Get Mystery Box with random crypto!

ያ አላህ ማረን ቱዩብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ya_allah_maran — ያ አላህ ማረን ቱዩብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ya_allah_maran — ያ አላህ ማረን ቱዩብ
የሰርጥ አድራሻ: @ya_allah_maran
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.71K
የሰርጥ መግለጫ

የyou Tube ቻናላችንን Subscribe ያርጉ👇
https://m.youtube.com/channel/UCaBJnwghDup7wt0cFRWaaiw
የfacebook #page like ያርጉ
👇👇👇👇👇
http://www.facebook.com/yaAllahmarantube
የቴሌግራም. Groupቻናላችን join ይበሉ
👇👇
@YAM_TUBE2
ማንኛው #Comment ካላቹ
👇
@EsmaelIbnuAhmed

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 21:30:17 ሰውዬው ሌት ተ ቀን ዒባዳ እያደረገ ከጌታው ጋር ቅርበት ለመፍጠር ይጥራል። ከእለታት አንድ ቀን በሌሊት ተነስቶ ጌታውን ሲማፀን ኢብሊስ ይመጣ ና እንዲህ ሲል ሹክ ይለዋል፦‹‹እስከመቼ ነው አላህን ስትማፀን ከርመህ አንዲትም ምላሽ እማይመጣልህ? መቼ ነው ያንተ ዱዓህ ተቀባይነት አግኝቶ ውጥንህ ሚሰምረው?››

ባርያ ቅስሙ ተሰበረ፣ ሀሞቱ ፈሰሰ፣ ሞራሉ ተነካ፣ ከአምልኮውም ተዘናግቶ በብስጭት ጥላ ስር ተጠለለ።

ከእለታት አንድ ሌሊት በእንቅልፍ ተውጦ ሳለ የህልም ተጣሪ እንዲህ ሲልም ተጣራ፦‹‹ባርያ ሆይ! ስለምን ከአምልኮ ተቋረጥክ? ስለመቋረጥህ ምክንያት ይኖርህ?! ››

ባርያውም በህልም ሰመመን እየዋለለ እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠ፦‹‹አላህ ተማፅኖዬን አልሰማህ አለኝ፤ ምናልባትም እኔ ከደጃፉ የተባረርኩ እና የተጠላሁ መስሎ ታየኝ፤ ጠፋሁም››

ተጣሪውም እንዲህ ሲል ምላሽ ይሰጠው ጀመር፦‹‹በፍፁም ከደጃፉ አልተባረርክም። አላህን ማወደስህ እና መማፅንህ አላህ ዘንድ ተፈላጊነትህን እና ቅቡልነትህን ማመላከቻ ነው። ያ ባይሆንማ ምትሻውን ሰጥቶ ከደጃፉ ባባረረህ!

አላህም እንዲህ ይልኃል "እኔ ነኝ እኮ ወደ እኔ መዋደቅን እና እኔን ማውሳትን በልብህ ያስዋብኩልህ። ወደ እኛ መዋደቅህ እና እኛን ማውሳትህ በኛ ዘንድ በፍቅር የመሳብህ ውጤት እንጂ ሌላ አይደለም።

የዝንጉዎችን ልቦችማ! ወደኛ እንዳያስቡ እና ከደጃፋችን እንዳይዋደቁ ግርጆ አድርገንባቸዋል። በችግሮቻቸውም ግዜ ከደጃፋችን መዋደቅን አንለግሳቸውም"››

ያ ረብ ከደጃፍህ አዋድቀን!
Sefwan sheik ahmedin
https://t.me/ya_Allah_maran
391 views śmîle , edited  18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:38:48 የመልካምነት ምላሽ

ሳውዲ አረቢያ
ጅዳ ኤርፖርት

ከሪም እና ሰኢድ ትውውቅ የላቸውም
ለሀጅ ጉዞ ጅዳ ኤርፖርት ነበር የተገናኙት..

ከሪም በማሌዥያ በህንፃ ተቋራጭ በኮንስትራክሽን የስራ ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን
ሰኢድ ደግሞ በኢንዶናዥያ በግል ሆስፒታል ውስጥ ፊዚዮ ቴራፒስት ሆኖ ያገለግላል

የኢስላማዊ ወንድማማችነት ጭውውት ይጀምራሉ

ከሪም ነበረ ጨወታ የጀመረው
" አላህ ወፍቆኝ ለአስረኛ ጊዜ ነው ሀጅ ዚያራ የመጣሁት "

ሰኢድ ፈገግ በማለት " ሀጅ መብሩር አላህ ይቀበልህ ወንጀልህንም ይማርህ .

አሜን ወንድሜ
.. አንተስ ስንተኛ የሀጅ ጉዞህ ነው ?

ሰኢድ መለሰ :- የመጀመሪያዬ ነው በመጨረሻዋ ሰአት የአላህ ተአምር ታክሎበት ተሳካልኝ እንጂ የሀጅ የጉዞ ፕሮግራሜ ተስተጓጉሎ ነበር

ፕሮግራምህ እንዲት ነበር ሊስተጓጎል የነበረው?

ታሪኩ ረጅም ነው ባልጀምረው ይሻላል

ግድ የለም ቀጣዩ ወደ መካ በረራችን ሰአታት ይቀሩታል
ታሪኩን አጫውተኝ መስማት ጓጉቻለሁ

ካልክ እንግዲህ ይኸውልህ
" እኔ በግል ሆስፒታል ውስጥ ፊዚዮ ቴራፒስት ነኝ ክፍያው ብዙም አጥጋቢ ባለመሆኑ የሀጅ ጉዞን ለማሳካት ለ20 አመታት ነበር ገንዘብ ሳጠራቅም የኖርኩት
እናም በዚህ አመት ሀጅ ለማድረግ የሚያስችል በቂ ገንዘብ ስላኖርኩ በደስታ ነበር የሀጅ መሰናዶዬን በማጠናቀቅ ላይ ነበርኩ

በምሰራበት ሆስፒታል ሙሉ አካሉ ፓራላይዝ የሆነ ሚስኪን ታዳጊ ልጅ ክፍል ይዞ ህክምና ይከታተላል
ወደ ምሳ ሰአት አካባቢ ላይ ነው የታዳጊው እናት ወደ ቢሮዬ ዘለቀች

ለታዳጊው ለረጅም ጊዜ የህክምና አገልግሎት ከሚሰጡት ውስጥ በቀዳሚነት እኔ ኑኝ
በእርግጥም ብዙም ባይባል ከዕለት ዕለት በጤናው ላይ መጠነኛ መሻሽሎችን አይቻለሁ ..

እናቲቱ ፊቷ ላይ ጭንቀት እና መረበሽ ይታይባታል

በሀዘን በተዋጠ በሰለለ ድምፅ
ጋሼ ብላ ነው የምትጠራኝ
" ጋሽ ሰኢድ ልጄን ከእንግዲህ ለአላህ ልተወው ነው ዛሬ የመጨረሻችው የህክምና ዕርዳታ የምናገኝበት ቀን ነው " አለችኝ

ግራ ተጋባው
ለልጇ በምንሰጠው የህክምና አገልግሎት ደስተኛ ስላልሆነች ሌላ ሆስፒታል ልትቀይር ነው? በማለት በውስጤ አሰብኩ

እናቲቱ ቀጠለች " ጋሽ ሰኢድ አላህ ምስክሬ ነው አንተ ለልጄ ከአላህ በታች የተቻለህን እርዳታ አድርገሃል ብዙ መሻሻልም አሳይቷል አላህ ጀዛህን ይክፈልህ በማለት እንባዋን እያፈሰሰች ከቢሮዬ ወጣች ..

ታሪኩን ተመስጦ የሚሰማው ከሪም ግራ በመጋባት
" በምትሰጡት አገልግሎት ደስተኛ ከሆነች እና የልጇ ጤንነት መሻሻሉን ካመነች ታዲያ ለምን ሆስፒታሉን ለመልቀቅ ወሰነች ?

" በወቅቱ እኔም ተመሳሳይ ጥያቄ ነበር ጭንቅላቴ ውስጥ የተመላለሰው
ከቢሮዬ ወጥቼ ቀጥታ ወደ ሆስፒታሉ አስተዳደር በመሄድ ሴትየዋ የነገረችኝን በመግለጽ ምን እንደ ተፈጠረ የሚያውቁት ነገር ካለ ብዬ ጠየቅኩኝ

አሳዛኝ መልስ ነበር የሰማሁት
የታማሚው ልጅ ወላጅ አባት ከስራ በመባረሩ ምክንያት ለቀጣይ የህክምና ወጪ የመክፈል አቅም ስለሌላቸው ሆስፒታሉን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸው ነበር

በሰማሁት ዜና እጅጉን ተረበሽኩ

ሆስፒታሉ ወጪውን ሸፍኖ ታዳጊው ቀሪ ህክምናውን ይከታተል ዘንድ አስተዳደሩን ተማፀንኩት

" ይሄ የግል ሆስፒታል እንጂ የበጎ አድራጎት ድርጅት አለመሆኑን በመግለጽ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ነግሮኝ ጥያቄንዬ ውድቅ አደረገው ።

ልቤ በሀዘን እንደተሰበረ ቢሮውን ለቅቄ ወጣሁ።

ከነፍስያዬ ጋር ሙግት ገጥሜ ከውሳኔ ላይ በመድረስ
ለሀጅ ጉዞዬ በማለት ለ20 አመታት ሳስቀምጥ ወደ የነበረውን ገንዘብ አውጥቼ ተመለስኩ

" አላህ ሆይ የአንተን ቤት እንዲሁም የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ ) መስጊድ ለመዘየር ህይወቴን በሙሉ ገንዘብ ሳጠራቅም መኖሬን ታውቃለህ የእናት ለቅሶ የታዳጊ ልጅ ስቃይ ቸል ብዬ በንፁህ ህሊና ጉዞ ማድረግ አይቻለኝምና ይህንን ገንዘብ ለእናት እና ልጅ ለመስጠት ወስኛለሁ " በማለት ከአላህ ጋር አውርቼ ቀጥታ ወደ ሆስፒታሉ ሂሳብ ክፍል ሄድኩኝ

ለቀጣይ 6 ወራት ህክምና በቂ የሚሆን ገንዘብ ነበር

ለገንዘብ ተቀባዩ
እባክህን ለልጁ እናት ክፍያውን እኔ መሸፈኔን አትንገራት ሆስፒታሉ ነው በላት አልኩ

በተመስጦ ሲያዳምጥ የነበረው ከሪም
" ለ20 አመታት ያጠራቀምከውን ገንዘብ በጠቅላላ ለበጎ ተግባር ካዋልከው ታዲያ እንዴት ወደ ሀጅ ልትመጣ ቻልክ ? በማለት በግርምት ጠየቀ

የሀጅ ዕድሌን በማጣቴ ብቆጭም ለጊዜውም ቢሆን ለእናት እና ልጅ በመድረሴ ልቤ በደስታ እና እርካታ ተሞልቶ ነበር ምሽት ወደ መኝታዬ የሄድኩት

በቀጣዩ ሳምንት ነበር
ከእንቅልፌ የስልክ ጥሪ ቀሰቀሰኝ

የሆስፒታሉ አስተዳደር ነበር የደወለው

የሆስፒታሉ መስራች እና ባለቤት የሆነው ግለሰብ የዲስክ መንሸራተት ችግር ስላለበት የግል ቴራፒስት ሁሌም አይለየውም ነገርግን
ሚስቱ እርግዝናዋ ዘጠኝ ወር ስለገባ በማንኛውም ሰአት ልትወልድ ትችላለች በሚል የግል ዶክተሩ እሷን ይከታተል ዘንድ አድርጓል

እሱ ደግሞ በአላህ ቤት ተገኝቶ ለሚስቱ እንዲሁም ለሚወለደው ህፃን ዱአ እና ሀጅ ለማድረግ ጉዞ አቅዷል
በመሆኑም
ሀጅ አብሮት የሚጓዝ የህክምና ባለሙያ አዘጋጅልኝ ስላለኝ አንተን ልጠይቅህ ነው የደወልኩት
ለአንተም ትልቅ ዕድል ነው በዛውም ሀጅ ታደርጋለህ አለኝ

ስልኩ ጆሮዬ ላይ እንዳለ ነበር ሱጁድ የወረድኩት

አየህ የአላህን ታላቅነት እና ተአምር
ያለምንም ወጪ በቅንጡ የአውሮፕላን ክፍል በመብረር ወደ ሀጅ እንድመጣ አደረገኝ
አላሁ ወክበር ..

በበረራ ላይ በነበረን ቆይታ ለሆስፒታለ ባለቤት.. ስለ ሚስኪኗ እናት እና ስለ ፓራላይዝ ልጇ ታሪክ ሁሉንም አጫወትኩት

በጣም ነበር ያዘነው

የታዳጊውን ህክምና ሙሉ ወጪ ለመሸፈን እና ከስራ ገበታው ለተፈናቀለው የልጁ አባት ስራ እንደሚሰጥ ቃል ገባልኝ
በተጨማሪም
ለሀጅ ጉዞ ለ20 አመታት አጠራቅሜ የነበረውን እና ለልጁ ህክምና የከፈልኩት ገንዘብ ሙሉ ቡሙሉ ተመላሽ እንደሚያደርግ ገለፀልኝ

ይህ የአላህ ውሳኔ እንጂ የማንም አይደለም
ታላቅ ውለታ ከታላቁ ጌታ ..

በሰማው ታሪክ ልቡ የተነካው ከሪም
በእርግጥም መልካም ሰው ነህ በማለት ሰአድ እቅፍ በማድርገ
" በእራሴ እንዳፍር ነው ያደረግከኝ
በየአመቱ ተመላልሼ ሀጅ ማድረጌ ትልቅ ጉዳይ መስሎ ይሰማኝ ነበር የአንተ ሀጅ ከእኔው ሺህ ተመጣጣኝ ነው ..

እኔ ወደ አላህ ቤት ስመጣ ኖሪያለሁ
አንተን ግን አላህ ቤቱን እንድትዘይር አመቻችቶልሃል ..
አላህ ሐጅህን ይቀበልህ
@ቢላል ዘይድ
https://t.me/ya_Allah_maran
773 views śmîle , edited  05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 08:38:04
የመልካምነት ምላሽ
.
.
.
ታሪኩን ለማምበብ
@ya_Allah_maran
491 views śmîle , edited  05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 06:41:42 ከቻልክ
መልካም ነገር ሁሉ የሚገባበት በር ሁን፣
ካልሆነ ብርሃን የሚገባበት መስኮት ሁን፣
ካልቻልክ የደከማቸው የሚደገፉበት ግድግዳ ሁን::
ይህንን ሁሉ ካልቻልክ ሰዎችን የሚያስቸግር የመሬት እሾህ አትሁን
اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين
የአላህ እዝነትና ሰላም መልካም ነገርን ሁሉ ባስተማሩን ነቢይ ላይ ይስፈን።
በሰለዋት፣ በዱዓ፣በካህፍ የተዋበና ሰላም የሆነ ጁምዓ ይሁንልን!
497 viewsAtika Bint, 03:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:54:27 ሌሊት ነው። ከጥቂቶች በቀር የአደም ልጆች ሁሉ በተኙበት ቅፅበት አንዲት ከጌታዋ ጋር እምታወጋ እንስት ቤት ሌባ ገብቶ ወዲህ ወድያ ይዋልላል። እንስት ሰላት ላይ ናት። (135 አመተ ሂጅራ)

ከቤቱ የገባው ሌባ ቤቱን ሲያስስ ቆይቶ ከአንዲት የውሀ ማንቆርቆርያ ውጭ ባለማግኘቱ ባዶ እጁን ሊወጣ ሲል እንስት ሰላቷን አጠናቅቃ ቀና አለች።

«ለመዝረፍ መጥተህ እንደሆን እባክህ ባዶ እጅህን እንዳትወጣ!» ብላ ተማፀነች።
«ምንም እኮ የለም ቤትሽ ውስጥ» ብሎ በግርምት መለሰላት።

«አንተ ምስኪን! ሂድ እስኪ በዚህ ማንቆርቆርያ ዉዱ አድርግ'ና እዚያች ክፍል ሂደህ ሁለት ረከዐ ስገድ፤ ባዶ እጅህን አትወጣም» ሌባዋን ልትካድም ምትፍጨረጨር ሴት ተናገረች።

ከመስገጃዋ ንቅንቅ አላለችም፤ የሰማያት ደጆች ደንበኛ የሆነውን እጇን ወደ ላይ ከፍ አድርጋ፦ «ጌታዬ! ይሄ ሰው እኔ ዘንድ መጥቶ ምንም አላገኘም። ከበርህ እንዲቆም ልኬዋለሁ'ና ከፀጋህ እና ከምንዳው ለግሰው» አለች።

ሌባው ውዱውን አጠናቅቆ ሰላት ጀምሯል። ያዘዘችውን ሁለት ረከዓ ሰግዶ ሲጥመው ይደጋግም ጀመር 4 ረከዐ፣ 6 ረከዐ፣ 10 ረከዐ...ፈጅር ደረሰ።

«እሺ! ሌሊቱ እንዴት ነበር?» ብላ ጠየቀችው።
«እጌታዬ ዘንድ ተዋርጄ እና ተዋድቄ ቆምኩ፤ ይቅርታዬን ተቀብሎኝ ስሜቴን ጠገነው። ውጥኔም ተሳክቷል» ብሎ ትቷት ወጣ።

እጆቿ ዳግም ወደ ሰማይ ተዘረጉ፦ «ሰዪዲ! ያ መውላይ! ይህ ሰው ውስን ሰዐታትን ከፊትህ ቢቆም ተቀበልከው፤ እኔ እስካወቅኩህ ድረስ ከፊትህ ከመቆም ተወግጄ አላውቅም። ታድያ ተቀብለኸኝ ይሁን?» በምታውቀው ወግ ጌታዋን በጥያቄ ያዘችው።

ከጀርባዋ ጥሪ ተስተጋባ፦«አንቺ ራቢዓ! ስላንቺ ስንል ተቀብለነዋል፣ ባንቺው ምክንያትም አስጠግተነዋል»

ይህች ሴት ራቢዐተል ዐደዊያ ናት። ለጌታዋ ፍቅር ነፍሷን የሰዋች ድንቅ ማንነት፣ የውዴታ መስዋዕት፣ የአላህ ተዐምር...።

አምልኮዋ ከእዩልኝ ብቻ ሳይሆን ከቅጣት ፍራቻ እና ከምንዳ ክጀላም ፀድቶ የተጥራራም ነበር። ጀነትን ከጅላ እና እሳትን ፈርታ ሳይሆን በውዴታው ተጠምዳ እንደምታመልከው እንዲህ ስትል ታወጋው ነበር፦

«ጌታዬ! ጀነትን ብቻ ከጅዬ ካመለክሁህ፤ ጀነትን ንሳኝ። ግና ውዴታህን ብቻ ከጅዬ እማመልክህ እንደሆን እባክህ ፊትህን ከማየት አትንፈገኝ» የኢኽላስ ላይኛው ክፍል።

ሰዎቹ ቋንቋቸው ይለያል። የሚናገሯትን ንግግር በቅኔ አስመላሽ ተርጓሚ ካልተፈሰረልህ ሳትረዳው ሰምቶ-አደር ብቻ ትሆናለህ።

የጌታዋን ፍቅር በቋንቋዋ ዘውትር ስታዜም ሰምቶ ማይደመም ጃሂል፣ ዐሊም፣ ዐቢድ፣ ዓሪፍ የለም'ና ከመጀመርያው ምድብ ላይ ቆሜ እንዲህ ስትል ተደመምኩ።

ሁለት አይነት ውዶች አንተን ወደድኩህ
አንዱን ለፍላጎቴ አንዱን ለክብርህ

ለፍላጎት ብዬ የሰየምኩልህ
ስጠመድልህ ነው እያወደስኩህ

ለክብርህም ብዬ አንተን የወደድኩህ
ግርጆህን ገፈኸው አንተን እስካይህ
* * ***
አልመሰገንም በዚህም በዝያኛው፤
በዚህም በዝያኛው ምስጋና ያንተ ነው።

ዐጂ....ብ ራቢዓ! ቃላቶችሽን ዐጅበው የወጡ ትንፋሾች ጀነት ላይ የተተከሉ ዛፎችን አስዘምረው የዐርሹን ቀበሌያት እንደሚያስተጋቡ የቀልቤ ስሜት ምስካሪ ነው።

ትንፋሽ እሚግራ ውሀ አጣጭ የማያሻት ራቢዓ ዘመናትን በብቸኝነት ከጌታዋ ጋር ስታወጋ ታሳልፋለች።

ብቻዋን ሁና ከምትዋልልበት የፍቅር ግዛት ውስጥ ለቀልቧ እንጂ ለስጋ ግድ የሌላት እንስት የሰው ዘያሪ ቢጎበኛት በፍቅሯ አብዮት ትዘምራለች፦

የልቤ አንደበት ላንተ አውጊ ነው
ለዘያሪ ሰዎች ስጋዬን ትችያለው

ስጋዬን ለ'ንግዳ አጫዋች ሳደርገው
ቀልቤን ለወዳጄ «አውጋ» እለዋለሁ።

ዑለማኦች ከፊቷ ሲቀርቡ ያቀረቅራሉ፣ ሙፈሲሮች ምክርን ሲሹ ከቀዬዋ ደጅ ይጠናሉ፣ ሙሐዲሶች አክባሪዎቿ ናቸው...። ያላህ ወዳጅ የምድር ተወካይ ትመስል፤ ሰዎቹ ማዕከል አድርገዋታል።
* **

ማሊክ ኢብኑ ዲናር፣ ሀሰነል በስሪይ እና ሸቂቅ አል በለኪይ ከራቢዓ ቀዬ ተሰይመዋል። (ትላልቅ ዑለማኦች) ራቢዓ ህመም ጠንቶባት ካልጋዋ ተቆራኝታለች።

«ወዳጁ በሚሰነዝረው ዱላ ትዕግስት እሚያጣ ሰው እውን ወዳጅ አይደለም። » ሲል ወቀሳ ቢጤ ማፅናኛ ለራቢዓ ሰነዘረላት ሀስነል በስሪይ። (አላህ ባመጣው በሽታ ታገሺ እያላት እኮ ነው! ፖ...አላወቃትም መሰል!)

«ይኼ የራስ ወዳድነት ሽታ ያለው ንግግር ነው» አለች፤ ተናግረህ ሙተኻል አይነት ቅኔ አዘል ዘዬ ባለው ለዛ።

«ወዳጁ በሚሰነዝርበት ዱላ ያላመሰገነ ሰው እውን ወዳጅ አይደለም» ብሎ ለማሻሻል ሞከረ ሸቂቅ የሀሰንን ንግግር ተንተርሶ። በበሽታው አመስግኚ እያላት ነው።

«ያንተው ትንሽ ከዝያኛው ይሻላል» አለችው፤ ምስጋና ብርቋ እንዳልሆነ ሰሙን ከማሩ ሳትለይ እያስነበበችው።

« ወዳጁ በሚሰነዝርበት ዱላ የማይረካ ሰው እውን ወዳጅ አይደለም» ሲል ማሊክ የጓደኞቹን ንግግር አሻሽሎ መጣ።

ከጓደኞቹ የተሻለ ፈሊጥ ይዞ ቢቀርብም፤ ራቢዓ ሀገር ስጡኝ ሳትል እንቆቅልሹን ልትፈታላቸው ልሳናኗን አስታጠቀች።

«ወዳጁ ከሚሰነዝርበት ዱላ ይልቅ በወዳጁ እይታ ያልተመሰጠ ሰው እውን ወዳጅ አይደለም» እስቲ ድገማት....አይጥምም? አያስደምም? ፉቀሀኦቹን እንዲህ ግራ ምታጋባ ልሳነ-ብርቱ እህት ናት ራቢዓ።
* * ***

ምትኖረው ለመሞት ነው፤ ምትሞተው ያ የጓጓችለትን የጌታዋን ፊት ለማየት ነው። አሟሟቷ እንጂ አኗኗሯ አሳስቧት አያውቅም።

በተጎሳቆለ እና በተጨናበሰ ገፅታ ሁና በጎዳናዎች ላይ ስትጓዝ ከሊቀ-ሊቃውንቱ ሱፍያን አስ-ሰውሪይ ራቢዓን አገኛት።

«ጉስቁልና እና ችግር የፀኑብሽ ይመስላል። እዝያ ጎተቤትሽ ያለውን ባለፀጋ እንዲደጉምሺ ብትጠይቂው ጥሩ ነበር።» አላት እዝነት በተቀላቀለበት ስሜት።

«ሱፍያን!! የምን ጉስቅልና ነው እምትለው? ልቅና እንጂ ጉስቅልና የሌለበት፣ ሀብት እንጂ ድህነት የለሌለበት ኢስላም ላይ አይደል እንዴ ያለሁት?

ወላሂ ዱንያ በእጁ የሆነችውን ጌታ ከ'ሷ ስጠኝ ብዬ ጠይቄው አላውቅም። ታድያ እንዴት ነው ዱንያ በእጁ ያልሆነችውን መክሉቅ ምጠይቀ?» ዝም ያስብላል።

የዛሬውን ሳይሆን የትናንትን ተሰዉፍ በተግባር ተውናው ዳግም በዱንያ ላይ አምሳያዋ ላይደገም አሻራዋን ትታ ያለፈችው ራቢዓ ዐጃኢቦችዋ በ'ስክሪን ሰሌዳዎች ከሚበተኑ ፊደላት የላቀ ነው።

Sefwan Ahmedin
_____

ንጭ፦
تذﻛﺮﺓ ﺍﻷﻭﻟﻴﺎﺀ
حلية الأولياء وطبقات الأصفياء
احياء علوم الدين
ሼር ያርጉ ይቀላቀሉን


https://t.me/ya_Allah_maran

የfacebook #page like ያርጉ

http://www.facebook.com/yaAllahmarantube
647 views śmîle , edited  05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 22:30:59 ልብ ላሉ ልቦች ልብ የሚነካ ታሪክ
#ንጉሶች_የሚጣሉበት_ጫካ


#ከወደዱት_ ሼር ያርጉት

የቴሌግራም ቻናላችንን join ይበሉ።


https://t.me/ya_Allah_maran

ግሩፓችን ላይ ሰው አድ ያርጉ
@YAM_TUBE2
582 views śmîle , edited  19:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:54:21
ጠብታን በአዳማ #ሐላል_ፍቅር
#የፊታችን_እሁድ በኦልያድ አዳራሽ /#ማለዳ 2 ሰዓት

ይህንን ፖስት ሁላችሁም ሼር በማድረግ
ለፕሮግራሙ ተደራሽነት አግዙን!

ለበለጠ መረጃ:- 0913514352 – 0927986637
659 views śmîle , 04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 08:03:40
እጅግ ውብ ምርጥ የሆነው ቅፅበት ሁሉም የአላህ ባሮች የሚናፍቋት የሚጠብቋት...........

አላህ ለመሄድ ከሚታደሉት ሰዎች አላህ ያርገን......አሚን
#መልካም ቀን
#EIA
Share ያርጉት
ቻናላችንን join ይበሉ
የቴሌግራም ቻናላችንን join ይበሉ።


https://t.me/ya_Allah_maran

ግሩፓችን ላይ ሰው አድ ያርጉ
@YAM_TUBE2
862 views śmîle , edited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:31:38 * ከተብቃቃን ትንሹም ብዙ ነው፣
* ከተስገበገብን ብዙዉም ትንሽ ነው፣
* ከወደድን እሩቁም ቅርብ ነው ሐቢቢ፣
* ከጠላን የቅርቡም እሩቅ ነው፣
* ምስጢሩ ለነገሮች ባለን እይታ ላይ ነው ያለው፣
* ደስታ አስተሳሰብ ነው መንገድ አይደለም፣
* አስተሳሰብህን ካስተካካከልክ ነገሩ ሁሉ ይስተካከላል።
* እይታህ ካማረ ነገሩ ሁሉ ያምራል።
* ታገል ነገሮችን ለማሳመር ሞክር።

اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين

በምስጋና፣ በሰለዋት፣ በዱዓ፣በካህፍ የተዋበና ሰላም የሆነ ጁምዓ ይሁንልን!
881 viewsAtika Bint, 04:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ