Get Mystery Box with random crypto!

...┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓ .' ከራስ ሽሽት '. | የካምፓስ ህይወት_MAHIR

...┏─━─━─━∞◆∞━─━─━─┓
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ ).
.╚─━━━━━━░★░━━━━━━─╝

በ @tibebislam_nw የቀረበ
ልብ አንጠልጣይ ታሪክ

ክፍል ሁለት (❷)
❃•❃ ════ ❁

አይኑን ወደአንድ ቦታ ተክሎ እየተመለከተ ይንሰቀሰቅ ጀመር። ምክንያቱን ባታውቀውም የሱ ለቅሶ ተጋብቶባት አብራው አለቀሰች። ምላሹን እየፈለገች አይኗን የአልይ አይን ላይ አንከራተተች። ትንሽ ካለቀሰ በኋላ
<< እማ...እማ ናፈቀችኝ! >> አለ እንባ በተናነቀው ድምፅ።

ሀዩ አሁን ይባስ ደነገጠች።
<< እንዴት ዛሬ ትዝ አለችህ ? >> የሷን ስሜት እሱም መጋራቱ አስገርሟታል።
<< በህልሜ አየዋት ..>> አለ። አሁንም ለቅሶውን አላቆመም። እልቅሻው ልቧን ነካው። የታደፈነውን ቁስሏን ሲነካው ተሰማት። አቅፋ ወደራሳ ካስጠጋችው በኋላ አብራው አነባች።

ዛሬ ውሎዋ በትዝታ ጀመረ። አልይን ካረጋጋችው በኋላ ሱብሂ ሰላትን ለመስገድ ስትነሳ እሱም አብሯት ተነሳ። ከሰላት በፊት የሚደረገውን ትጥበት ( ኦዱ ) አብረው ካደረጉ በኋላ አንድ ላይ ሰገዱ። እሱም ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ሰላት ውስጥ ስለሚባለው ነገር በትንሹም ቢሆን ያውቃል። አብሯት ጎንበስ ቀና እያለ የሱብሂን ሰላት ሰግደው ጨረሱ።

በስስት አይን እያየች ግንባሩን ሳመችው። ነገ እሱ ከፊት ሆኖ እንደሚያሰግዳት ታምናለች። ቁርስ ለማዘጋጀት ኩሽና ውስጥ ጉድ ጉድ ስትል እሱም ከኋላ ቀሚሷን ይዞ ይከተላታል። አልፎ አልፎ እቃ ያቀብላታል። አልይ ለሀያት ልዩ ፍቅር አለው። እሷም ልክ እንደእናት ሆና ነው የምታሳድገው።

ወፎች መንጫጫት ፣ ጎህ መቅደድ ሲጀምር የሀዩ ታናናሽ እህቶቿና አባቷ ከእንቅልፋቸው ተነሱ። መርየምና አባቷ ለመስገድ ሲሄዱ ፈቲያ ወደሀዩ ጋር መጣች።

<< ምነው አትሰግጂም እንዴ ፈቲ..>> አለቻት። ስራ ልታግዛት የመጣች ስለመሰላት...
<< አይ ሰላት የለኝም እህቴ ...>> አለች በሀፍረት አንገቷን እየደፋች። ሰላት የላኝም ማለት ሀይድ ላይ ወይም የወርአበባ ላይ ናት ማለት ነው። በዚ ጊዜ ሰላት ሰለማይሰግዱ
<< ሰላት የለኝም >> በሚለው ቋንቋ ነው የሚግባቡት። አሪፍ መግባቢያ ነው...

ከፈቲያ ጋር ሆነው ቆንጆ ቁርስ ካዘጋጁ በኋላ ተሰብስበው በሉ። ሀዩ አልይን እያጎረሰችው ለራሷ አልበላችም ማለት ይቻላል። እነሱ ሲጠግቡ ነው እሷም የምትጠግበው። አጁብ ፍቅር!

አባታቸው እንደልማዱ ትንሽ ገንዘብ አስቀምጦላቸው ወጣ። ዛሬ እሁድ ነው። ትምህርት ስለሌለ ከምትወዳቸው ወንድምና እህቶቿ ጋር ቀኑን ስለምታሳልፍ ደስ ብሏታል። ከፈቲያ ጋር እስከ 4 ሰአት ድረስ የቤቱን ስራ ሰርተው ጨረሱ። ከዛ ሰብሰብ ብለው ቁጭ አሉ። ቆንጆ ጊዜ ለማሳለፍ...

ልክ እንደሌላው ቀን መጀመሪያ የሁሉንም ደብተር check ካደረገችላቸው በኋላ የቤት ስራቸውን አሰራቻቸው። የዛሬን አያርገውና ያኔ ተማሪ እያለች ክፍል ውስጥ የሚፎካከራት ተማሪ አልነበረም። ታድያ ወንድምና እህቶቿም ከዲናቸው ቀጥሎ በትምህርታቸውም ቀልድ እንዳያውቁ አድርጋ ነው እያነፀቻቸው ያለችው።

የቤት ስራቸውን ከጨረሱ በኋላ የተለያዩ ጨዋታዎችን በመጫወት ጊዜውን ማሳለፍ ጀመሩ።

ፍቅራቸው በጣም ያስቀናል። ሀዩ እነሱን ለማሳቅ ፣ ለማዝናናት የምታደርጋቸው ነገሮች ለነሱ ያላት ፍቅር ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ አንዱ ማሳያ ነው። ሀዩ ለነሱ እንጂ ለራሷ እንደማትኖር በአንድ ቀን ያያት ሰው ራሱ መገመት ይችላል።

ከዙሁር ሰላት በኋላ 8 ሰአት አከባቢ ሀዩ አልይንና መርየምን አስተኝታ ከፈቲያ ጋር ቁጭ ብላ እየተጨዋወተች ባለችበት ሰአት የቤታቸው የግቢ በር ተንኳኳ። ሀዩም በሩን ለመክፈት ተነስታ ወጣች። የግቢው በር ጋር ደርሳ ከውስጥ ወደውጪ በሚያሳይ ትንሽዬ ቀዳዳ የሰውዬውን ማንነት ለማወቅ አጮለቀች።

ሀሰን ነበር በሩን እያንኳኳ ያለው። ሀሰን ማለት ትምህርት ቤት እያለች እንደወንድም ትቀርበው የነበረ ልጅ ነው። ሀሰን በጣም ዝምተኛና ከሰዎች ጋር ብዙ የማይቀራረብ አይነት ልጅ ነው። ከሀዩ ጋርም አንድ ጊዜ አማርኛ መምህራቸው በሰጣቸው የቡድን ስራ ምክንያት ነው መግባባት የቻሉት። ሀሰን አይደለም እንደዛሬ ሴት ቤት ሊመጣ ቀርቶ ሴት እንኳን ቀና ብሎ ለማየት በጣም የሚያፍር ልጅ ነበር።

ዛሬ ግን ሀዩን ፍለጋ ቤቷ መጥቷል። ምናልባት ከትምህርት ቤት መቅረቷ አሳስቦት ይሆናል። ሀዩ ልክ ስታየው በጣም ደነገጠች። ከተማሪዎች ጋር መገናኘት አትፈልግም። ደሞ እንደወንድም የምትቀርበው ሀሰን የሷ መቅረት አስጨንቆት እፍረቱን ለሷ ሰውቶ ሊጠይቃት በመምጣቱ አሳዘናት። ልክፈት ወይስ አልከፈት በሚል ሁለት አሳብ ውስጥ ገብታ መታገል ጀመረች።

#ክፍል_ሶስት..⓷.....ይቀጥላል....