Get Mystery Box with random crypto!

​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗ .' ከራስ ሽሽት '. | የካምፓስ ህይወት_MAHIR

​​​​╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
." ከራስ ሽሽት ".
. ( ሶፊያ አህመድ )

╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

. በ @tibebislam_nw የቀረበ
. ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.━─━────༺༻────━─━


ክፍልአራት...(⓸)
∴━━━✿━━━∴

የሀዩ የልብ ምት በጣም ጨመረ! ካሁን አሁን አየው እያለች መረጋጋት አቃታት። አባቷ በሩን በውስጥ በኩል ከቆለፈ በኋላ ወደቤት ገባ።
<< ኡፍ አልሀምዱሊላህ >> አለች በልቧ። እሱ እንደገባ እየሮጠች ሄዳ ደብዳቤውን አነሳችው።

አሁን ለማንበብ ስለማይመቻት ማታ ልተኛ ስትል ለማንበብ ወስኗ የልብሷ ኪስ ውስጥ ከታው ወደቤት ገባች።

የተኙትን ቀስቅሳ ሁሉንም ከሰበሰበች በኋላ እራት አበላቻቸው። ከነሱ ጋር ቁጭ ብትልም ልቧ ግን እዛ ደብዳቤው ላይ ነው ያለው።በልተው ከጨረሱ በኋላ እቃዎችን አስገባባች። አባቷ ለመተኛት ሲገባ እሷም ወንድምና እህቶቿን ይዛ ወደክፍል ገባች። በዛ ያረጀ ፍራሽ ላይ ሁሉም ጎናቸውን ለማሳረፍ ጋደም አሉ።

<< ዛሬስ የማንን ታሪክ ነው የምትነግሪን?? >> አለ አልይ ሁሌ ሊተኙ ሲሉ የምታውቀውን የነብያቶች ወይም የሰሀባዎችን ታሪክ ስለምትነግራቸው ለመስማት ጓጉቶ።

<< ኢንሻአላህ ዛሬ ታሪክ ሳይሆን የምነግራችሁ ከዚ በፊት ስለነገርኳችሁ ታሪኮች ጥያቄና መልስ ነው የሚኖረን...>> አለች አቀማመጧን እያስተካከለች።
ሁሉም ዝግጁ መሆናቸውን ካረጋገጠች በኋላ ተራ በተራ መጠየቅ ጀመረች...

ሀዩ፡ << ነብያችን ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ የት ተወለዱ? >>

አልይ፡ << መካ >>

ሀዩ፡ << ነብያችን ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ < ምላስ ላይ ቀላል አላህ ጋር ግን ሚዛን ደፊ የሆነ ዚክር > ያሉት ቃል ምንድን ነው? >>

መርየም፡ << ሱብሀነላህ ወቢሀምዲሂ ሱብሀን አላህ አልአዚም >>

ሀዩ፡ << 4ቱ ትልልቅ ኪታቦች እነማን ናቸው? የወረዱትስ ለማን ነበር? >>
ፈቲ፡ << 1) ዘቡር ለዳውድ (ዐ.ሰ)
2) ተውራት ለሙሳ (ዐ.ሰ)
3) ኢንጂል ለኢሳ ( ዐ.ሰ)
4) ቁርዓን ለነብዬ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ)

ሀዩ አንዳንድ ጊዜ ከጠየቀቻቸው በኋላ ልቧ የቅድሙን ደብዳቤ ለማንበብ ስለተንጠለጠለ እንዲተኙ አደረገቻቸው።

ሁሉም እንቅልፍ እንደወሰዳቸው ስታረጋግጥ ደብዳቤውን አውጥታ ማንበብ ጀመረች።

<< አሰላም አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ... ሰላም ነሽ ሀዩ... ስለናፈቅሽኝ ነበር ላገኝሽ የመጣውት...አንቺም ከናፈኩሽ በዚ ደውዪልኝ...>> ብሎ ከስር ስልክ ቁጥር አስቀምጧል።

ሀዩ አንብባው እንደጨረሰች በጣም ሳቀች። እሷ የጠበቀችው እንደዚ አልነበረም። ለነገሩ ልጁ እኮ ሀሰን ነው። ደብዳቤውን መላኩ ራሱ ለሱ ትልቅ ነገር ነው።

እሷም ሀሰን ናፍቋት እንደነበር የገባት ግን አሁን ነው። ስለሱ ስታስብ ፈገግ ማለት ታበዛለች። አሁንም ሁለት ሀሳብ ውስጥ ገብታ ከራሷ ጋር መከራከር ጀመረች። መደወል ወይም አለመደወል...

<< ደውዪለት ሀዩ...ሀሰን እኮ ወንድምሽ ነው... ይሄ ሁላ ጊዜ ሳታገኚው አልናፈቀሽም? ደሞ አንቺን ብሎ መጥቶ ...ደውዪና አግኚው ሀዩ..>>

<< ከዛስ ደውለሽለትስ? ልታወሩ? ከዛስ አውራቹ? ከዛ ያላቹ ግንኙነት ወደየት ሊሄድ ነው? አንቺ አሁን ከወንድ ጋር የምትጃጃዪበት ጊዜ አይደለም.. ትምህርት እንኳን ያቆምሽው ለነሱ ብለሽ ነው.. አሁንም ከነሱ ውጪ ምንም ነገር ማሰብ የለብሽም! >>

ውስጧ ለሁለት የተከፈለ ያህል በተቃራኒ ሀሳቦች መሟገቱን ቀጠለ...ሀዩ የምትወስነው ነገር ግራ ገባት። ብታገኘው ደስ እንደሚላት ብታውቅም እሱን ማግኘቷ ግን አሁን ካለችበት መንገድ እንዳያሰናክላትም ፈርታለች

በዚ ጊዜ ፍቅር ፣ ትዳር ለሀዩ ትርጉም የለውም። ሁሉ ነገሮቿ ወንድምና እህቶቿ ናቸው። ለነሱ ስትል የራሷን ህይወት ሰውታለች።
ከረጅም ሰአት ክርክር በኋላ አንዱን ለማድረግ ወሰነች።

#ክፍል\አምስት..⓹...ይቀጥላል
❯────────────