Get Mystery Box with random crypto!

​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗ .' ከራስ ሽሽት '. | የካምፓስ ህይወት_MAHIR

​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


.#ክፍል_ሶስት...( ⓷ )
┗•━•━•━ ◎ ━•━•━•┛

ሀዩ መወሰን አቅቷት ለረጅም ደቂቃ በሩ ላይ ቆማ ማሰብ ጀመረች። ሀሰን አንገቱን እንደደፋ የግቢውን በር ማንኳኳት ቀጥሏል። በውስጡ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ሲመጣ በዛው ልክ የግቢውንም በር በቀስታ ማንኳኳት ጀመረ። በመጨረሻም በሩ እንደማይከፈት ስላሰበ አንድ ደብዳቤ በበሩ ስር ከቶ ሄደ።ሀዩ ግን ያንን ደብዳቤ አላየችውም ነበር።

ሀሰን ሳያገኛት በመመለሱ በጣም ከፋው። ከቤት ሲወጣ ምን ብሎ እንደሚያናግራት ተለማምዶ ነበር የወጣው። የሀዩ ናፍቆት አላስችል ብሎት ነበር የመጣው ግን አልተሳካም።

<< ሀዩ ማን መጥቶ ነው ቆየሽ እኮ..>> አለች ፈቲያ ከቤት እየወጣች።
<< አይ መጣው ፈቲ ግቢ መጣው...>>

ሀሰን መሄዱን ካረጋገጠች በኋላ ወደቤት ገባች። ሀሰንን ማግኘት ፈልጋ የነበረ ቢሆንም ለሚጠይቃት ጥያቄ ግን በቂ ምላሽ እንደማታገኝ ስላወቀች ጨከነችበት።

እንደተከዘች ወደሳሎን ሄዳ ቁጭ አለች። ፈቲ ትንሽ አሟት ስለነበር ለመተኛት ወደመኝታ ስትሄድ ሁዩም ባለችበት ቁጭ ብላ የድሮ ትውስታዎቿን ታውጠነጥን ጀመር።

የመጀመሪያ ቀን ከሀሰን ጋር የተግባቡት አማርኛ የቡድን ስራ ተሰቷቸው እሷና ሀሰን እንዲሁም ሌሎች ልጆች በጋራ ሲሰሩ ነበር። ታድያ ያኔ ሀሰን በጣም አስቸግሯት ነበር። እያስረዳች እንደገባቸው ለማረጋገጥ ሁሉንም በተራ ስትጠይቅ ሀሰን ግን አንገቱን ደፍቶ ቁጭ ከማለት ውጪ ምንም መልስ አይሰጣትም። ያኔ በጣም ተናዳበት << ግሩፕ ውስጥ ምንም እየሰራ አይደለም ብዬ ነው ለመምህሩ የምነግረው >> ብላ ስታስፈራራው ነበር ለምኖ ያስተዋትና ስለራሱ በደንብ የነገራት።

ሀሰን ሌሎች ሴቶችን ቀና ብሎ የማያይ ልጅ ያኔ ለሷ ስለህይወቱ መናገሩ ለራሱም ጥያቄ ሆኖበት ነበር። በዛ ተዋውቀው ጥሩ የእህትና ወንድም ትስስር ፈጠሩ። ሀዩ በትንሹም ቢሆን ከሰዎች ጋር እንዲግባባ አደረገችው።

ስለሀሰን መቼም የማትረሳው ነገር ሌሎች ወንዶች ሊያዋሩአት ፈልገው እሷ ጋር ሲመጡ << አስተማሪ እየጠራሽ ነው >> እያለ ከልጆቹ የሚለያት ነገር ነው። ሀሳቡ እውነት ይመስል ፈገግ አለች።



ሀሰን ቤት ከገባ በኋላ ምንም አርፎ መቀመጥ አልቻለም። ትምህርት ቤት አትመጣም፣ ስልክ አይደውልላት ነገር ስልኳ የለውም። እሷን የማግኛ የመጨረሻ እድሉ ቤቷ መሄድ ነበር እሱም አልተሳካም።

<< ቆይ ለምንድን ነው የምትናፍቀኝ? ከመች ጀምሮ ነው እኔ ስለሴት ማሰብ የጀመርኩት? ጭራሽ የሴት ቤት እስከመሄድ ድረስ? ፍቅር ማለት ይሄ ነው እንዴ? ወድጃት ነው እንዴ? >> እራሱን በጥያቆዎች ማፋጠጥ ጀመረ።

እሱም በተራው የመኝታ ክፍሉ አልጋ ላይ ጋደም ብሎ ከሷ ጋር የነበረውን የማይረሳ ትውስታ በማሰብ በሀሳብ ጭልጥ አለ።
አንድ ጊዜ ትምህርት ቤት ውስጥ ሀዩ ተደብቃ ስትሰግድ ሀሰን ያያታል። የትምህርት ቤቱ ባለቤቶች ሙስሊም ስላልነበሩ እዛ መስገድን አይፈቅዱም። እሱ ብዙ ጊዜ ብቻውን መሆን ስለሚፈልግ አንድ ባዶ ክፍል ለመቀመጥ ሲሄድ ነበር ክፍል ውስጥ ጥግ ላይ ስትሰግድ ያያት።

ለሀይማኖቷ ያላት ጥንካሬ ፣ ድፍረቷ ፣ ጀግንነቷ ቀልቡ ውስጥ የገባው ከዛ ቀን ጀምሮ ነው። ሀዩ ለሱ ከሌሎች ሴቶች ትለይበታለች። ታድያ ምንም ያህል ወዷት ቢሆን እንኳን ያንን ጊዜ ሁሉ ፍቅሩን አልገለፀላትም ነበር። 2 አመት ሙሉ በናፍቆቷ ሲቃጠል ፣ ከዛሬ ነገ ትመጣለች እያለ ሲጠብቅ እሷ ግን የውሀ ሽታ ሆና ቀረችበት። እስካሁንም ልቡን ለሷ ዘግቶ እሷን እየጠበቃት ነው።



አመሻሹ ላይ የነሀዩ አባት ወደቤት መጣ። ለሱ በሩን ለመክፈት ልትሄድ ስትል አልይ ቀድሟት እሮጦ ከፈተለት። ልክ አባቷ እግሩን ወደግቢው ሲያስገባ ነበር ደብዳቤውን መሬት ላይ ያየችው። ቅድም ሀሰን መጥቶ ስለነበር ከሱ እንደሆነ ለማወቅ ጊዜ አልፈጀባትም።

በጣም ደነገጠች! አባቷ እግሩ ያለው ደብዳቤው ጋር ነው። ጎንበስ ካለ ማየቱ የማይቀር ነው። አየው ማለት ደሞ ለሀዩ ጥሩ አይመጣም። ልቧ በሀይለኛው መምታት ጀመረ!
<< ያረቢ ደብዳቤውን እንዳያየው አይኑን ሸፍንልኝ ! >> እያለች በልቧ ዱዓ ማድረግ ጀመረች።
ቅድም እንዴት እንዳላየችው ግራ ገብቷታል። ብቻ ግን አባቷ ይሄን ሰሞን አሪፍ ሁኔታ ላይ ስለሌለ ደብዳቤው ምንም ይሁን ምንም ከወንድ እንደተላከ ካወቀ ሁዩን እንዲው አይተዋትም።
አባቷ የግቢውን በር አልፎ ወደውስጥ ገባ....

ክፍልአራት..⓸ ይቀጥላል....
┍──━──━──┙◆┕──━──━──