነሳት ልማዱ ነው። እጁንና እግሩን ለማፍታታት እየተንጠራራ ከታኛበት ፍራሽ ብድግ አለ።

ፊቷ ላይ እየተንሸራተተ ወደመሬት የሚወርደውን እንባ አይቶ እንዳይረበሽ በማለት እንባውን ከአይኗ ጠራርጋ ወደአልይ ጋር ዞረች። መሬት ላይ የተነጠፉ ሁለት ያረጁ ፍራሾች ይስተዋላሉ። በአንዱ አልይና በቅርቡ 11 አመቷን የያዘችው ታናሽ እህቷ መርየም ተኝተውበታል። በአንዱ ፍራሽ ላይ ደሞ እሷን በደንብ የምትቀርባት ፣ በእድሜም ከእሷ በ2 አመት ብቻ የምታንሰው ሌላኛዋ ትናሽ እህቷ ፈቲያ ተኝታለች።

<< አባቴ ተነሳህ እንዴ?? >> እያለች ወደ አልይ ጋር ሄደች። አጠገቡ ሄዳ እንደተቀመጠች አልይ ማልቀስ ጀመረ። ሀያት በጣም ደነገጠች። አሁን ሲጠራት እኮ ምንም አልሆነም ነበር። አልይ ሲያለቅስ የሷ ውስጥ አብሮ ያለቅሳል። ታናናሾቿ አንድ ቀንም ቢሆን እንዲከፉና እንዲያዝኑ አትፈልግም። ለዛ ነው ይሄን ሁላ መስዋትነት ከፍላ ፣ ከጓደኞቿ በታች ሆና እየኖረች ያለችው።

<< ምነው አባቴ ምን ሆንክብኝ? >> አለች ከአይኑ የሚፈሱትን የሚያሳሱ እንባዎችን በእጇ እየጠረገች።

#ክፍል_❷....ይቀጥላል....
2.0K viewsIYI , 20:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-09 13:56:03 #ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ


#ክፍል10_የመጨረሻው_ክፍል


አብዱ ከክፍሉ ይዞኝ ወጣና ቦታዬ አስቀምጦኝ ቤቱን ለቆ ወጣ ጀማል መጣና ይዞኝ ወጣ ሰርግ ቤት ሳይሆን ለቅሶ ቤት ነበር የሚመስለው አባም እማም መጡ አይኔን ግን አላዩም ነበር በስራቸው ተፀፅተው ይመስለኛል እያለቀሱ ከቤት ወጣን።

እነሱ ቤት ስንደርስም ሰው በሽ ነው ምንም የቀረ ነገር የለም የታሰበበት ነው የሚመስለው።እኔ ግን ምንም ፊቴ አልተፈታም ተበላ ተጨፈረ ይዞኝ ወደራሱ ቤት አቀናን የኔ ሚዜዎች የለበስከለትን ቬሎ ቀያይረዉልኝ ሄዱ። ሽማግሌ ከተላከበት ቀን አንስቶ እስአ አሁን እንቅልፍ የሚባል አልተኛሁም አልጋው ላይ በተቀመጥኩበት እንቅልፍ ሸለብ አደረገኝ ትንሽ እንደተኛው ነቃ ስል አጠገቤ ጀማል ተቀምጧል ወደኔ ጠጋ ሲል አበድኩ ምን ያላልኩትት ነገር አለ ክፍሉን ለቆ እንዲወጣ ነገርኩት ምንም አላለኝም ወጣ በሩን ከዉስጥ ቆልፌ የሆንኩትን እያስታወስኩ አነባው ከማልቀሴ የተነሳ ፊቴ ፍም መስሏል ራስ ምታት ሊለቀኝ አልቻለም በዛው እንቅልፍ ወሰደኝ.......በማግስቱም ተመሳሳይ ነገር ነበር የተፈጠረው።

በ ሶስተኛው ቀን መልስ ተጠራን በጣም ነበር ደስ ያለኝ እንደዛ ቀን የተደሰትኩበትን ቀን ሁላ አላስታውስም ወላሂ...መልስ ሲባል ያሰብኩት መመለሴን እቤት የምቀር ነገር ነበር ግን አይደለም ሄድን አሪፍ ዝግጅት አድርገው ነበር። 5 ሰአት አካባቢ የተሰጠኝን ስጦታ ጭነን መጣን ትዳር ሲባል የራስን ስሜት ማዳመጥ ብቻ አይደለም የባል ሀቅ የሚባለውም ነገር አለ ምንም ማድረግ አልችልም ላያስችል አይሰጥም አይደል የሚባለው..ወላሂ በዛን ሰአት ጀማልን ቀና ብዬ ሳየው ራሱ ይቀፈኛል ራሴን ጠላዋለው ቢሆንም ግን ምንም አማራጭ አልነበረኝም ቢጃማዬን ቀይሬ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ እንዳልኩ ጀማል መጣ ሰውነቴን እንደ እሾህ ይወጋኝ ጀመር ከዛን ሰአት በኋላ ምን ይፈጠር ምን ልሁን የማውቀው ታሪክ የለም ብቻ ስነቃ ያስተዋልኩት ማማ ግርግዳውን ተደግፋ ታለቅሳለች ሳሎን ላይ ተዘርሬ ብርድ ልብስ አልብሰውኛል ሁለት ሼኽዎች በግራና በቀኝ ቁርአን ይቀሩብኛል ዙሪያዬ በቤተሰቦቼ ተከብቤያለሁ።.....ከዛን ጊዜ በኋላ ተለከፍኩ ጊዜ እየጠበቀ ህመሜ ይነሳብኛል ቁርአንም ቤት እመላለሳለው።

አንድ ቀን እንደ ወትሮ ቁርአን ሲቀራብኝ እለፈልፍ ጀመር ለካስ የዚ ሁሉ መንስኤ ሀምዛ እና እናቱ ነበሩ ሱብሀንአላህ እኔ በህይወቴ በትዳሬ ደስተኛ እንዳልሆን አስደግመውብኛል ወላሂ ይሄንን ሳውቅ ሀምዛን ከልቤ እርግፍ አድርጌ አወጥቼ ጣልኩት ሀምዛንኮ ሌላ ባገባ ብወልድ ራሱ አልረሳውም ነበር...ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ በህይወቴ ምንም ደስታ አልነበረኝም 2 ልጆች አሉኝ ደስታዬ ግን አልነበረም አልሀምዱሊላህ ይሄን ስራቸውን ካወኩኝ በኋላ ቁርአንም መከታተል ስቀጥል ደስታ ወደ ቤቴ ገባ። ጀማል ይሄን ሁሉ ታገሰኝ ሁሌ ያዘነች ሚስት ቤት ውስጥ እያየ ሁሌ ያኮረፈች ሴት እያየ ኖሯል ሆኖም ግን አንድ ቀን እንዲህ ሆኜ ብሎኝ አያውቅም ታገሰኝ ይህንን ሳስብ እሱን ይበልጥ እንድወደውና እንዳከብረው አደረገኝ።

አልሀምዱሊላህ ከዛን ጊዜ በኋላ ደስተኛ ነኝ አሁን ላይ ትምህርቴን ጨርሼ ተመርቄ በተመረኩበት ሞያ ላይ እየሠራው ነው ሶስተኛ ልጄን ወልጃለው ለሁሉም ግን አልሀምዱሊላህ...........


#ተፈፀመ....
2.4K viewsIYI , 10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-06 23:59:59 #ኢማን

#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ


#ክፍል9

ወደ 7 ሰአት ገደማ ሰርገኛ መጣ በእልልታም ተቀበሉት። ምሳ ተበላ ተጨፈረ ኒካም ታሰረ ብናይ አይወጡም ብናይ አይወጡም። የሆነ የሰፈር ህፃን ልጅ መጣና በጆሮዬ " ልክ ቀለበቱን እጅሽ ላይ ሲያጠልቅ እኔን ከልብሽ አውጥተሽ አትጣይኝ ሁሌም አኑሪኝ" የሚል ከ ሀምዛ የተላከ መልእክት ነበር ውስጤ ተረበሸ ግራ ገባኝ እያለቀስኩ ሳለ የ አባ ወንድም አጎቴ መጣ
"እ ኢሙ ተበላ ተጠጣ መዝናኛ እንሂድ እየተባለ ነው ፎቶ ተነስታቹ አመሻሽ ላይ ትመለሳላቹ" ምን ትዝ አለኝ አንዷን ጓደኛችን እንዲህ ብለው ማይሆን ነገር ሰርተዋታል ማለት ወሰዷት እቤታቸው የሷ በቤተሰብ ቢሆንም ወዳዋለች ግን እኔስ?? ሃሃሃሃ በጣም ትሸውዱ የለም እንዴ በል ንገራቸው እንዳልተስማማው
"አረ እንደሱ አያደርጉም ካደረጉማ 20,000 አስይዘናል ይቀጣሉ" ታድያ ለኔ ምን ያደርግልኛል ከሄድኩ በኋላ እናንተ ትበሉበታላቹ ትጠጡበታላቹ በቃ ሲያቅተው አብዱን ጠራው ያው ቀረቤታዬም ከሱ ጋር ስለሆነ ምንም ቢለኝም አምነዋለዋ።
እ አብዱ የሚለው እውነቱን ነው?
"አዎ እውነቱን ነው" አለኝ አይ እንደሱ ከሆነማ እሺ ብዬ ስነሳ ዘወር ብሎ በምልክት እንቢ በይ አለኝ አረ አልፈልግም አልሄድም አልኩ ድጋሜ አጎት ተብዬው ተናዶብኛል ከፈለጋቹ እነሱ ከሄዱ በኋላ እኛ ሄደን እንዝናናለን አልኩት።

እንደዚህ እየተከራከርን 12 ሰአት ሆነ እነ ሀምዛ ቤት ተረብሸዋል ይሄ ነገር የምር እዚህ የሚደርስ አልመሰላቸውም ነበር ማዘርየው አልመጡም መረጃ የሚያመላልስ አለ ከኔ ወደነሱ ከነሱ ወደ እኔ መጨረሻ ላይ ጀማልን ጥሩልኝ ብዬ መጣ።
ቆይ ግን ያምሀል ምን ብላቹ ነበር መጀመሪያ እእእእ
"አንቺ ራሱ ምንድነው የምትይው እኔ ትምህርትሽን ስትጨርሺ እና የማስተካክላቸው ነገሮች አሉ ስጨርስ ብዬሽ አልነበር በአንዴው ምን ተለውጦ ነው ካልወሰድከኝ የምትይው"??
በጣም ደነገጥኩ ምን እንደሚያወራ ራሱ ግራ ገብቶኛል በሰአቱ ለካ ይሄን ሁሉ የሚጠነስሱት የኔ አጎት እና የሱ አባት ነበሩ። አባ እና እማ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም የሱ አባት ልጅቷን ይዘን ካልሄድን ከዚህ ንቅንቅ አንልም አሉ አማም አባም ግራ ተጋብተዋል እኔን ተነሽ ሂጂ እንዳይሉ እጎዳባቸዋለው የመጣውንስ ሽማግሌ እንግዳውን ምን ብለው ተነስታቹ ውጡ ይላሉ? ተያይዘው ወጥተው መስጊድ ሄደው ማልቀስ ጀመሩ። ህዝብም ደሞ መጨረሻውን ሳናይ ንቅንቅ አንልም ብለዋል መሰለኝ የሚወጣም የለም በቆሙበት እርስ በእርሳቸው ይንሾካሸካሉ ትወጣለች አትወጣም የሚለውን በመሀል አባን ጥሩልኝ ስል ነው እንደሌሉ ያስተዋልኩት
ቆይ በአላህ ከኔ ከልጃቸው ሽማግሌ በልጦባቸው ነው የሸሹት? እ ለምንድነው መተው ማያባርሩልኝ ሁሉም እኔን እያየ የሚያለቅስ እንጂ ምንም የሚለኝ ጠፋ።

ማንም ከጎኔ ሊቆም አልቻለም ነበር መጨረሻ ላይ ተሸነፍኩ የተሸነፍኩትም አብዱ መጣና ይዞኝ ባዶ ክፍል ገብተን እንዲህ አለኝ
"በቃ ኢሙ አልቻልኩም ወላሂ ብዙ ጣርኩ አቃተኝ ከዚህ በላይ ምን ላርግልሽ እእ "ስቅስቅ እያለ ነበር የሚያለቅሰው
በቃ አብዱ አንተም ተሸነፍክ ምንም ተስፋ የለኝም ማለት ነው ከጎቴ በሩን እየቀጠቀጠ አንተ ነህ ልጅቷን የምትመክራት ተዋት ትሂድበት ይለዋል
"ኢሙ ሰማሽ አይደል ሁሉም እኔን እየወቀሱኝ ነው ኢሙዬ ከዚህ በላይ መታገል አልችልም ይቅርታ"እያለ እግሬ ስር ወደቀ
የኔ የ ኢማን ህይወት እዚህ ጋር አበቃ ማለት ነው እንጫወታለን ብለን ተጫወቱብን አይደል? አቅፌው መንሰቅሰቅ ጀመርን።


#የመጨረሻው_ክፍል10_.........
2.2K viewsIYI , 20:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 10:11:12 #ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


#ክፍል8

ቤት ሁሉም ለ ሰርጉ ሽር ጉድ ማለቱን ተያይዘውታል የቀረ ሰው ያለ አይመስለኝም ከ ክፍለ ሀገር የ እማም የአባም ቤተሰቦች መተዋል። አንድ የ እማዬ ወንድም አለ በጣም ነው ምወደው ሚወደኝ ምንም ብነግረው ይረዳኛል እሱ የመሰለው ፍቃደኛ ሆኜ እንደማገባ ነው ነገሩን ሲሰማ ግን የተገላቢጦሽ ነው
"ያልገባኝ ነገር ለምንድነው ይሄን ያህል ጀማልን የምትጠይው?"
ምን ብዬ የምወደው ሰው ስላለ ልበለው የቱንም ያህል ብቀርበው ይሄንን ማውራት ግን አልቻልኩም
በቃ ቀልቤም አይወደውም በዛ ላይ ተማሪ ነኝ.....
"እህ እሱ ታዲያ መች ልውሰድሽ አለ ኢሙ ትምህርትሽን ጨርሰሽ ነውኮ ምትገቢው"
አብዱ እንዴት ነው በአላህ የምጠላውን ሰው አግብቼ ምኖረው?
" እሱ ከሆነ ቀላል ነው የምትጠይውን ሰው መውደድ ትችያለሽ ዋናው ነገር ጊዜ ነው በጊዜ ሂደት ማይለወጥ ነገር የለም ም/ቱም ኒካህ ነው ሚታሰርልሽ በጊዜ ሂደት ስትገናኙ ትወጂዋለሽ"
አይ አልወደውም አይ አልወደውም እያልኩ እንባ ተናነቀኝ
" እሺ ኢሙ እንደሱ ከሆነ አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን እቃ ስትገዛዢ አታብዢ ትንሽ ትንሽ ግዢ በጊዜ ሂደት ካልወደድሽው ኒካሽ ይወርድልሻል የገዛውንም እቃ ታስቦ እኔ አመልስለታለው"


አልሀምዱሊላህ የሆነ ነገር ቅልል አለኝ።አብዱ እንዳለኝም ወርቅ የእጅ እና የጆሮ ብቻ ገዛው ልብስም ሁለት ቅያሬ ሂጃብም እንደዛው ገዝተን ተመለስን እነ ማሚ ሲያዩት በጣም ነበር የተናደዱብኝ " ምንድነው ቁንጥር ቁንጥር ያለ እቃ ምትገዢው" እያሉ ተራ በተራ ጮሁብኝ ያሰብኩትን ማውቀው እኔ ነኝና ያሉትን ከምንም አልቆጠርኩትም

የኒካው ቀን ደረሰ የሰው ጫጫታ ሽር ጉዱ ሲታይ ግን ኒካ አይመስልም ነበር መቆሚያ ቦታ ራሱ የለም።የሰፈር ሰው ሁሉ ተጠርቷል ማንም አልቀረም።የመጀመሪያ ሚዜ ሰሚራ ናት ሁለቸኛ የ አክስቴ ልጅ ሀያት ሶስተኛም ዘመዴ ናት ሰአዳ። ከ ሚዜዎቹ ጋር አንድ ሀሳብ መጣልን " ሲታይ ገንዘብ ሚያወጣ አይመስልም ለምን ተናዶ እንዲተው ወጪ አናበዛበትም?"ሀያት ነበረች "እውነቷን ነው ቬሎ ተከራይ እንበለው" አለች ሰአዳ ደወልንለትና መከራየት እንደምንፈልግ ነገርነው አሺ ወደ ማታ ላግኝሽ ብሎኝ ጨረስን ማታ አካባቢ ከ ሀዩ ጋር ሄደን ተቀብለን በማግስቱ ሄደን ተከራየን መልካም ጋብቻ የሚል ፅሁፍ አፅፈን መጣን። በኛ ቤትኮ። እቃ እቃ መጫወታችን ነው አይ ልጅነት ሌላ ነገር አናስብምኮ በቃ የኒካው ቀን ደረሰና ለብሼ ተቀምጫለው ቤቱ ፏ ብሏል ሰው መምጣት ጀምሯል አጎት ተብዬው መጣ ሲያይ ቬሎ ለብሻለው ሲያይ መልካም ጋብቻ ይላል ጠራኝና
"አንቺ ግን እብድ ነሽ ወላሂ ብልጥ ትመስይኝ ነበርኮ ከመች ጀምሮ ነው ለ ኒካህ ቬሎ ሚለበሰው ምንድነውስ ጋብቻ ማናምን ያላቹት"!!!!
አረ አብዱ እኛኮ ምንም አስበን አይደለም አልኩት
"ምን ለነገሩ ቬሎ ስለለበስሽ ይወስድሻል ማለት አይደለም ፏ በይበት እንደውም" ብሎኝ ነገሩን ቀለል አደረገው።

#ክፍል9....ይቀጥላል......
2.1K viewsIYI , 07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-04 12:23:59 #ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


#ክፍል7

እንደዛ እየባለ ህይወት ቀጠለች። አሁን ላይ ትምህርትም ስለተጀመረ ሀምዛን አየዋለው በማናገር ደረጃስ ብትሉኝ አናወራም እሱም ለኔ የተጨነቀ ይመስላል በአይን ብቻ ነበር ምናወራው ከ 7 ወር በኋላ ግን ህይወቴ ምስቅልቅሉ ወጣ አባ ጫማ ቤት ሲሰራ ምሳ እኔ ነበር ምወስድለት ጀማልም እዛው አጠገብ ሱቅ ነበረው ስመላለስ ያየኛል ለ አባም ሊያገባኝ እንደሚፈልግ ይነግረዋል አባና እማ ተነጋግረው ጨርሰዋል ፍቃደኛነታቸውን ገልፀውለታል አባ ከ 7 ወር በፊት ልጅ ናት አሁን አልድራትም ያለው አሁን ተቀየረ በትውውቅ ይሁን በሼም ወላሁ አእለም የሚገረረመው ደሞ የኔ ፍላጎት ሁላ አልተጠየቀም ምንም አላውቅም ሰጀምር like እንደ ክፍለ ሀገር ነው ሚያስቡት የኛ ቤተሰብ ደሞ ወግ ያጠብቃሉ አባም ከ ሀምዛ ጉዳይ በኋላ የኔ ነገር ሳያሳስበው አልቀረም መንገድ ላይ ስንሄድ ሁላ ለምን ወንዶች አዪሽ ብሎ ነበር ሚቀያየረው ትኩረት መስጠት ጀመረ። ማሚን የሰፈር ወንዶች "እቺን ልጅሽንማ ጠልፈን ነው ምንወስዳት" ይሏታል የዛኔ ልጅነትም አለ ቀይ ቀጠን ረዘም ያልኩ ስትስቂ ደስ ትያለሽ እባላለው ይመስለኛል ስስቅ ጉንጮቼ ላይ የሚወጣው ስርጉድ ውበቴን አግዝፎ ያወጣዋል አባ አሁን ሀሳብ የሆነበትን ጉዳይ ሊገላገል ነው....ተነገረኝ ያው ምንም ማድረግ አልችልም ዝም ነበር ያልኩት ጀማል ከ ትምህርት ቤት ስወጣ ይጠብቀኛል የሁል ጊዜ መልሴ ተማሪ ነኝ ነበር ሌላ ምንም አልለውም አይደለም እሱን አግብቼ መኖር ይቅርና እሱን ማየት ራሱ አልወድም ነበር ሆኖም የኔ ፍላጎት መች ተጠበቀ ጀማልን ባገኘሁት በ ወሩ ሽማግሌ ተላከ ለሀምዛ ማን እንደሚነግረው አላውቅም ብቻ ግን ይሰማ ነበር ከዛ በኋላ ነው አራስ ነብር የሆነው።

የሆነ ቀን ከ ት/ቤት ስወጣ ጠበቀኝ ሳየው ደስ አለኝ ዘለሽ ተጠምጠሚበት ይለኛል ውስጤ ሀይማኖቴ አይፈቅደውም እንጂ "ሰላም አለይኪ" አለኝ በቀዘቀዘ ድምፅ ወአለይከ ሰላም አንገቴን ደፍቼ ነበር ማወራው "ኢሙ አስችሎሽ ነው ግን ከኔ መለየቱ....እእእ ለነገሩ አንቺ መች ፈለግሺኝ አንቺ የያዝሽው ምርጫ ነው አይደል እስከ አሁንም እየጠበቅሽ ያለሽው ገንዘብ ሀብት ያለውን ነው" እንዲ ሲለኝ በጣም ነበር የተናደድኩት እኔ ነኝ ያለሁበትን ጭንቀት የማውቀው ማንምም ሊረዳኝ አልቻለም ...ምንም አይነት መፍትሄ የለኝም! ምን እንድሆን ነው ምትጀየፈልገው እእእ!! ሁለታችንም ተረብሸናል እሱም እንድንጠፋ ጠየቀኝ ምንም ያህል ባስበው አንድም ቀን ይሄ ሀሳብ መቶልኝ አያውቅም ሀምዛ ትዳር ማለት የ ሁለት ሰዎች ህይወት ብቻ አይደለም እነሱ ደስተኛ ካልሆኑ እኛም ጋ ደስታ አይኖርም። " ልክ ነሽ ኢሙ ሀራም ላይ እንወድቃለን"ወላሂ እንዲህ ሲያስብ ይበልጥ እንድወደው አደረገኝ አንዳንዴ የማትጠብቁትን ነገር በማትጠብቁት ቦታ ታገኙታላቹ ዱርዬ ነው ብዬ ያሰብኩት አስተሳሰቡ ግን ማሻ አላህ...ተያይዘን እነሱ ቤት ሄድን ለ እናታቸውም ነገርናቸው "ልጄ አንቺን ከልጅነትሽ ነበር ለልጄ ምከጅልሽ ቢሆንም ግን ቤተሰቦችሽ ሳይፈቅዱ ምንም የሚሆን ነገር የለም አላህ አንድ ላይ ትሆናላቹ ካላቹ ትሆናላቹ ካላለውም አላለውም ነው"....

#ክፍል8_ይቀጥላል........
2.0K viewsIYI , 09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-03 05:17:25 #ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ

#ክፍል6

የዛን ቀን ነገራቶች እንዳለ ተደበላልቀውብኛል መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠኝ ሁላ ምኞቴ ነበር የአባዬን አይንማ እንዴትም አላየውም መጥፋት አለብኝ አልኩ ልብሴን ሰብስቤ የት እንደምሄድ ባላውቅም ወጣሁ ትንሽ እንደተራመድኩ አይ ይሄ መፍትሄ ሊሆን አይችልም አባዬን የባስ እንዲናደድብኝ አደርገዋለው ብዬ ማንም ሳያየኝ ተመልሼ ገባው አሁንም ሱቅ ሄድኩ ሰኢድ ዘመዳችን ነው የኛን ሱቅ ተረክቧል ሰኢድ በረኪና ስጠኝ አልኩት ለካ ወሬዉን ሰምቷል አልሰጥም አለኝ በቃ በዛን ሰአት ወላሂ ራሴን ላጠፋ ብዙ ነገር ሞክሬ ነበር አንድ እምነት ግን ነበረኝ ይሄ ሁሉ ነገር መፍትሄ አንደማይሆን መምሸቱ አልቀረምና መሸ ጨንቆኛል አባ መምጫው ሰአት ደርሷል ኡስታዝ ሰሚራን እያስቀሩ ነው ኢማንስ ካሉሽ ዛሬ ተረኛ ቡና ምታፈላው እሷ ናት በያቸው ብያት ነበር "ዛሬ ኢሙ ምን ሆና ነው መታ ማታፍዘው? ሌላ ቀንስ ተሽቀዳድማ ነበር ምትመጣው"አሉ ኡስታዝ ወጥቼ መጨረሻ ላይ ሀፍዛለው ኡስታዝ.....ሰሚራ ጨርሳ ጠራችኝ ልክ ቁርአኑን ከፍቼ መቅራት ስጀምር እምባዬ ቀደመኝ በቃ መቅራት አልቻልኩም በሁኔታዬ ኡስታዝ ሹአይብ ሳይደናገጡ አልቀሩም "ኢሙ ምነው ምን ነካሽ"? በዛን ሰአት ለማንም ያልተናገርኩትን ምንም ሳላስቀር ነገርኳቸው። ደብዳቤውን አባ እንዳገኘው እና አፈይቱ አስደርገለልኝ ብዬ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ "ተይ እንጂ ኢማን አንቺ ጎበዝ ልጅ ነሽ ካንቺ ብዙ ነገር እንጠብቃለን አብሽሪ" አሉኝ ወዲያው እማም አባም ተጠሩ አባዬ በጣም እንደተናደደ ያስታውቅበታል "እንግዲህ ኢማን ባለማወቅ አጥፍቻለው ይቅርታ ይደረግልኝ ድጋሚ አልደግመውም እያለች ነው አፉታቹን ትሻለችና ይቅርታ አድርጉላት" ሹአይብ ነበር ያሉት "እስኪ በአላህ የትኛው ደራሲ ነው ይሄን የሚፅፈው? እ እኔኮ ኢሙ እንዲ አልጠብቅሽም ባንቺ ላይ ያለኝን እምነት እያወቅሽ"!! አባ እንዲ ብሎ ሲናገር ውስጤ ተረበሸ በራሴ አዘንኩ ይሄን ያህል አስከፍቻቸዋለው? እማ ጥግ ላይ አፏን ይዛ ትሰማለች ምንም ምትናገረው ነገር የለም እግራቸው ላይ ተደፍቼ ይቅርታ ጠየኩኝ እንደማልደግመውም ቃል ገባው። በቃ ቤት ውስጥ እንደ እስረኛ ተቀምጫለው።

ከ ሳምንት በኋላ በ ኡስታዝ ሹአይብ በኩል ሰው መጣ ያው ትዳር ምናምን ነገር ማለት ነው ማክሰኞ ማታ ኡስታዝ ጠየቁኝ እንደዚ እንደዚ አይነት ሰው ጠይቋል ኒካ አስሮ ነው ሚያስቀምጥሽ ትምህርትሽን ስትጨርሺ ይወስድሻል። ተናደድኩባቸው ሀምዛኮ ሲጠይቀኝ ልጅ ነሽ። አልደረስሽም ብላቹኝ ነበር አሁን እንዴት እእ?? አልፈልግም አልኩ "ሀምዛኮ አንቺን ነው እንጂ ቤተሰብሽን አልጠየቀም በዉጪ በውጪ ሊያበላሽሽ ነው የፈለገው ይሄ ግን በ ሀላል መንገድ ነው ላግባሽ ያለው ልዩነቱን አስቢ እንጂ" የሆነው ይሁን አልፈልግም ብዬ በአቋሜ ፀናው። አላስጨነቁኝም እሺ ብለው ወጡ....በድጋሚ ኡስታዝ ያገባችው የሷ ወንድም ቤተሰብ ጠየቀ ኡሱም እንደዚው ትምህርቷን ትጨርስ ኒካህ ብቻ ነው ልሰር ያለው እማ ተስማማች አባ በፍፁም አይሆንም አለ አልሀምዱሊላህ ወላሂ ይሄ ሁሉ ሲሆን ልቤም ሀሳቤም ሀምዛ ጋር ነው ከተያየን ቆይተናል ቢሆንም ልረሳው አልቻልኩም...

#ክፍል7_ይቀጥላል
1.9K viewsIYI , 02:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 09:46:28 #ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ
#ክፍል5

ሁሉን ነገር ዛ ላይ ደመደምኩት ምክንያቱም ከሷ ምደብቀው ነገር የለም ቢያንስ ይሄንን መንገር ትችል ነበርኮ ዛን እንድጠላ ሚያደርጉ ጥያቄዎች ይፈታተኑኝ ነበር ከጊዜ በኋላ ሀምዛም ሊተወኝ አልቻለም ባገኘው አጋጣሚ ሊያዋራኝ ይፈልጋል ት/ቤት በር ላይ እየመጣ ያዋራኛል እስከ ሰፈር ሸኝቶኝ ይመለሳል እሱ ያወራል እኔ ሰማለው ግን ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠውም ነበር እሱን ማየት ያስደስተኛል ስሜቴን ግን ግልፅ አድርጌ አለረነግረውም ክረምቱም መጣ ትምህርት ተዘጋ በጣም ነበር የከፋኝ ሌላ ሳይሆን ሀምዛን ከዚ በኋላ የት እንደማገኝ ነበር ሀሳብ የሆነብኝ....

ወሩ የ ረመዳን ወር ነው ረመዷን ላይ ማታ ማታ ተረዊህ ሰላት እኔ እና ሰሙ ተራ በተራ እንሄዳለን ደስ ነበር የሚለኝ በዛዉም ሀምዛ ካለ በአይኔ እፈልገው ጀመር ግን የለም ጠፋ ጠፋ መጥፋቱ ያሳስበኝ ጀመር ዛን እንዳልጠይቃት እንደበፊቱ አይደለንም። ከ ሳምንት በኋላ ሳየው ደስ አለኝ ሳገኘው ሲርየስ ምንም እንደማይገባው ገገማ ነበር ምሆነው ሲያዋራኝ መልስ የለም ዝም.."አንድ ቀን ስታድጊ የኔ ስቃይ ይገባሻል" በሱ ምክንያት ብዙ ነገር እንደተቀየረ አልገባውም.....በመሀል ለ ማሚ ወሬ ተነገራት አይ ሀበሻ ሰውን ባዩበት ማዋል ይፈልጋሉ እማ መጀመሪያም ያንን ቤተሰብ አትወዳቸውም አይደለም ይሄን ሰምታ ያው ግን ልጅ ናትም ብላ ስለምታስብ ይሁን እንጃ ቀለል አርጋ ነው ያየችው "ከዚ በኋላ እንዳላይሽ ከዛ ቤተሰብ ራቂ" ሁሌም ጥያቄ ሚሆንብኝ ግን ለምን ይሄን ያህል ትጠላቸዋለች የሚለው ነበር እማ በተፈጥሮዋ ሰው ትወዳለች ትቀርባለችም እነሱን ግን ለምን.....ሃሃ ታምኑኛላቹ ግን ይሄ ሁሉ ሲሆን ሀምዛ ምኔ እንደነበር እንኳን አላውቅም ከ ሰላምታ እና ከ ወሬ ውጪ ስንገናኝ ራሱ አናስብም።

ማማ ካወቀች አባ መስማቱ አይቀርም የ አባን እምነት ማጣት ግን ሳስበው ራሱ ያመኛል። አንድ ቀን ደብዳቤ ፃፍኩለት ደብዳቤው ላይም ቤተሰቦቼ እንዳወቁ ከሱ ጋር ድጋሚ መታየት እንደማልችል አንድ ቀን ግን አላህ ፈቅዶ እነደምንገናኝ ነበር። ስፅፍለት ግን ሙሉ በሙሉ እንዲተወኝ አልፈለኩም ተወኝ አትተወኝ አይነት ነገር አለ አይደል።በዛን ሰአት ከቤተሰቦቼ ትዕዛዝ መውጣት አልችልም ነበር በደብዳቤው ላይ የተጠቀምኳቸው ቃላቶች በጣም የሚደንቁ ነበሩ እንኳን አይደለም እኔ ትልቅ የሚባለው ራሱ ሊጠቀመው አይችልም ከጨረስኩ በኋላ ድጋሚ ፅፌ አንዱን እቤት አስቀመጥኩ አንዱን ሰፈር ሲመጣ ሰጠሁት ያስቀመጥኩበት ምክንያትያው ለራሴ ደግሜ አነበዋለው ብዬ ነበር እማ ቁርአን ቤት እንዳንሄድ አስጠነቀቀችን ኡስታዝ ቤት መቶ እንዲያስቀራን ተደረገ የሆነ ቀን ማታ ደብዳቤውን ሰሚራ ከቦርሳዬ አገኘችው ለአባዬ ሰጠችብኝ......አባ ሁሌ አለሜን ምታሳየኝ ኢሙ ናት በሰጠችው ነገር የ ኢማን አይደለም እንዳይል ከኔ ቦርሳ ነው የተገኘው የኔ ፁሁፍ ነበር ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔ ምንም አላውቅም እቃ እያጠብኩ ሰሚራ ከደብዳቤው አንድ አንድ ቃል እያወጣች በአሽሙር ታወራለች ደነገጥኩ ተጠራጠርኩ ይሄ ነገር እኔ የፃፍኩ አይደል እንዴ? እማ ቤት አለነበረችም መጣች "ኢማኔ እኔ የወለድኩሽ ቀን በምጥ አልተቸገርኩም ዛሬ ያማጥቁትን ያህል ጨነቀኝ ዛሬ አባትሽ ይገልሻል ምን ላድርግሽ የት ወስጄ ልደብቅሽ"? አይ እማ ከኔ በላይ እሷን ነበር የጨነቃት....

#ክፍል6_ይቀጥላል.................
1.9K viewsIYI , 06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 09:56:58 #ኢማን

#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ


#ክፍል4

እማ የዛን ቀን በጣም ተናዳብኝ ነበር። ቀጥ ብላ እሷ ቤት ሄደች እዛም የለሁም መድረሳም ሄደች እዛም የለሁም በሌላ መንገድ አቋርጬ ቤት ገብቼ ነበር አቤት የዛን ቀን የመታችኝን መቼም አልረሳውም ወላሂ እማ ዛን አትወዳትም ሁል ጊዜ ከዚች ልጅ ጋር ያለሽን ነገር አቁሚ ጀርባዬ አይወዳትም ትለኛለች።

የሰርጉ ቀን ሁሉም ተማሪ ሄዷል እኛም ፏ ብለናል በመሀል የመንዙማ ካሴት ተፈለገ እኛ ቤት ስለነበር ላመጣ ሄድኩ ካሴቴን ይዤ እየመጣው ሀምዛ መንገድ ላይ አገኘኝ የያዝኩትን ካሴት ተቀበለኝ ብለምነው ብሰራው አልሰጥ ሲለኝ ተናድጄበት በቆመበት ትቼው ሄድኩ እንደደረስኩ ሲጠይቁኝ ነገርኳቸው። ከሌላ ቦታ ተፈልጎ መጣና ቀኑ አለፈ ሀምዛ በዚህ ካሴት የመጣ እንድንቀራረብ ፈልጎ ነበር ያደረገው ያው ሳገኘው መጠየቄ የት ይቀራል ያው እንዳሰበውም ሳይሆንለት አይቀርም በትንሽ ጊዜ ውስጥ እየተቀራረብን መጣን ከ ት/ቤት ስወጣ ይጠብቀኛል ወደ ሰፈር ይሸኘኛል በቃ...ያኔ እንደ አሁኑ ስልክ የለም ተገናኝቶ ጊዜ ማሳለፍ የለ በቃ በአጋጣሚ ነው ሁላ ምንገናኘው።

በዛችው ሳምንት ውስጥ ምግብ መብላት አቆምኩ ገና ለገና ምግብ ሳይ ያቅለሸልሸኛል እንቅልፍ የለም ያለ ምክንያት ማልቀስ ነበር ስራዬ እንደዚ መሆኔ ያሳሰባቸው ቤተሰቦቼ በጣም ተጨንቀው ነበር በተለይ አባ ከስሬ አይጠፋም ነበር ሲደጋገምባቸው ሀኪም ቤት ይዘውኝ ሄዱ ከምርመራው ውጤት በኀላ ምንም እንደሌለብኝ ነፃ እንደሆንኩ ተነገረን ከወጣን በኋላ አባን ብቻውን ጠርቶ "ያው ምርመራው ላይ ምንም የሚታይ ምልክት የለም ሆኖም ግን የሚያስጨንቃት የምታስበው ነገር ካለ ቀርበው ያናግሯት" አለው አባም አመስግኖት ተሰናብቶት ወጣ ዛ ስጠፋባት ልትጠይቀኝ መታለች ሁሉ ነገር ነገርኳት ስነግራት ከት ብላ ትስቅብኛለች ተናድጄባታለው ወላሂ እንዳልሞት ያክል ልብላ እንጂ ትቻለው ማለት ይቻላል።

በማግስቱ ጠዋት ስራዬን ጨርሼ ዛ ጋር መሄድ ፈለኩ እማ.. "ወዬ ኢሙ አመመሽ እንዴ" በተደናገጠ ድምፅ አይ እማ ደብሮኛል ዘሀራ ጋር ልሂድ? "አልተውም አልሽ አይደል በይ እሺ ቶሎ ደርሰሽ ነይ"! አሺ ብያት ወጥቼ ሄድኩ ቤታቸው ስገባ ኮርኒስ እየተሰራ ነበር ሚሰራው አናፂ መሀሪ ነበር ስለምንተዋወቅ ሰላም ብዬው ቤት ገባው ሰላም አለይኩም... "ወአይኩም አሠላም"የ ዛ እናት ነበሩ "ግቢ ልጄ ግቢ" ዛ መጣች ሰላምታ ተለዋወጥን እናቷን ለበቀደሙ ይቅርታ ጠየኳቸው እንዳልተከፉብኝ ነገሩኝ ምስኪን የሆኑ እናት ናቸው በተለይ ለኔ መንገድ ላይ ስንገጣጠም እንኳ ተነስተው ነበር ሰላምታ ሚሰጡኝ ሰው እንዴት ለ ትንሽ ልጅ ይሄን ያህል ክብር ይሰጣል ለዛ ለዛም በጣም ወዳቸዋለው አኛ አያወራን እነሱ ሻይ እያፈሉ ያልጠበኩት ሰው መጣ......ሀምዛ ግቢ ውስጥ ቆሞ ሚሰራውን ያያል ዛ ይሄ ልጅ እኮ ነው የነገርኩሽ....እዚህ ምን ይሰራል ባለፈውም አየሁት አናፂ ነው እንዴ? መስማቷን ትታ ያለማቋረጥ ትስቃለች ምንም ሊገባኝ አልቻለም ለካ ይሄን ሁሉ ሙሉ ቤተሰብ ያውቃል እንድንቀራረብ ነበር የሚፈልጉት ወንድሟ እንደሆነ ነገረችኝ በጣም ነበር የደነገጥኩት የፈላውን ሻይ ትቼው ቀጥ ብዬ ወጣው ዛ ከኋላ እየተከተለች እንድመለስ ትማፀነኛለች በዛን ሰአት የሷን ወሬ ሳይሆን እማ ያለችኝ ነበር ትዝ የሚለኝ ካለችኝ ነገር ጋ ተገጣጠመብኝ ህመሜም በነሱ ምክንያት እንደሆነ አሰብኩ ደስ የሚለው ስሜት ጠፍቶ ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ውስጥ ገባው።

#ክፍል5_ይቀጥላል.......
2.0K viewsIYI , 06:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 08:43:12 #ኢማን
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሠረተ


#ክፍል3

ከዛን ቀን በኋላ አስበው ነበር በድጋሚ በሳምንቱ በተመሳሳይ ሰአት ሱቅ ቆሜ መጣ አሁንም "ውሀ ይኖርሻል"? አለኝ ሰጠሁት ጠጥቶ አመስግኖኝ ሄደ እህ ይሄ ነገር ምንድነው ማነውስ ልጁ ምንስ ፈልጎ ነው.. ከራሴ ጋር መከራከር ጀመርኩ ከዛን ቀን በኋላ ሁል ጊዜ ሰፈር አየው ጀመርኩኝ ከሩቅ አይቶኝ ተመልሶ ይሄዳል እኔም ነገሩ ተደጋገመብኝ እሱን እጠብቅ ነበር ሰበብ ፈልጌ ያለ ምክንያት ከቤት ወጣለሁ እንደ አጋጣሚ ሆኖም እንተያያለን ተመልሶ ይሄዳል ከሰፈር እስኪርቅ በአይኔ እሸኘው ነበር ደሞ ሲገጣጠም በር ላይ የ እማዬ ጉሊት አለች የሌለብኝን እኔ ነኝ ምጠብቀው እያልኩ ወጣለው ከምር አሁን አሁንማ ከቀረ ሁላ ይደብረኝ ጀመር። ሃሃሃሃሃ የሚገርመኝ እኮ ምንም የምናወራው ወሬ የለም Just በአይን መተያየት ብቻ......

አንድ ጓደኛዬ አለች ዘሀራ ትባላለች የኔ ከምላቸው ሰዎች አንዷ ናት። መድረሳችንም ት/ቤታችንም አንድ ቦታ ነው።ዛ ከኔ በእድሜ ትበልጣለች አንድ ቀን መድረሳ ቁጭ ብለን ኡስታዝ ልታገባ እንደሆነና ሙሉ ጀመአው እንደተጠሩ ተነገረን።የዛን ቀን ማንም ሚያስቀራን አልነበረምየ ዛ ቤት ከ ኡስታዝ ቤት ጎን ለጎን ነው" ኢሙ በአላህ ኡስታዝ እንሂድ እእ በዛውም ድባብን አይተን እንመጣለን"? የ ዛ ጥያቄ ነበር አረ ዛ እማዬ መሄዴን ካወቀች ትናደድብኛለች ይቅርብን አልኳት "ምን ሆነሻል እንዴትም አታውቅም እዚህ መቀመጡ ለውጥ የለውም ባይሆን እስኪወጡ እንደርስባቸዋለን እእ"

ከዚህ በላይ አልቻልኩም ነበር ተያይዘን ወደነ እሱ ቤት አቀናን በሩን ከፍተን ስንገባ እናቷ እና ያ እንደውም ሰፈር ሚመጣው ልጅ ተቀምጠዋል በጣም ነበር የደነገጥኩት ያለ ማካበድ እግሬ ሁላ ሲንቀጠቀጥ ይታወቀኛል "አሀ ልጄ ሰላም አለይኩም ምነው በር ላይ ቆምሽ ነይ ግቢ እንጂ" የዛ እናት ነበሩ ወአለይኩም አሠላም እማ ብዬ የሠላምታቸውን አፀፋ መለስኩ ወይ መቀመጥ ለራሴ ድንጋጤ ውስጥ ነኝ ዛ ብዬ ተቻኩዬ ወጣሁ ተከትላኝ ምን እንደሆንኩ ጠየቀችኝ ምንም ብዬ የ ዛን እናት ምንም ሳልላቸው መውጣቴ ትዝ ያለኝ መንገድ ላይ እየሄድኩ ነበር ዛ በአላህ ማማን አፈይቱ አስደርጊልኝ እያናገሩኝ ትቻቸው ወጣሁኮ...አረ አብሽሪ ብላኝ ወደ ኡስታዝ ቤት አቀናን ኡስታዝ የተደናገጠች ትመስላለች ሰው ጉድ ጉድ ይላል "ኢሙ ቁርአን የለም እንዴ" ማንም የለም ብለን ነው አለች ዘሀሩ ታዲያ ቢሆንስ ቁጭ ብላቹ አታጠኑም ነበር? ብላ ተቆጣች ወዲያው ተሰናብተናት ወደ ቤታችን አቀናን....እቤት እሳት ተቀጣጥሏል የቁርአን ቤት ልጆች ተለቀዋል ሰሚራም ቤት ገብታለች ኡሚ ቁርአን ቤት አብራቹ አልነበራቹ እንዴ ብላ ስትጠይቃት አጅሪት ከ ዘሀራ ጋር ወተው ሄዱ ብላ ንግር አይ ሰሚራ የተለየች ፍጥረት ናት ወሬ መደበቅ አትችልበትም እኮ.........

#ክፍል4_ይቀጥላል.......
2.2K viewsIYI , 05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ