Get Mystery Box with random crypto!

የዳዕዋ ጎዳና

የቴሌግራም ቻናል አርማ ye_daewa_godana — የዳዕዋ ጎዳና
የቴሌግራም ቻናል አርማ ye_daewa_godana — የዳዕዋ ጎዳና
የሰርጥ አድራሻ: @ye_daewa_godana
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 747
የሰርጥ መግለጫ

በቻልኩት አቅም ቁርአኖችን፣ የሶሀቦችን ታሪኮች፣ ሐዲሶችን፣ አስለቃሽ ምክሮችን እንዲሁም በአላህ ፈቃድ የጋብቻ ፕሮግራም .... የምለቅበት ቻናል ነው።
ዱንያየንም አሂራየንም አላህ እንዲያሳምርልኝ ዱአ አርጉልኝ።
የምትልኩትን የጋብቻ መረጃ በውስጥ መስመር ብቻ ነው የምታደርሱኝ። በዚህ 👇

owner👉 @albarselan

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 14:22:21 " አለች ሀጅራ አሁንም እየሳቀች።
.
በልተን እንደጨረስን የገብሬ ጀልባ ላይ ወጥተን ሀይቁ ላይ መንሳፈፍ ጀመርን። "ይኸዉ አባይ ጣናን ሲጋልበዉ!" አለ ገብሬ ጣናን ንጣፍ አድርጎ ከላይ የሚሄደዉን የአባይን ዉሀ እየጠቆመን።
ተፈጥሮ ይገርማል ፣ አባይ በጣና ላይ ምንም ከጣና ጋር ሳይቀላቀል ያልፋል።
በነገራችን ላይ ዛሬ ጣና ላይ መንሸራሸሩን ያቀድነዉ በዋነኛነት ከሀጅራ ጋር ስንብት እንዲሆነን በማሰብ ነዉ። እሷ የኮምቦልቻ ልጅ ስለሆነች ክረምቱን አናገኛትም። እኛ እንኳን የሸገር ልጆች ስለሆንን ከፈለግን እዛዉ መገናኘት እንችላለን።
"አኩ ጉማሬ! ጉማሬ! አለች ሀያት ከጀልባችን አቅራቢያ የሚዋኘዉን ዳለቻ ፍጥረት እያሳየችኝ።
ራሄል የጀልባዉ ወንበር ላይ በጉልበቷ ተንበርክካ ከሀይቁ ዉሀ በእጇ እየዘገነች ትረጨን ጀመር። ሁላችንም የጣናን ዉሀ ተረጫጨነዉ። ራሄል ገብሬን ሳይቀር አበሰበሰችዉ።
ጣና ላይ እስኪሰለቸን ከተሽከረከርን በኋላ "በሉ ወደ ደሴቷ እንመለስ ይመሽብናል።" አለ ገብሬ ጀልባዋን እያዞረ። ስንመለስ ሰዓቱ ለአስራ ሁለት ስለተጠጋ ንፋሱ ዉሀዉን ያንቀሳቅሰዉ ነበር። አንዴ በናጠን ቁጥር እነሀዩ ሲጮሁ እርስ በእርስ ሲያያዙ እኔና ገብሬ እንስቃለን።
.
ከጀልባዉ እንደወረድን ገብሬን ሞቅ ባለ ክፍያ አስደሰትነዉ። የሚሰራ ሰዉ ገንዘብ ሲያገኝ ደስ ይላል። ለአጭበርባሪ ለማኝ ገንዘብ ከመስጠት ለገብሬ አይነቱ እጥፍ መክፈል እርካታ ይሰጣል። ስንቱን ቀዳዳ እንደሚሸፍንበት ገብሬ ነዉ የሚያዉቀዉ።
.
ማታ ግቢ በር ጋር እራት እየበላን ቀጣዩን ቀን የምናስፈርማቸዉን ነገሮች ጨራርሰን ጁምዓ(አርብ) ወደየቤታችን ለመሄድ ወሰንን።
ቆይ አሁን እንዴት ነዉ ከሀያት እና ከራሄል ጋር ወደ ሸገር የምመለሰዉ? ሀያት ገና የሄድን ቀን ኺጥባ(ለጋብቻ በተጫጩ ጥንዶች መካከል የሚካሄድ ዉይይት) ካልጀመርን ማለቷ አይቀርም።
ቆይ ራሄልስ ምን አስባ ነዉ እንደዛ በርግጠኝነት የራሷ እንደምታደርገኝ የዛተችዉ? እናያለና!
.
ይቀጥላል...

.
65 viewsĺëñã , 11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:22:20 መንታ መንገድ
ክፍል አራት
(ፉአድ ሙና)
.
.
ሰሞኑ የፈተና ስለሆነ ዉሏችን እና አዳራችን ላይብረሪ ሆኗል። ሀያት በቃሌ መሰረት ድጋሚ ስለፍቅር ጥያቄዋ አንስታ አታዉቅም። ፈተና እስክንጨርስ እየጠበቀች ይመስለኛል።
.
ረቡዕ ዕለት ፈተና ጨረስን። ከከሰዓት ያለዉን ጊዜ ከነሀጁ ጋር ጣና ላይ ልናሳልፈዉ ቀድመን አቅደን ነበር።
ምሳ በልተን ዘጠኝ ሰዓት ሲል ወደ ጣና ሄድን።
ከፔዳ ኮንትራት ከያዝናት ባጃጅ ጊዮርጊስ ጋር ወርደን ወደ ሀይቁ ወረድን። ሰዓቱን ስናየዉ የአስር ሰላት (አስር ሰዓት አካባቢ የሚሰገደዉ ስግደት) ሰዓት ደርሷል። ጀልባ ላይ ከመዉጣታችን በፊት ለመስገድ አሰብን። ኪሴ ዉስጥ ተጣጣፊ መስገጃ ይዤ ነበር። መስገጃዋን እየተቀባበልን ሶስታችንም ሰገድን። ሰግደን ስንጨርስ ራሄል የጀልባ ደምበኛችን ገብሬ ጋር ደወለች። ከጣና ድባቦች አንዱ የማይረሳዉ የጀልባ ባለቤቶች የሰዉ ሽሚያ ነዉ። አንዱ ቀድሞ ከያዘህ ሌላዉ አይቀናቀነዉም። ህጋቸዉ ነዉ! ታዲያ ለመቅደም ሽሚያዉ ለጉድ ነዉ። ገብሬ ወዲያዉ ሲከንፍ መጣ። ሁሌም ጣና ላይ መንሳፈፍ ሲያሰኘን የገብሬን ጀልባ ተኮናትረን መንሳፈፉን እንመርጣለን። ሙድ ያለዉ ሰዉ ነዉ።
ጀልባዋ ላይ እንደወጣን ገብሬ "ወዴት ላስፈንጥራት?" አለ።
ራሄል "ሀጁ ዛሬ ደብረማርያም ገዳም ያለዉን ቅጠል ካላየሁ ብላለች መጀመሪያ ወደዛ እንሂድ!" አለችዉ።
"ኣሀ የሰዉነገርን?" አለ ገብሬ ወደ ሀጅራ እየዞረ። የሰዉ ነገር የሚባለዉ ቅጠል በእጅ ሲነካ ኩምሽሽ የሚልና ቀለሙን የሚቀይር ቅጠል ነዉ።
"አዎ ገብሬ" አለችዉ ሀጅራ። ገብሬ ወደ ደብረማርያም ገዳም መቅዘፍ ጀመረ።
.
ሀይቁ ላይ ብዙ ጀልባዎች አሉ። ብዙዎቹ ሀይቁ ላይ የሚዝናኑት ጥንዶች ናቸዉ። የፈጣሪ ነገር ገረመኝ። ዉሀ ላይ እየታመፀ ዝም ይላል። ዉሀ ላይ ስትሆን ከፈጣሪህ ሌላ ምንም ተገን የለህም። ጀልባዉ ከመንሳፈፉ እኩል የመስመጥም እድል አለዉ። የሚንሳፈፈዉ በፈጣሪ ይሁንታ ብቻ ነዉ።
ከአጠገባችን አንዲት ጀልባ ተጠጋችን። የጀልባዉ ጫፍ ላይ ጥንዶች ቆመዉ ይሳሳማሉ። ታይታኒክ ፊልም መርከብ ላይ እንጂ ጀልባ ላይ እንዳልተሰራ ማን በነገራቸዉ! የጀልባዉ ቀዛፊ ጀልባዋ ሚዛን እያጣችበት ስለሆነ ወደ መሀል እንዲመለሱ እየጮኸ ይነግራቸዋል። ብቻቸዉን ኮንትራት ስለያዙት እነሱ ወደ አንድ አቅጣጫ ሲያዘነብሉ ጀልባዋ ሚዛን ማጣቷ አይቀርም። እንደዉም ጀልባዉ የሞተር ጀልባ ስለሆነ ነዉ እንጂ እስከአሁንም ሊሰጥም ይችል ነበር። ጥንዶቹ ወደ መሀል ተመልሰዉ ልፊያቸዉን ቀጠሉ። ዛሬ በጌታዬ ታጋሽነት በጣም እርግጠኛ ሆንኩ። የሰዉ ልጅ ግን ደፋር ነዉ እንዴት ዉሀ ላይ ሆኖ የፈጣሪን ህግ ይዳፈራል? እኔ ራሱ ሀይማኖቴ እንዲህ ሚስቴ መሆን ከሚችሉ ሴቶች ጋር እንድገለል አይፈቅድልኝም። ግን ፈጣሪም በትዕግስቱ አለፈን። ቅጣቱን ለመች አቆይቶት ይሆን? ዘንጊ እንኳን አይደለም!
.
ደብረማርያም ገዳም እንደደረስን ገብሬ "አደራ ከአስር ደቂቃ በላይ እንዳትቆዩ!" አለ።
"ኧረ ገብሬ አሳ እንበላለን እኮ ሀያ ደቂቃ አድርገዉ!" አለች ሀያት የራሄልን እጅ ይዛ ከጀልባዉ እየወረደች።
በነገራችን ላይ ደብረማርያም ገዳም ጋር ያሉት አሳ ቤቶች አሳቸዉ ትኩስ ስለሆነ በጣም ይጣፍጣል።
ሀጅራ እና ሀያት የሰዉነገር የሚባለዉን ቅጠል ለማየት ወደ ገዳሙ ሲገቡ እኔና ሪቾ አሳ አዝዘን ለመጠበቅ የገዳሙ በር አካባቢ ያለዉ የሰሌን ቤት ዉስጥ ገባን።
የቤቱ ባለቤት ወዲያዉ ብቅ ብላ "ራሄሌ" ብላ ራሄልን ከሳመች በኋላ "አንተ የማትጨበጠዉ ነህ አይደል?" አለች እየሳቀች።
"አዎ አራት አሳ አምጪልን!" አልኳት አባባሏ እያሳቀኝ።
"አሀ ሙስሊሞቹ ልጆችስ?" አለች እነሀጅራን ማለቷ ነዉ።
"ገዳም ሊጎበኙ ገብተዉ ነዉ። ይመጣሉ።" አለቻት ራሄል። ጣና ከመጣን እዚህ ቤት መጥተን አሳ ሳንበላ አንመለስም። ለዛ ነዉ ልጅቷ በደንብ የምታዉቀን። ልጅቷ አሳዉን ለማዘጋጀት ወደ ዉስጥ ገባች።
.
ቤቱ ዉስጥ እኔናራሄል ብቻ ነዉ ያለነዉ።
"አክረሜ የማታዉን ልጅ እኮ አገኘሁት!" አለችኝ ራሄል እጆቿን ጉልበቷ መካከል ከትታ ፤ አይኗን ጣራዉ ላይ እያንከራተተች።
"የቱን ልጅ?" አልኳት ግራ እየተጋባሁ።
"እንደዉም አንድ ቀን ማታ ለብቻችን ተገናኝተን ግጥም ያነበብኩልህ ጊዜ ለማን ነዉ የፃፍሽዉ? ሙስሊም ይመስላል ምናምን አላልክም ነበር?" አለችኝ። ወዲያዉ ትዝ አለኝ። እንደዉም ፌስቡክ ላይ ራሱ አገኘሁት ብላ ፅፋልኝ ነበር። የሀያት የፍቅር ጥያቄ አስረስቶኝ አልጠየቅኳትም እንጂ!!
"እኔ እኮ የኛ ክፍል ልጅ መስሎኝ ነበር። ምንድነዉ የሚያጠናዉ?" አልኳት አይኗን ተከትዬ እኔም ጣራዉን እያየሁ።
ራሄል አይኖቿን ወደኔ እየመለሰች "ኧረ የኛዉ ክፍል ልጅ ነዉ!" አለችኝ።
"አልተሳሳትኩማ! ኡስማኔ ነዉ አይደል። ድሮም ጭቅጭቃችሁ የፍቅር መሆኑ ያስባንን ነበር!" አልኩ ላሳምናት አይኖቿ ላይ አፍጥጬ
"ቲሽ አዉቀህ ሞተሀል። ባክህ አይደለም።" አለችኝ።
"ሪድዋን?"
"አይደለም ባክህ የማይናገር የማይጋገር ልጅ ትጠራለህ እንዴ?" አለች እየበሸቀችብኝ።
"ሌላ ሙስሊም ልጅ እኛ ክፍል የለም እኮ!" አልኳት ሲጀመርም ክፍል ዉስጥ ያለነዉ ወንዶች ከአስር አንበልጥም።
ራሄል ወደኔ እየተጠጋች "አክረሜ ለምን እንዳልገባህ ትሆናለህ? በጣም ሰዉ ማስጨነቅ ትወዳለህ! አፈቅርሀለሁ! ይኸዉ በቃላት ነዉ እንድነግርህ የምትፈልገዉ! ይኸዉ እወድሀለሁ!" አለችና በረዥሙ ተነፈሰች።
ክዉ ብዬ ቀረሁ። ያኔ ያነበበችልኝ ግጥም አሁን በደንብ ገባኝ።
"አንተ ሌት ስግደት ላይ ፣ ሰማይ ስትጠራ፣" የሚለዉ ስንኝ ትዝ አለኝ። ራሄል ወደ ንጋት አስራ አንድ ሰዓት አካባቢ ፌስቡክ ላይ አትጠፋም። እኔ የፈጅር(ንጋት) ስግደት ሰግጄ ፌስቡክ ላይ ስገባ ሁሌም "ፀለይክልኝ?" ትለኝ ነበር።
ራሄል ዝም ስል "ምነዉ መናገር አልነበረብኝም?" አለች እንባዋ አይኗን እየሞላ
ራሄል በጣም ቆንጆ ናት ደግሞ በሁኔታዋ የሆነ ሰዉነትን የመቆጣጠር ሀይል አላት።
"ኧረ እንኳንም ነገርሽኝ" አልኩ አይኗን የሞላዉ እንባ እንዳይፈስ በልቤ እየፀለይኩ
"ምን አይነት ስሜት አለህ ለኔ? ማለቴ ትወደኛለህ?" አለችኝ ሰዉነቷን ወደኔ ሙሉ ለሙሉ እያዞረች!
እዉነት ለመናገር ራሄል በጣም ደስ ትለኛለች። እብድነቷ ፣ አነጋገሯ ፣ በዛ ላይ ደግሞ ግጥም ትፅፋለች።
ግን ደግሞ በዚህ በኩል ሀያት የሌላ ስሆን ከምታይ ሞቷን ትመርጣለች። ራሄል የሀያት ስሆን ካየች ደግሞ ጓደኝነታችን ሊበጠበጥ ነዉ።እኔ በመሀል እንደ ድፎ ዳቦ ልለበለብ ነዉ። ራሄል ልትስመኝ ከንፈሯን ወደ ከንፈሬ አስጠጋች ፣ነዘረኝ። አቀረቀርኩ። ብስማት አልጠላም ፣ ግን የሀይማኖቴ "ያላገባሀትን ሴት አትንካ" የሚል ክልከላ አለ።
"ገባኝ! እንደዚህ አይነት ነገር ዉስጥ ከጋብቻ በፊት መግባት አትፈልግም።" አለችና ፊቷን ከኔ እየመለሰች "ግን አንተን የኔ ከማድረግ ሀይማኖትም ይሁን ምንም አያግደኝም!" አለች። ዉስጧ ላይ እልህ አለ። እልኋ ዉስጥ ፍቅር አለ። ሁሉ ነገሯ ዉስጥ ደሞ ዉበት አለ። ወደድኳት እንዴ? አላዉቅም።
.
ሀያት እና ሀጅራ የሰዉነገርን ጎብኝተዉ ተመለሱ።
"ደብሬ መጥተዋል አቅርቢልን" አለች ራሄል ምንም ያልተፈጠረ ለማስመሰል እየሞከረች።
ደብሬ ስምንት ትናንሽ አሳዎችን በሳህን በሳህን ሁለት ሁለት አድርጋ ከዳቦ ጋር አቀረበችልን።
አሳዎቹ እንደቀረቡ ሀዩ አንዱን የኔን አሳ አንስታ እሾሁን ታወጣልኝ ጀመረች። ራሄል ተከትላት የሌላኛዉን አሳዬን እሾህ ማዉጣት ጀመረች። ሀጅራ እያየቻቸዉ ትስቃለች።
"ኧረ መስተንግዶ አበዛችሁበት ይብላበት እንጂ!
48 viewsĺëñã , 11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:22:19 ሱት!" አለች።
ሁሉም ተስማሙ። በርግጥ ርዕሱ ከግጥሙ ጋር የሚገናኝ አይደለም። የስሟን አማርኛ ትርጉም ነበር ለግጥሜ መጠሪያ የሰጠችዉ። ይህቺ ልጅ ፎንቃዋን ግልፅ እያደረገችዉ ነዉ።
.
ከሻይ ቤቱ ወጥተን ወደ ግቢ ገብተን ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ላይብረሪ ጋር ስንደርስ ሀጅራ "ወይኔ በአላህ ብር ከኤቲኤም አወጣለሁ ብዬ ረሳሁት።" አለች። ላይብረሪዉ በር ላይ እንድንጠብቃቸዉ ነግረዉን ከራሄል ጋር ግቢ በር ጋር ወዳለዉ ኤቲኤም ሄዱ።
እኔና ሀያት ብቻ ቀረን። ሀዩ አቀርቅራ "አክረሜ ኺጥባዉን ለመጀመር አሰብክ ወይስ?" አለችና ሂጃቧን ማስተካከል ጀመረች።
ኺጥባ ማለት አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ለማግባት ሲፈልግ በወንዱና በሴቷ መካከል በእስልምና ሀይማኖት አስተምህሮ የተፈቀደ ዉይይት ነዉ። አንዳንድ ለሌላ ወንድ ማየት የማይፈቀዱ የሰዉነት ክፍሎችን እስከማሳየት ይዘልቃል። ፀጉር ፣ አንገት ምናምን! ከዴቲንግ ጋር የሚለያየዉ ቤተሰብ ባለበት የሚደረግ በመሆኑና ንክኪዎች ክልክል በመሆናቸዉ ነዉ።
ሳቄን ለመቆጣጠር እየሞከርኩ "ሀዩዬ ኺጥባ ባስብ እንኳ እኮ እናትሽ ባሉበት እሱንም ቤታችሁ ዉስጥ ነዉ እንጂ እዚህ ባህርዳር ዉስጥ ማንም በሌለበት ማድረግ ለዝሙት በር መበርገድ ነዉ።" አልኳት።
"እሱ ችግር የለዉም። የዚህ አመት ትምህርት ሊያልቅ ፈተና ብቻ ነዉ የሚቀረን። ክረምት ላይ እኛ ቤት ኡሚ ባለችበት ልናደርገዉ እንችላለን። አሁን ወሳኙ ያንተ ፈቃደኝነት ብቻ ነዉ።" አለችኝ።
በጣም ጨነቀኝ። ልገፋት አልፈለግኩም።
"ሀዩ ቢያንስ ፈተና እስከምንጨርስ ስለዚህ ጉዳይ ባንጨነቅ ፕሊስ? ኤግዛም እንዳለቀ ብናወራበት ይሻላል። ትዳር ዝም ተብሎ አይመሰረትም እኮ ተረጋግተን ክረምት ላይ እናዉራ! አይመስልሽም?" አልኳት።
ሀያት ምራቋን ዋጥ እያደረገች "አክረሜ ግን የሌላ ሰዉ ሆነህ ካየሁ ሰዉ አልሆንም!" አለችኝ።
ምናባቴ ነዉ የሚሻለኝ በአላህ? እኔ ቤተሰቦቼ ዘወትር ሲባሉ ስለመኖር እንጂ ስለልጃቸዉ የወደፊት ህይወት ትዝ የሚላቸዉ አይነት አይደሉም። ላግባት ብልስ ማነዉ በወጉ የሚድረኝ? በርግጥ አባቴ ሊያቋቁመኝ ይችላል። ግን ዋናዉ ጥያቄ እኔ እሷን ለማግባት እወዳታለሁ ወይ? ማለቴ ሳያት ደስ ትለኛለች? እሱማ በደንብ ነዉ እንጂ!
እና? እናማ ትንሽ ልረጋጋ! ዉስጤ ሌላ ምርጫ ያለዉ ይመስል እየወላወለ ነዉ።
.
ይቀጥላል...
.
.
44 viewsĺëñã , 11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:22:18 መንታ መንገድ
ክፍል ሶስት
(ፉአድ ሙና)
.
.
ዶርም እንደገባሁ አልጋዬ ላይ ተዘርሬ ሀያት አስቀምጬልሀለሁ ያለችኝን መልዕክት ለማንበብ ፌስቡክ ሚሴንጀሬን ከፈትኩ።
ሁለት መልዕክት አለኝ። አንዱ ከራሄል ነዉ። "አኩሻ የምወደዉን ልጅ እኮ ዛሬ አገኘሁት። ማታ እንገናኝና አሳይሀለሁ።" ይላል። መልስ ሳልፅፍ የሀያትን መልዕክት ከፈትኩት።
.
የሀያት መልዕክት ረዥም ነበር። ቀደም ብላ አዘጋጅታዉ አብረን የነበርን ጊዜ ኮፒ ፔስት አድርጋ እንደላከችልኝ ገባኝ።
"አክረሜ ጥቁር ሂጃብ የምትለብስ ሴት እንደምትወድ ከነገርከኝ በኋላ ከጥቁር ሂጃብ ዉጪ ለብሼ አላዉቅም። ሴት እንደማትጨብጥ ካየሁ በኋላ ወንድ ጨብጬ አላዉቅም። ሰዉነቴ ላይ የተጣበቀ ቀሚስ ለብሼ ከተቆጣኸኝ ወዲህ ቅርፄን የሚያሳይ ልብስ በፍፁም አለበስኩም። ሀይማኖትህ ላይ ያለህን ከፊል ጥንካሬ በጣም አደንቅልሀለሁ። ሁሌም እንደወንድም ስትመክረን እና ስትቆጣን በጣም ነበር ደስ የሚለኝ። ግን አኩዬ በነዚህ ሁሉ ወንድማዊ ቅርበቶችህ ምክንያት ልቤ ዉስጥ ካንተ ሌላ መድሀኒት ያጣሁለት ህመም ተፈጥሯል። ወድጄሀለሁ!!
በርግጥ ለወራት አፍኜዉ የነበረዉን ፍቅሬን ዛሬ ያለምክንያት አልነገርኩህም። ትናንት ማታ ከራሄል ጋር ለብቻችሁ እንዳመሻችሁ ሳዉቅ እንዳልቀደም በጣም ፈራሁ። የፈጣሪን ትዕዛዝ እጋፋለሁ ብለህ አትፍራ! እኔ ፈቃደኛ ከሆንክ ካንተ ጋር ዛሬ ኒካህ ለማሰር ፈቃደኛ ነኝ። አፈቅርሀለሁ!!" ይላል።
ኒካህ ማሰር ማለት በኢስላማዊ ስነ ስርዓት መጋባት ማለት ነዉ።
.
ሀያት ስለኔ እንደዚህ አይነት ምልከታ ይኖራታል ብዬ ገምቼ አላዉቅም። እኔ በፍፁም ከወንድምነት በዘለለ በሌላ እይታ ማናቸዉንም አላየሁም ነበር። ቆይ ሀዩ ምን አይነት ልጅ ነበረች? ቀይ ሁሌም ፈገግታ ከፊቷ ሳቅ ከንግግሯ መሀል የማይጠፋ ቆንጆ ልጅ ናት። ስትስቅ የሆነ ሁሉ ነገርህን የመቆጣጠር ሀይል አላት። ለምን እንደሳቀች ሳታዉቅ በሳቋ ሀይል ብቻ አብረሀት ትስቃለህ። ትንሽ ኩራት ተሰማኝ። በሀያት መፈቀር ደስ ይላል። ኤርሚያስ እና ዮናስ ወደዋት ቁም ስቅላቸዉን ሲያዩ ዞርም ብላ አላየቻቸዉም ነበር። ለካ መፈቀር በጣም ያኮራል። ያዉ በዚህ ዘመን አንበሳ መግደል ህገ ወጥ አደን ስለተባለ ፣ ጦርነትም ስለሌለ ማንንም ገድለን መኩራት አንችልምና ሴቶች አፈቀርናችሁ ሲሉን የአንበሳ መግደሉንም የመዝመቱንም አንድ ላይ ደርበን እንኮራለን።
.
ምን ልበላት? የሀያትን ጓደኝነት ማጣት አልፈልግም። ደግሞ አሁን ላይ ከማንም ጋር ኒካህ ለማሰር ዝግጁ አይደለሁም። ግራ ገባኝ። ኦ ሀዩ ምንድነዉ ያደረግሽዉ? ባትነግሪኝ ነበር የሚሻለዉ።
የፍቅር ጥያቄዋን አልቀበልም ካልኩ ጓደኝነታችን ሊጎዳ ነዉ። እሺ ካልኩ ደግሞ ሳልዘጋጅ ኒካህ ላስር ነዉ። ኒካህ ሳናስር ፎንቃ ፎንቃ እንጫወት ካልን ደሞ ዝሙት ላይ ልንወድቅ ነዉ። ሀዩ ምን አይነት አጣብቂኝ ዉስጥ ነዉ የከተተችኝ? ቢሆንም ጓደኝነታችንም ሳይጎዳ ፣የፍቅር ጥያቄዋንም ሳልቀበል ሀዩን አረጋግቼ ማቆየት ይኖርብኛል።
የሰዉን ልብ ከሰበርክ መልሶ መግጠሙ በጣም ከባድ ነዉ። አብረህ ስትሆን በመልካም እንደሆነዉ ሁሉ ስትለያይም በመልካም መሆን አለበት። አሁን የማደርጋቸዉ ነገሮች ሀያትን መካከለኛዉ የጓደኝነት ሜዳ ላይ ለማቆየት ወሳኝ ናቸዉ። ከሀያት ጋር በጓደኝነት ከተለያየን ግን ከሀጅራ እና ራሄል ጋር ያለንም ጓደኝነት ይበላሻል። ብቻዬን መቅረቴ ነዉ።
ከስልኬ ላይ አክሱም ሄደን የነበረ ጊዜ የተነሳነዉን ፎቶ አዉጥቼ ተመለከትኩት። መለያየት የለብንም አልኩ በልቤ። በነገራችን ላይ የምንማረዉ ትምህርት ከኢትዮጵያ የቱሪዝም መስህቦች ጋር የተያያዘ ስለሆነ ወደ ተለያዩ ክፍለ ሀገራት ጉዞ እናደርጋለን። የመጀመሪያ አመት ተማሪ ስለሆንን የሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል በደንብ ጎብኝተናል።
.
የምሳ ሰዓት ሲደርስ ራሄል ደወለችልኝ። አነሳሁት
"ኧ ሰዉየዉ ለምሳ እየወጣን ነዉ። የት ነህ?" አለች ራሄል።
"ዶርም ነኝ በቃ መጣሁ እዘዙ!" አልኳት ከአልጋዬ ላይ እየተነሳሁ።
"ዛሬ ሀጅራም ከኛ ጋር ነዉ የምትበላዉ ምን እንዘዝ?" አለችኝ።
"አሪፍ ያላችሁትን እዘዙ!" ብዬ ስልኩን ዘግቼ ከግቢ ዉጪ ወዳለዉ ምግብ ቤት ሄድኩ።
.
ወደ ምግብ ቤቱ ስደርስ ሀያት እና ራሄል እየተከራከሩ ነዉ።
"የፔዳ በር ተገልብጦ ነዉ የተሰራዉ! ከዉስጥ ወደ ዉጪ ስትወጪ እየገባሽ እኮ ነዉ የሚመስለዉ!" ትላለች ራሄል
"ታዲያ ለምን የዘበኞቹ ቤት ከዉስጥ በኩል በሩ ላይ ተሰራ?" ትላለች ሀያት
ሀጅራ ዝም ብላ ታያቸዋለች።
እጄን ታጥቤ ስቀመጥ "አቦ አድቡ በቃ በማያከራክር አትከራከሩ!" አለች ሀጅራ።
ሀያት መምጣቴን ስታይ በሀፍረት አንገቷን አቀረቀረች። ምንም ያልተፈጠረ በማስመሰል ሀፍረቷን ዛሬ ካልገደልኩት ነገ እኔ ያለሁበት መምጣት ታፍራለች።
"ሀዩ ግን እንደ ኢንጂነሪንግ ተማሪ ስለበሩ አሰራር ስትከራከሩ አይደብራችሁም? ምን አገባችሁ?" አልኩ እየሳቅኩ። ሀያትን ከሀፍረቷ ለመገላገል ብዬ እንጂ ስለበሩ ማዉራት ፈልጌ አልነበረም።
ካቀረቀረችበት ቀና እያለች "ይሄ እኮ የትልቅ ዩኒቨርሲቲ በር ነዉ። ዛሬ ተራ በር ቢሆንም ሲቆይ ቅርስ መሆኑ አይቀርም። ስለዚህ ይመለከተናል!" አለችና ፈገግ ለማለት ሞከረች።
ራሄል እጇን ለሀያት እየዘረጋች "ቴክ ፋይቭ ካንቺ ጋር ቱሪዝም በማጥናቴ ኩራት ይሰማኛል!" ብላ እየሳቀች ምላሷን አወጣችብኝ።
.
ምግቡ ቀርቦ ከበላን በኋላ ሁሌም ምግብ እንደበላን ሻይ ለመጠጣት ወደምንሄድበት ሻይ ቤት ሄድን። ይሄ ቤት ግቢያችን በር ላይ ካሉት ሌሎች ቤቶች በጣም ይለያል። ዉስጥ ሲገባ መሬቱ ሙሉ ለሙሉ ጠጠር የለበሰ ነዉ።ጠጠሮቹን እያነሱ መጫወት ይቻላል። እንደወንበርነት የሚያገለግሉት ከቤቱ ጠርዝ ላይ ዙሪያዉን ተደርድረዉ የተለሰኑት ቦለኬቶች ናቸዉ። እንደ ጠረጴዛ ደግሞ የእንጀራ ምጣድ በሚያምር መልኩ ተሰናድቷል። ምጣዶቹ ላይ አንድ ሁለት መፅሀፍ ይቀመጣል። እንግዲህ ይሄን ቤት ለየት የሚያደርገዉ የባህላዊነት ስሜት ስላለዉ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ባልተለመደ መልኩ መፅሀፍ በመኖሩ ነዉ።
.
ወደ ሻይ ቤቱ ገብተን አራት ሻይ ካዘዝን በኋላ ሀጅራ "አቦ ራሄል እና አክረሜ ምነዉ ፈዘዛችሁ ግጥም አንብቡልን እንጂ! እኛ መች ሻዩ አማረን" አለች።
እዉነቷን ነዉ እዚህ ቤት የምንመጣዉ አብረን አሪፍ ጊዜ ለማሳለፍ በሚል ነዉ እንጂ ሻይ የመጠጣት ፍቅሩ ኖሮን አይደለም።
"ሪቾ ቀጥይ" አልኩ ለመዳመጥ እራሴን እያመቻቸሁ። ትናንት ማታ ያነበበችልኝን ግጥም አነበበችዉ። ሀያት ፊቷ ተቀያየረ። ግራ ገባኝ። ዉጥረቱን ለማርገብ በቃሌ የያዝኳትን የራሴን አንድ ግጥም ለማንበብ ስዘጋጅ ሀያት ፈገግ ብላ ትኩረቷን ሙሉ ወደኔ አደረገች። ፈገግ አልኩላትና ማነብነብ ጀመርኩ።
"ደራሽ ፍቅርሽ መሀል፣ ፈራሽ ቤት ገንብቼ፣
ሙሉ አንቺነትሽ ዉስጥ ፣ ግማሽ እኔን ይዤ፣
ሙሉ የሆንኩ መስሎኝ ፣ ሁሉ ጎደሎዬ ተሸፍኖ ባንቺ፣
አልፈልግሽም ስል አምነሽኝ ብትሄጂ፣
ፈገግታዬ የለም ፣ ሳቄን የት ወሰድሽዉ?
ኩራቴ ከሰመ ፣ ልቤን የት አኖርሽዉ?
ዛሬ ትንሽ ሳስብ ፣ ቆሜ ለብቻዬ፣
የመሳቄ ሚስጥር ፣ የኩራት ካዝናዬ ፣
አንቺ ነሽ ገብቶኛል ፣ ተመለሽ በአምላክሽ፣
ከእቅፌ አልለይሽም እንኳን ላስቀይምሽ፣
እንኳን በቃኝ ልልሽ!
ተመለሽ በፍቅርሽ! ነይልኝ ልካስሽ።" ብዬ ስጨርስ ሶስቱም አጨበጨቡልኝ።
ራሄል ፈገግ ብላ "ሌላ ጊዜ አንብብልን ለማለት እንዲመቸን ርዕሱን ንገረን!" አለችኝ።
"ርዕስ እንኳ አልነበረዉም ደስ ያላችሁን አዉጡለት" አልኩ ራሄልን እያየሁ።
ሀያት ፈጠን ብላ "ህይወት ብላችሁ አስታዉ
55 viewsĺëñã , 11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:30:37 ጋታዉ ወደ ክፍል ስገባ ሀያት እና ሀጅራ ብቻ ነዉ ያሉት ራሄል የለችም። ሁለቱም ዝም ብለዉ ይተያያሉ። "ሀጁ ራሄል በሰላም ነዉ የቀረችዉ?" አልኩ ሁለቱንም እያየሁ።
"ኧረ መጥታለች ዉሀ ልትገዛ ላዉንጅ ሄዳ ነዉ።" አለች ሀጅራ።
ሀያት ዛሬ በጣም ቀዝቅዛብኛለች ፈገግታ ጠፍቶበት የማያዉቀዉ ፊቷ ዛሬ ጭር ብሏል።
"ሀዩ ችግር አለ እንዴ?" አልኳት ከአጠገቧ እየተቀመጥኩ
"አኩዬ የሆነ የማማክርህ ነገር ነበር። ምን መሰለህ፣ ቆይ ግን ቆንጆ ነኝ አይደል?" አለችኝ አይን አይኔን እያየች።
"አዎ በተለይ እንዲህ ለምቦጭሽን ስትዘረግፊዉ በጣም ታምሪያለሽ!" አልኳት እየሳቅኩ።
ፊቷ ፈካ አለ። ሀጅራ "ሪቾ ቀረች እኮ!" ብላን ተነስታ ሄደች። ሀጅራ ስትወጣ የክፍላችን ተወካይ ዮናስ ቲቸር ዛሬ እንዳልተመቻትና እንደማትመጣ ነግሮን ወጣ። ሁሉም ተማሪ ከክፍል ወጥቶ እኔና ሀያት ብቻ ቀረን።
"አክረሜ ገና እዚህ ግቢ ስንገባ ጀምሮ ጓደኛሞች ነን። አሁን አመቱ ሊያልቅ ነዉ። እና " አለችና ስልኳን አዉጥታ ከነካካች በኋላ "ፌስቡክ ላይ መልዕክት አስቀምጬልሀለሁ እየዉና እናወራለን ብላኝ ትታኝ ሄደች።
ሀዩ ዛሬ ምን ነክቷታል? በጣም ግልፅና ተጫዋች ልጅ ነበረች።
ራሄልናሀጅራ ሲመጡ ሀያት የለችም ብቻዬን ነኝ።
"ሀያትስ?" አለች ራሄል
"እኔንጃ!" አልኳቸዉ የት እንደሄደች ለኔም ግልፅ አይደለም።
ምንድነዉ እንዲህ ያበረራት ቆይ? ፌስቡክ ላይ ያስቀመጠችልኝን መልዕክት ለማየት እነ ሀጅራን ትቻቸዉ ወደ ዶርም ሄድኩ።
ዉይ ሰዉ ግን ልብ ማንጠልጠል ሲወድ! ምናለ እዛዉ ብትነግረኝ።
.
ይቀጥላል...
.
53 viewsĺëñã , 11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:30:37 መንታ መንገድ
ክፍል ሁለት
(ፉአድ ሙና)
.
.
ከዶርም ወጥቼ በቢዝነስናኢኮኖሚክስ ላይብረሪ በኩል ወደ ላቭ ስትሪት አቀናሁ። ራሄል መግቢያዉ ጋር ቆማለች። የለበሰችዉ አጭር ቀሚስ ከባቶቿ አልዘለለም። ከላይ ባለኮፍያ ሸሚዝ ለብሳለች። ሸሚዙን አልቆለፈችዉም። ከዉስጥ የለበሰችዉ ቦዲ ይታያል። በርግጥ ባህርዳር ምሽቷም ብርዳማ አይደለም። ራሄል አንድ ፒንክ ደብተር ይዛለች።
አጠገቧ እንደደረስኩ "አንተ ብዙ አስቆምከኝ እኮ!" አለች እየተሟዘዘች።
የሷ ዶርም ለላቭ ስትሪት ትንሽ ስለሚቀርብ ቀደመችኝ እንጂ እንደደወለችልኝ ነበር የወጣሁት። በላቭ ስትሪት በኩል ዎክ ማድረግ እንደጀመርን "ሪቾ እንዴት ከነሀዩ ጋር አልመጣሽም? ማለቴ እንዴት ብቻሽን?" አልኳት።
በአይኖቿ ሰረቅ አድርጋ ተመለከተችኝና "በርግጥ እነሱም ነበሩ ግን ሰሞኑን የሚሰማኝ ስሜት የተለየ ስለሆነ ነዉ ካንተ ጋር መሆን የፈለግኩት!" አለችኝ።
"ደሞ ምን ተሰማሽ መችስ ያንቺ ከራስምታት አይዘልም!" አልኩ እየሳቅኩ።
"ሂ የሆንክ ሞዛዛ .. አሁን ራስ ምታት ስሜት ነዉ? ባክህ የፍቅር ግጥሞችን መፃፍ ጀምሬ ነዉ። እና ላንተ ላነብልህ ፈልጌያለሁ። ያንተንም ግጥሞች ባዳመጥ ደስ ይለኛል።" አለችኝ ፒንኩን ደብተር እየከፈተች።
ሰዓቴን አየሁት ሶስት ሰዓት ከሩብ ይላል። እኛ ግቢ ከአራት ሰዓት በኋላ ወንድናሴት አብረዉ ግቢ ዉስጥ ከተገኙ በሜትሮዎች መታወቂያ ይቀማሉ። ሜትሮ የምንላቸዉ በሌሎች ግቢዎች የካምፓስ ፖሊስ የሚባሉትን ነዉ።
"እሺ ለአራት ሩብ ጉዳይ እስኪሆን አንብቢልኝና እንለያያለን!" አልኳት።
እዉነት ለመናገር ራሄል ዛሬ በጣም አምሮባታል። የሆነ ስሜቴን እየተፈታተነችኝ እንደሆነ እየተሰማኝ ነዉ። ሴት ልጅ ምንም ብትሆን የሆነ ከፈጣሪ የተቸራት ዉበት አለ። ሪቾ ደግሞ ሲጀመርም በጣም ቆንጆ ናት። ዛሬ ደግሞ ዉበቷ ሀይሉን ጨምሮ እየተንፎለፎለ ነዉ። እስከዛሬ ግን ለምን እንዲህ አልተመለከትኳትም? አዎ ለብቻችን ተገናኝተን አናዉቅም።
አሀ አንድ ወንድና ሴት ብቻቸዉን ከተገናኙ ሶስተኛዉ ሰይጣን ነዉ የሚባለዉ እዉነት ነዉ ማለት ነዉ።
.
"አኩ ተመለስ እንጂ!" ብላ ጣቶቿን ስታጮሀቸዉ ከገባሁበት የሀሳብ ሰመመን ወጣሁ። ሪቾ ከፊቴ መንገዱን ዘግታ ቆማለች። በጣም ቀርባኛለች። ሽቶዋ መላ ሰዉነቴን ሲወረዉ ተሰማኝ። ፈገግ አለችና "ባይተዋር" ብላ ቀና ብላ አየችኝ። የግጥሙ ርዕስ መሆኑ ነዉ። እያዳመጥኳት እንደሆነ ካረጋገጠች በኋላ ግጥሙን ማንበብ ጀመረች።
"አንተ ሌት ስግደት ላይ ፣ሰማይ ስትጠራ፣
እኔ መዝሙር ጥናት ፣ ፌሎ ልጆች ጋራ
ማሸብሸብ ማወደስ ፣ ሸብረክ ከጉልበቴ
እሱን የኔ አርግልኝ፣ የዘዉትር ፀሎቴ
አንተ የለህም እዚህ
መስጊድ ሄድክ መሰለኝ ፣ አዛን ተባለ እንዴ?
ንገረዉ ለጌታህ የኔ እንዲያደርግህ ፣ ሳይገለኝ መዉደዴ።
በመዝሙር ጥናት ዉስጥ ፣በሽብሸባዉ ሁላ ፣
ልቤን ሰርቀኸዋል ያሰብኩት ሰዉ የለም እኔ ካንተ ሌላ።
ማፍቀር አንተን ብቻ ፣ ዉድድ እንደ ጣና
ፍቅሬን ተቀበለኝ ፣ በደስታ ልታጀብ ዳግም እንደገና።"
ብላ አይኔን እያየች "በፍቅር ጎዳና!" አለች።
አጨበጨብኩላት እሷም እየሳቀች ሁለት እጆቿን ከፍ አድርጋ ተሽከረከረች። ያለንበት ቦታ ጨለማ ነዉ። እብድነቷ ምሽቱን ብርሀን አልብሶታል።
ተሽከርክራ ስትጨርስ "ሪቾ ግን ፎንቃ ገባልሽ እንዴ?" አልኳት።
"ምነዉ?" አለችኝ እየሳቀች
"የሆነ ለየት ያሉ ነገሮችን እያየሁብሽ ነዉ። የፍቅር ግጥም መፃፍ መጀመርሽ፣ ቅድም ደሞ ለየት ያለ ስሜት እየተሰማኝ ነዉ ብለሽኝ ነበር ሲቀጥል ከሀጁናሀዩ ጋር ተለይተሽ የማታዉቂዉን ዛሬ እንቅልፍ እንቢ አለኝ ብለሽ ብቻሽን አገኘሽኝ። እና ምንድነዉ ይሄ አዲሱ ፀባይ?" አልኩ አይኖቿ ዉስጥ መልስ እየፈለግኩ።
ራሄል ዙሪያዬን እየተሽከረከረች "አንተ የፍቅር ግጥም ትፅፋለህ! ግን አላፈቀርክም አይደል? ሲቀጥል ባታፈቅርም ለየት ያለ ስሜት ሊሰማህ ይችላል እኮ!" አለች።
"እንቅልፍ እንቢ ማለቱስ? ከነሀዩ ተለይቶ መምጣቱስ?" አልኳት።
"አኩሻ በቃ አታጨናንቀኝ! እኔ እኮ" ስትል ስልኬ ጠራ።
.
ራሄል ዙሪያዬን መሽከርከሯን ትታ ፊትለፊቴ እየቆመች "ማነዉ?" አለችኝ።
"ሀጅራ ናት!" አልኩ ስልኬን እያየሁ
"አክረም ፕሊስ አብረን እንደሆንን አትንገራት። ሳልነግራቸዉ ስለወጣሁ ሊደብራቸዉ ይችላል።" አለች በአይኖቿ እየተለማመጠችኝ።
ስልኩን አነሳሁት "አሰላሙአለይኩም አኩሻ አፍወን ተኝተህ ነበር እንዴ?" አለችኝ ሀጅራ እንደተለመደዉ ረጋ ብላ
"ወአለይኩሙሰላም ኧረ አልተኛሁም በሰላም ነዉ በዚህ ሰዓት?" አልኳት ስለ ራሄል ከጠየቀችኝ ለመዋሸት ራሴን እያዘጋጀሁ።
"አቦ እንደዉ ባክህ ራሄል ጠፋችብን። ሳትነግረን ወጥታ ቀረች። ስልኳን ደሞ አልያዘችዉም። አይተሀት እንደሆን ብዬ ነዉ።" አለችኝ።
የሀጅራ ሚስኪንነት መዋሸት እንዳልችል አደረገኝ። "ኧረ አብረን ነን።" አልኳት።
ራሄል ደንግጣ አፏን ይዛ ደርቃ ቀረች።
"ኡፎይ በአላህ እኔ ደሞ ምን ሆነች ብዬ በቃ ቶሎ ላካት!" አለች ሀጅራ።
ስልኩን እንደዘጋሁት "ሶሪ ሪቾ አልቻልኩም። በጣም ተጨንቀዉ ነበር።" አልኳት።
"አይ በቃ ችግር የለዉም! ስንት ደቂቃ ቀረን?" አለችኝ በፈገግታዋ ውስጥ ይቅርታዋን እንድረዳ ፍልቅልቅ እያለችልኝ።
"ሩብ ጉዳይ ሊሆን አምስት ደቂቃ ይቀረዋል።" አልኳት እንደሁሌዉ ሳቋ እየተጋባብኝ።
"እሺ እየተመለስን!" አለች ፊቷን ወደመጣንበት አቅጣጫ እያዞረች።
"ባይ ዘዌይ ስለ ግጥሙ ሳስብ ነበር። አንቺ ያዉ ሀዋርያት ነሽ። የፃፍሽለት ልጅ ደግሞ ሙስሊም መሰለኝ። እንዴት ልትፅፊዉ ቻልሽ?" አልኳት።
ቆም አለች፤ስትቆም ቆምኩኝ። በጣም ተጠጋችኝ። አተነፋፈሴ ተዘበራረቀ። አይኔን ሰበርኩት።
"አንድ ሙስሊም ቆንጆ አፍቅሬያለሁ።" አለችኝና መራመዷን ቀጠለች። ተነፈስኩ ትንሽ ቆማ ቢሆን ኖሮ እሳሳትባት ነበር።
በፍፁም ከዚህ በኋላ አንድን ሴት ብቻዋን ላላገኝ ለራሴ ቃል ገባሁ። ከሴትም ራሄልን!
"ሪቾ ማነዉ ልጁ?" አልኩ ክፍላችን ዉስጥ ያሉትን ሁለት ሙስሊም ወንዶች እያሰብኩ። ሪድዋን እና ኡስማን ይባላሉ። ራሄል ከሪድዋን ጋር ስታወራ አይቻት አላዉቅም። ከኡስማን ጋር ደሞ ሁሌም እንደተጨቃጨቁ ነዉ። ስለዚህ ኡስማን ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ።
"አሁን አልነግርህም ግን በቅርቡ ማወቅህ አይቀርም!" አለችኝ።
"ካልሽ ይሁን አላስጨንቅሽም!" አልኳት።
.
እኔ ሁሌም ሰዎች አፈቀርን ሲሉ ይገርመኛል። በፍቅር እና በስሜት መካከል ያለዉ ልዩነት አይታየኝም። አንድ ሴት አንድን ወንድ አፈቀርኩ ስትል ከሱ ጋር የስጋ ጥማቴን ማርካት ፈለግኩ እያለች እንደሆነ ነዉ የሚሰማኝ። እንጂማ ሰዉ በአይን ተያይቶ እንዴት አፈቀርኩ ይላል? እዉነተኛ ፍቅርም ሆነ ጥላቻ ያለዉ ትዳር ዉስጥ ነዉ። የአንድ ሰዉ ትክክለኛ ማንነት የሚታወቀዉ አብሮ በመኖር ነዉ። አንድ ሴት ባሏን ስታፈቅር እዉነተኛ ፍቅር ነዉ ምክንያቱም አብራዉ እየኖረች ሁሉንም ጉዱን እያወቀች ነዉና የወደደችዉ። እንጂማ አንድ ወንድ በሳምንት ሶስት ቀን ከሁለትናሶስት ሰዓት ላልበዛ ጊዜ ለሚያገኛት ፍቅረኛዉ መልዐክ መስሎ መቅረብ በፍፁም አይከብደዉም። ሴቷም በተመሳሳዩ! ለዚህም ይመስለኛል በፍቅረኛነት ከሰባት አመት በላይ የቆዩ ጥንዶች በተጋቡ በወራት ዉስጥ ባሌ በፍፁም የማላዉቀዉ ሰዉ ሆነብኝ፣ ሚስቴ እንደዚህ አይነት ሴት ነበረች እንዴ? ተባብለዉ ለፍቺ የሚዳረጉት።
.
ራሄል ልንለያይ ስንል እጇን ዘረጋችልኝ። ደነገጥኩ።
"ከመቼ ጀምሮ?" አልኳት ልትጨብጠኝ እጇን መዘርጋቷ ገርሞኝ።
"ኦ ዞሮብኛል አኩዬ ይቅርታ!" አለችኝ እጇን እየሰበሰበች።
.
በነ
39 viewsĺëñã , 11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:30:37 "ዉይ አኩሻ እናትህ እኮ የባሏ ዘመዶች ቤቷ ሲመጡ እያስቀየመቻቸዉ አሁን ማንም እናንተ ቤት ድርሽ አይልም። አባትህን የስራ ቦታዉ ሄደን ነዉ የምንዘይረዉ!" አለችኝ።
ለእናቴ ያለኝ ጥላቻ ከፍ ሲል ተሰማኝ። ኢሙን ተሰናብቼ ስልኩን ዘጋሁት እና አባቴ ጋር ደወልኩ።
ሰላም ከተባባልን በኋላ "አባ ዘመዶቻችን ቤት የማይመጡት እማዬ አስቀይማቸዉ ነዉ እንዴ?" አልኩት።
"አይ አክረሜ የሷንስ ነገር ተወዉ መላ ጠፍቶለታል። ባይሆን አንድ ምክር ልምከርህ እኔ መልኳን አይቼ አግብቼ ነዉ እንዲህ የምቃጠለዉ አንተ ስትደርስ አደራህን እምነቷ ላይ ያላትን ጥንካሬ ሳታይ ስነ ምግባሯን ሳትመዝን እንዳታገባ።" አለኝ። የእናቴ ነገር ቢያናድደኝም የአባቴ ምክር ፈገግ አስባለኝ። እኔ ለትዳር ደርሻለሁ ማለት ነዉ? አባዬ እንደትልቅ ነዉ የሚያስበኝ? ደስ ሲል።
.
ልብሴን ላወልቅ የሸሚዜን ቁልፍ ስፈታ ስልክ ተደወለልኝ። አየሁት ራሄል ናት። ምነዉ ያለመደባትን በዚህ ሰዓት?
"ኧ እብዷ ህልም እናዋጣልሽ?" አልኩ ስልኩን አንስቼ
"አንተ ያለህበት ከሆነ ደስ ይለኛል" አለች እየሳቀች።
"ምነዉ እንቅልፍ እንቢ አለሽ እንዴ?" አልኳት ሳቋ እየተጋባብኝ።
"አዎ ባክህ ካላስቸገርኩህ ብትመጣና ትንሽ አምሽተን ብንለያይ ደስ ይለኛል።" አለችኝ።
"ልተኛ ነበር በቃ እሺ መጣሁ የት እንገናኝ?" አልኳት።
"ላቭ ስትሪት እንገናኝ መግቢያዉ ጋር እጠብቅሀለሁ።" ብላኝ ስልኩን ዘጋችዉ። ላቭ ስትሪት ግቢያችን ዉስጥ ያለ ረዥም መንገድ ነዉ። መብራት ስለሌለበት እና በዛፎች የተከበበ ስለሆነ ብዙ ጥንዶች ዎክ ያደርጉበታል።
ሹራብ ለብሼ ራሄል ወደ ቀጠረችኝ ቦታ ለመሄድ ተነሳሁ።
የራሄልን እንቅልፍ ከራሄል ጋር ላቭ ስትሪት ላይ ልንጠብቀዉ።
.
ይቀጥላል...
.
.
35 viewsĺëñã , 11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:30:37 መንታ መንገድ
ክፍል አንድ
(ፉአድ ሙና)
.
.
ከልጅነቴ ጀምሮ ቤት ዉስጥ ጭቅጭቅ እያየሁ ነዉ ያደግኩት። ትንሽዬ የጦርነት ሜዳ ውስጥ! እናቴ ምላሷ አይጣል ነዉ። አባቴ ደግሞ የእናቴ ምላስ ይመስገንና ሳይደበድባት ነግቶ አይመሽም። በርግጥ አባቴ ከእናቴ ጋር ለመጋጨት የእሷ ነገረ ስራ አስገድዶት እንጂ ሳትደርስበት ደርሶባት አያዉቅም። እኔም ድብድቡን ወንበር ስር መሽጌ እየተመለከትኩ አደግኩ። ፀባቸዉ ገና ሲጀመር እንባዬ ከአይኖቼ ዱብ ዱብ እያለ ወንበር ስር ተደብቄ አያለሁ። ሁሌም ሰላም የለኝም። አንዳንዴ የእናቴ ተግባር እኔን ራሱ በጣም ያበሳጨኝ ነበር። እንግዳ በሚመጣበት ጊዜ አሊያም ከጓደኞቿ ጋር ስትሆን የአባቴን የግል ሚስጥር ሳይቀር ትለፈልፋለች። እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ እና ነገሮችን ላቅ ባለ እይታ ማገናዘብ ስጀምር የእናቴ ተግባር ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ ስለተረዳሁት የአባቴ ድብደባ ሲያንሳት ነዉ ወደሚል ድምዳሜ ደረስኩ። ምንም እናት ብትሆንም በፍፁም ለልጆቿ አርዐያ መሆን እንደማትችል ከስነ ምግባር ዝቅጠቷ ተረዳሁ። ቤት ዉስጥ ያለነዉ ሶስት ልጆች ነን። ሁለቱ እህቶቼ ናቸዉ። ታዲያ እናቴ ለእህቶቼ ስለ አባቴ መጥፎ አስተሳሰብ እንዲኖራቸዉ የሆነ ያልሆነዉን እየነገረች ቤት ዉስጥ ትርምስ መፍጠር ጀመረች። እህቶቼ የእናቴ ኮፒ ሆኑ። በዚህም ምክንያት ከቤታችን ዉስጥ ሰላም ጓዙን ጠቅልሎ ወጣ። አባቴ በእህቶቼ ሳይቀር በጣም መናቅ ጀመረ። እኔ እናቴ እያደረገች ያለችዉ ነገር ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ ላስረዳት ብሞክርም "አንተ የአባትህ ኮፒ ነህ!" እያለች ምክሬን አልቀበልም አለች። እናቴ ለአባቴ ልክ እንደ ልብስ ሆና ሚስጥሩን መሸሸግ እና ክፍተቱን መሙላት ሲገባት የሱን ስም ለማጥፋት መቅጠፍ ድረስ ሄደች። ስግደት ለሰዉ ተገቢ ስላልሆነ እንጂ እንድትሰግድለት ልትታዘዝለት የነበረችዉ ሚስት ባሏን በጣም መናቅና ዉሳኔዎቹን አለማክበር ጀመረች። የትዳር መሰረት ተናጋ! ህፃናት ልጆች በእናትና በአባት መካከል ጣልቃ ሲገቡ የትዳር መሰረት መናጋቱ የማይቀር ነዉ። እኔ ግን የሚገርመኝ የአባቴ ትዕግስት ነዉ። ለምን አይፈታትም? እኔ ብሆን የሱን ያህል የምታገስ አይመስለኝም።
.
እድሜዬ ከፍ ብሎ የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ስሆን ቤት መግባት የሚባል ነገር አስጠላኝ። ጠዋት ከቤት የወጣሁ ማታ አራት ሰዓት ወደ ቤት ብመለስ ነዉ። ማታ ወደ ቤት ስመለስ ልክ ወደ መገደያዉ ስፍራ እንደሚወሰድ እስረኛ እየቀፈፈኝ ነዉ። ወደ ቤት ላለመመለስ ስል ቀኑን በተቻለኝ መጠን ራሴን በተለያዩ ነገሮች ቢዚ በማድረግ አሳልፋለሁ። ከቤተሰቤ ያጣሁትን ፍቅር ፍለጋ የተለያዩ ሀይማኖታዊ ክበቦች ላይ እንዲሁም የኪነ ጥበብ ማህበሮች ላይ መሳተፍ ጀመርኩ። ብዙዎቹ ጓደኞቼ ቤታቸዉ ዉስጥ ያላቸዉ ሰላም እና የቤተሰብ ፍቅር ምን ያህል ትልቅ ፀጋ እንደሆነ አይረዱትም። እኔን በተለያዩ ክበቦች ላይ በንቃት ተሳታፊ እንደሆንኩ ሲመለከቱ በጥንካሬዬ ይገረማሉ። እኔ ከቤቴ ያጣሁትን ፍቅር እና ሰላም ፍለጋ እነዚህ ክበቦች ዉስጥ መመሸጌን አያዉቁም።
ቤተሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነዉ። መልካም ባልሆነ ቤተሰብ ዉስጥ ያደገ ልጅ መጥፎ ቢሆን አይገርምም።
ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ የምሳተፍባቸዉ ሀይማኖታዊም ሆኑ የኪነ ጥበብ ቡድኖች ለጊዜዉ ያለሁበትን ጭንቀት ከማስረሳት በዘለለ ግላዊ ፍላጎቴን ማርካት እንዳልቻሉ ተገነዘብኩ። እያንዳንዱን ጉዳዬን የማማክረዉ ሰዉ ሊኖር ይገባል። በሰዓቱ የነበርኩበት የእድሜ ደረጃ እንደተራ ሰዉ ፍቅረኛ መያዝ የሚል አማራጭን ቢያቀርብልኝም ከሴት ጋር ያን ያህል ቀረቤታ ስላልነበረኝ ከወንድ ጓደኞቼ ጋር ያለኝን ትስስር ለማጠናከር ወሰንኩ። በሰርግ ምክንያት ከተዋወቅኩት አንድ ጓደኛዬ ጋር የወንድም ያህል ተቀራረብን ሚስጥሬን ሁሉ የማካፍለዉ ለሱ ሆነ። ጭንቄንም ቢሆን ከፈጣሪዬ ጋር በግንባሬ ተደፍቼ ከመከርኩበት በኋላ ከሱ ጋር እወያይበታለሁ። ጓደኛዬ ሰዒድ ይባላል። እሱን ከተዋወቅኩ በኋላ ትንሽ ጭንቀቱም ቀለል አለልኝ። ከጎንህ የሚያማክርህ አንድ ታማኝ ወንድም እንደማግኘት የሚያስደስት ነገር የለም።
.
እድሜዬ አስራዘጠኝ ሲሆን ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፓስ ተመድቤ ቱሪዝም እና ሆቴል ማኔጅመንት ማጥናት ጀመርኩ። ባህር ዳር በጣም ዉብ ከተማ ነች። መንገዶቿ በአረንጓዴ ልማት ያጌጡ እና ፅዱ ናቸዉ። ኑሮ ከሸገር ጋር ሲነፃፀር በጣም ርካሽ ነዉ። አየሯ ከአዲስ አበባ ጋር ሲወዳደር ትንሽ ሙቀታማ ከተማ ናት። የጣና ሀይቅ አይን አይቶ የማይጠግበዉ ... ብቻ ምንልበላችሁ በጣም ብዙ ዉበቶች በአንድነት የሰፈሩባት ለምለም ምድር ናት።
የተመደብኩበት ፔዳ ካምፓስ ደግሞ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ካሉት ካምፓሶች ትልቁ ካምፓስ ነዉ። የተፈጥሮ ሳይንስናየማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች ይሰጡበታል። ግቢዉ ዉስጥ ብዙ ካምፓሶች አሉ። ግቢዉም እንደ ከተማዋ አረንጓዴ ነዉ። የፔዳ ካምፓስ እንደኔ ሰላም ከሌለዉ ቤተሰብ ለመጣ ሰዉ ትልቅ ሰላም ያለዉ ቦታ ነዉ። ትምህርት ተጀምሮ ጥቂት እንደተማርን ከክፍል ተማሪዎች ጋር መግባባት ጀመርን። ትንሽ ቆንጆ ነገር ነኝ በዚህ ምክንያት ወንዶቹ "አክረም ቺኳ" እያሉ ይጠሩኛል። ሲጀመርም የትምህርት ዘርፋችን አምሮ መታየት እንደ መስፈርት የሚታይበት ነበርና የሴቶቹ አለባበስ እና አኳኋን ቀልብ የሚያስት ነበር። ከአለባበስ ጀምሮ እስከ ፀጉር ስታይል ሁሉም ራሳቸዉን መኳል ስራቸዉ ነዉ። ወንድ ሆኖ እኛ ክፍል ዉስጥ መማር የማይፈልግ ያለ አይመስለኝም። ወንዶች ትንሽ ስለሆንን በሴቶቹ ተከበን ነዉ የምንማረዉ። ብዙዎች የኛን የትምህርት ዘርፍ የሴቶች ነዉ ይሉታል። ከአዲስ አበባ ከ500 በላይ ኪሎ ሜትሮችን ርቄያለሁ በዚህ ሰዓት ቤተሰብ አጠገቤ የለም። ፈጣሪዬን ካልፈራሁና ለራሴ ክብር ከሌለኝ የፈለግኩትን ማድረግ እችላለሁ። ጓደኛዬ ሰዒድ ከአዲስ አበባ ሆኖ አሁንም በስልክ ያማክረኛል።
ሀያት ፣ ሀጅራ እና ራሄል የቅርብ ጓደኞቼ ሆኑ። በዩኒቨርሲቲ ካገኘኋቸዉ ልጆች በሳል ብዬ የቀረብኳቸዉ እነሱን ነዉ። ከእህቶቼ ጋር መልካም ቅርርብ ስላልነበረኝ የእህትነት ፍቅርን ከነሱ ለማግኘት ብዬ በደንብ ቀረብኳቸዉ። ሀጅራ ረጋ ያለችና ምክር የምታበዛ ጠይም የኮምቦልቻ ልጅ ናት። ሀያት ሲፈጥራትም ሳቂ ብሎ የፈጠራት ይመስል ከፊቷ ላይ ፈገግታ ከንግግሯ መሀል ሳቅ የማይጠፋ የሸገር ቆንጆ ናት። ራሄልን በቅፅል ስሟ ፋሽንሾዉ ብለዉ ይጠሯታል። ሁሌም የምትለብሳቸዉ ልብሶች ድግስ የምትሄድ ኮረዳ እንጂ ለሌክቸር የምትሄድ ተማሪ ልብስ አይመስሉም። በጣም ቆንጆ ከመሆኗ የተነሳ ብዙዎቹ የክፍል ልጆች ስለሷ ሳያወሩ ስብስባቸዉ አይበተንም። እሷም እንደኔዉ የሸገር ልጅ ናት።
.
የፍሬሽማን ሙድ እየለቀቀን ግቢዉንም እየተላመድን ስንመጣ በመካከላችን ያለዉም ትስስር በጣም እየጠነከረ መጣ። ራሄል እና ሀያት ምግብ ከኔ ጋር ካልሆነ አይበሉም። ሀጅራ ካፌ ተጠቃሚ ስለሆነች የምግብ ሰዓት ላይ አንገናኝም። እኔ ፣ሀዩ እና ሪቾ ከግቢያችን በር ላይ ካሉት ምግብ ቤቶች ኮንትራት ይዘን እንመገባለን። የግቢያችን በር አራት ሰዓት ሲሆን ስለሚዘጋ በጊዜ ወደ ግቢ ገብተን በተለምዶ ሜንላዉንጅ የሚባለዉ ቦታ ላይ ትኩስ ነገር እየጠጣን ስንጨዋወት እናመሻለን። ብዙ ጊዜ የዶርም ጓደኞቼም ይቀላቀሉናል።
.
ሀሙስ ማታ ከነሀያት ጋር ተለያይተን ወደ ዶርም እንደገባሁ የአክስቴ ልጅ ደወለች። ከእህቶቼ በላይ በጣም ነዉ የምወዳት። ኢማን ትባላለች። ብዙ ከተጨዋወትን በኋላ
"ኢሙ እንዴት ነዉ እነማማን ዘይራችኋቸዉ ታዉቃላችሁ?" አልኳት።
ኢሙ ትንሽ ዝም ካለች በኋላ
54 viewsĺëñã , 11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:35:13 ግርዶ ተፈጽሟል እንዴት ነበር በሌላ ታሪክ እንድንመጣ የእናንተ የማበረታቻ ላይክ ያስፈልገናል
163 views#_Miftah, 16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 17:08:12 ግርዶ
የመጨረሻው ክፍል
ክፍል አስራሁለት
(ፉአድ ሙና)
.
<<ከሁለት ዓመት በኋላ!>>
መካኒሳ የሚገኘው የነዩሱፍ ቤት ውስጥ አንድ ህፃን የዩስራ መኝታ ክፍል ውስጥ ድክ ድክ እያለ ይራመዳል። ዩስራ "አሚሾ ቡቡቡቡቡ" እያለች ህፃኑን ለማጫወት ትሞክራለች። ቀኑ ቅዳሜ ነው። ዘቢባ መስገጃዋን እያጠፈች "አጫውተሽ ሞተሻል። ይኼኔ በውስጡ ምኗ ሞኝ ናት እያለ እየፎገረሽ ነው" አለቻት።
"ነይ ውሰጂልኝ አሁን ላንብብበት ሰኞ ፈተና አለኝ!" ዩስራ ማጫወቱ ስራ ሆኖባታል።
ዩስራ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ትምህርት ቤት የሁለተኛ ዓመት ትምህርቷን እየተከታተለች ነው።
ዘቢባ ልጇን አስተኝታ ተመለሰችና "ስሚ ደግሞ ይኼ የምትወጂው ቆርቆሮ አዲስ ጩኸት ለቀቀ እኮ!" አለች። ዘቢባ ዩስራ አሁንም ነሺዳ እንደምትወድ ስለምታስብ እያጣጣለች ልታበሽቃት ትሞክራለች።
"ተይው ባክሽ!" ዩስራ ችላ አለቻት።
"ኧረ ምነው ሲያገባ ደበረሽ እንዴ? የላጤ ነሺዳ ካልሆነ አትሰሚም?"
ኢስማኢል ካገባ ስድስት ወር ገደማ እንደሚሆነው ዩስራ ታውቃለች። አገባ ሲባል ገርሟት ነበር። ምናልባት ራሱን በአንድ ሊቆጥብ ከሆነ ትልቅ ለውጥ ነው ብላ አድንቃለት ነበር። በውስጧ ግን አሁንም በጋብቻው ላይ ሸፍጥ የሚሰራ እየመሰላት ትጠረጥረዋለች። ላለፉት ሁለት አመታት ለኢስማኢል ከመፀለይ የቦዘነችበት ቀን የለም። ወንጀሉን ተረድቶ ከጥፋት እጁን እንዲሰበስብ ፈጣሪ ልብ ይሰጠው ዘንድ ተማፅናለች።
ዘቢባ ዩስራ ዝም ስትላት "ለማንኛውም ዩሱፌን ማታ የነሺዳውን ሲዲ ገዝተህ ና ብዬዋለሁ። እኔ ስመጣ ልገዛ ብዬ ረሳሁ።" ብላ ወጣች።
ዛሬ ሰሚር እና ኹሉድ እራት ተጠርተዋል። እነዩሱፍ በየወሩ እንዲህ ያለ ዝግጅት እያሰናዱ ትስስራቸውን ለማጥበቅ እየሞከሩ ነው።
አመሻሹን ዩሱፍ ወደ ቤት ሲመለስ መስጂድ በር ላይ ካለች አንድ ትንሽዬ የመፅሀፍት እና የሲዲ መሸጫ የኢስማኢልን አዲሱን የነሺዳ አልበም ገዛ። አርዕስቱ "የፀፀት እንባዎች" ይላል።
ምሽቱን ወ/ሮ ጀሚላ እና ዘቢባ ባዘጋጇቸው በርካታ ምግቦች ሰሚር እና ኹሉድን ሊያስተናግዱ ሱፍራውን በአይነት በአይነቱ ሞሉት። ዩስራ ፈተና ስላለባት በጥናት ተወጥራ በምግብ ዝግጅቱ አልተሳተፈችም።
ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ሲል ዩሱፍ ሰሚርና ኹሉድን ይዟቸው መጣ። በቤታቸው መካከል ያለው ርቀት ብዙም ባይሆንም ሌላ የትራንስፖርት አማራጭ ስለሌለ እንዳይቸገሩ በማሰብ ነበር ቀድሞ ሄዶ ያመጣቸው።
ኹሉድ የአንድ አመት እንደሷ ውብ የሆነች ሴት ልጇን እያጫወተች ለመዓዱ ቀረቡ። ዩስራ ምግብ መቅረቡን ሰራተኛቸው ሰሚራ ሹክ ስትላት ወደ ሳሎን ሄዳ ተቀላቀለቻቸው።
"እ ሆዶ ለምግብ ሲሆን ጥናቱ ይቋረጣል አይደል?" ዘቢባ ዩስራ ገና ከመምጣትዋ አሾፈችባት።
ዩሱፍ ዩስራን ሲያይ የገዛው የነሺዳ አልበም ትዝ እያለው "ፀፀት ምናምን የሚል ሲዲ አለ ክፈችው እስኪ!" አላት። ዩስራ ሲዲውን ማጫወቻው ውስጥ ስትከተው የኢስማኢል ውብ ድምፅ መስረቅረቅ ጀመረ። ሰሚር የነሺዳው መጀመሪያ ላይ የሰማው ድምፅ እየገረመው "ቆይ ኣኣኣ ኡኡኡ ምናምን ካላሉ ነሺዳውን አይጀምሩም እንዴ? አሁንስ ቢስሚላህ አስመሰሉት እኮ!" አለ። ከዩስራ በስተቀር ሁሉም ሳቁ።
ዩስራ የነሺዳውን ግጥም ስትሰማ ማንባት ጀመረች።
"አነባለሁ ፣ ጨንቋት ነፍሴ፣
ሰላም አጣሁ ፣ በመርከሴ።
ፈተና ነው ፣ ብለህ ነግረህ የፈተንከኝ፣
ስወድቅበት ፣ ስዘቅጥበት ያልታወቀኝ፣
ተደራርቦ ሰማይ ነካ፣
ለጥፋቴ እሳት ቦካ።
ሊጋገር ነው ከገላዬ፣ የእሳት ማማ፣
የኔ ኑሮ ፣ ከትዕዛዝህ አልተስማማ።
ምስኪኑን ነፍስ ፣ ከአዘቅት ጣልኩት፣
ያመነኝን ከመንገድህ አሳሳትኩት።
ባንተው ሹመት ፣ አመፅኩበት፣
እልፍ ጨዋን ፣ ጨቆንኩበት።
አነባለሁ ፣ ጨንቋት ነፍሴ፣
ሰላም አጣሁ ፣ በመርከሴ።
ከክብራቸው ሲናጠቡ ፣ በኔ አለንጋ፣
ውብ ቀናቸው ሲጨላልም ፣ ልቤን ወጋ።
ከውጉ ስር ከፈሰሰ ፣ ጥቂት ኩራት፣
የእኔነቴን ትንሽነት ፣ አየሁባት።
ምናለ አልኩኝ
ባልገረፈ አለንጋዬ ፣ ያንን ገላ፣
ለትዕዛዝህ የወደቀን ፣ ባላጉላላ።
በሹመትህ ባልቀበጠ ፣ ያንተን ክብር ባስተዋለ፣
የያዝከውን ቀን ፣ የሚያድነው እንደሌለ።
ምን ነበረ? ምን ተሻለ?
ያቆሰልኩት ፣ ያደማሁት ብዙ አለ።
አነባለሁ ፣ ጨንቋት ነፍሴ፣
ሰላም አጣሁ ፣ በመርከሴ።
ይቀርታ ነው የምለምን ፣ ከተጎዱ፣
ካንተ ሽተው ፣ እኔን መማር ከወደዱ።
ይቅር ካሉኝ ፣ ከነፃሁኝ ከሰው እዳ፣
በእዝነት ወንዝህ እጠብ ነፍሴን ፣ ውስጤ ይፅዳ።
እንባ በዛ ተመለጠ ሽፋሽፍቴ፣
በሹመትህ ፣ በመቅጣቴ፣
አነባለሁ ፣ ጨንቋት ነፍሴ፣
ሰላም አጣሁ ፣ በመርከሴ።
ፈተና ነው ፣ ብለህ ነግረህ የፈተንከኝ፣
ስወድቅበት ፣ ስዘቅጥበት ያልታወቀኝ፣
ተደራርቦ ሰማይ ነካ፣
ለጥፋቴ እሳት ቦካ።"
ዩስራ ያደረገችው ፀሎት መስመሩ ደስ አሰኛት። ፈጣሪዋን አመሰገነች። ዘቢባ የዩስራን ማንባት ተመልክታ "ሰው በቁርዓን ያለቅሳል አንቺ በነሺዳ! አላህ ይሁንሽ!" አለች። ዩስራ ነቆራዋ ስለገባት ፈገግ ብላ አለፈቻት።
እራት ተበልቶ እንደተጠናቀቀ ዩስራ ወደ መኝታ ክፍሏ ሄዳ ኢስማኢል ጋር ደወለች።
"ዩስራ!" ኢስማኢል ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ ተቀበላት።
"ነሺዳህን ሰማሁት! አሁን የእውነት የተፀፀትክ ይመስላል!"
"አዎን እጅግ ፀፅቶኛል። እባክሽ ይቅር በይኝ?"
"እኔ ይቅር ካልኩህ ቆይቻለሁ። አላህ ይቅር ይበልህ!"
"በጣም አመሰግናለሁ ዩስራ!"
ተሰነባብተው ስልኩ ተዘጋ። የሱን ነውር የሸፈነው ፈጣሪዋ የሷንም ጉድ እንዲሸፍነው በልቧ ለመነች።
የእራት ስነ ስርዓቱ ተጠናቆ ዘቢባ እና ዩሱፍ እንግዳዎቻቸውን ቤታቸው ለማድረስ ተነሱ። ዩሱፍ እየነዳ ዘቢባ እና ኹሉድ ከኋላ ገብተው ሰሚር ጋቢና ተቀምጧል። የነዩሱፍ ሰፈርን ቅያስ ወጥተው ወደ ኮንደሚኒየሙ መግቢያ ጋር ሊደርሱ ሲሉ አንድ የተቀዳደደ ልብስ የለበሰና ፀጉሩ የተንጨባረረ ጎረምሳ ከራሱ ጋር እየጮኸ ሲያወራ ተመለከቱት። ሁሴን ነበር። ድግምቱ ከከሸፈ በኋላ ወደ እሱ ዞሮበት አብዷል። ሰሚር ሁሴንን እያየ "ድግምት ወደ ደጋሚው ዞረ ማለት ይሄ ነው እንግዲህ!" አለና "አላህ ይዘንለት!" አለ። ሁሴን ካበደ አንድ አመት ገደማ ሆኖታል። ንብረቱ ሁሉ በሰራተኞቹ ተበልቶ ከስሯል። "ኹሉዴ አለች እሷ እኮ የምድር አምላክ ነች ..." ሁሴን ብቻውን ይቀባጥራል። መኪናው ሁሴንን አልፎ ወደ ኮንደሚኒየሙ መግቢያ በር ፈሰሰ። ሰሚር እና ኹሉድን ብሎካቸው ጋር አድርሰው ዘቢባናዩሱፍ ተመለሱ።
ኹሉድ እና ሰሚር የሚወዱትን የአልጋ ላይ ትግላቸውን ለመከወን በአይናቸው ተግባብተው ወደ ቤታቸው ተቻኮሉ። የታቀፈችው ህፃን ችኮላቸው የገባት ይመስል "ኣኣሀሀይይ" ብላ አሽሟጠጠች።
ዩሱፍ እና ዘቢባ ቤት ሲደርሱ ዩስራ ግጥም እየሞነጨረች ነበር። አንድ ቀን ከነማንነቷ ተቀብሎ የሚያገባት ሰው እንደሚመጣ በፈጣሪዋ እርግጠኛ ናት።
የፃፈችውን ግጥም ትኩር ብላ አየችው።
"የሰበረኝ መዶሽ ፣ ባንተ ከታቀበ፣
ክፉው የጥፋት እጅ ፣ ከተሰበሰበ፣
ስብራቴ እንዲድን ፣ እንዲሽር ህመሜ፣
መዶሹን ባቀብከው ፣ ይጠገናል ቅስሜ።
ወዲህ በል ግጣሜን ፣ ልሰካ ከጎኑ፣
ይፈወስ ህመሜ ፣ ላመስግን አንተኑ።
ልፈወስ ነው መሰል ፣ ተረጋጋ ልቤ፣
ማንን ነው የላከው ፣ ልጠብቅ ተውቤ።" ግጥሙ አልጥም ሲላት ቀደደችው። "አንድ ቀን ለኔ የመረጥከው ሰው ያገባኛል! ያ አንድ ቀን እስኪደርስ በትዕግስት እጠብቃለሁ!" ለራሷ ተናገረች። ውስጧ አዳመጣት መሰል ፈገግ አለች።
***
ተፈፀመ!
151 viewsĺëñã , 14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ