Get Mystery Box with random crypto!

ስልጣን አደጋም ጭምር ነው .. በአንድ ወቅት የአብዱል-መሊክ ኢብኑ መርዋን ሳንቲም በአንድ ጉድጓድ | የሕያ ኢብኑ ኑህ - Yahya Ibnu Nuhe

ስልጣን አደጋም ጭምር ነው
..
በአንድ ወቅት የአብዱል-መሊክ ኢብኑ መርዋን ሳንቲም በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀ። ከጉድጓዱ ውስጥ የወደቀውን 1 ሳንቲም ለማውጣት ለአንድ ሰው 13 ሳንቲም ከፈለ። ሰዎች በተግባሩ ግራ ተጋብተው ሲጠይቁትም “የአላህ ስም በላዩ ላይ ተጽፏል” ሲል መለሳላቸው።
..
❝አል-ቢዲያህ ወ-ኒሃያህ”፣ 12/377❞
..
አብዱልመሊክ ህይወቱ ሁለት ምዕራፎች ነበሩት። የመጀመሪያ ምዕራፍ በጣም አሏህን ፈሪና ዓሊም የነበረበት ዘመን ሲሆን ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ ስልጣን ከያዘ በኃላ በጭቆና የሚታወቅበት ምዕራፍ ነው። ስልጣን ክፉ ነው፤ መነሻ ምዕራፍህን ሳይቀር ይቀይረዋል።
..
አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን..!
---------------------
T.me/Yahya5