Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር "የስፖርት ልማት ለትምህርት ጥራት!" በሚል ርዕስ ለርዕሰ መምህራን ስልጠና ሰጠ።

(ቀን ጥር 9/2016 ዓ.ም)

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር "የስፖርት ልማት ለትምህርት ጥራት!" በሚል ርዕስ ለርዕሰ መምህራን ስልጠና ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ታጋይቱ አባቡ ስልጠናው ለርዕሰ መምህራን የተዘጋጀው የስፖርታዊ እንቅስቃሴን በየትምህት ቤቶቻችሁ በይበልጥ ለማጠናከር እንዲሁም ተማሪዎች በስፖርታዊ ውድድር ውስጥ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲችሉ ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በስልጠና መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የእስፓርት ትምህርት ስልጠና ዳይሬክተር አቶ ጎሳዬ አለማየሁ የስልጠናው ዋና አላማ ተተኪ ስፖርተኞችን በብዛትና በጥራት ማፍራት ነው ያሉ ሲሆን ርዕሰ መምህራን በየትምህት ቤቶቻቸው ለተማሪዎች የስፖርታዊ ማዘወተሪያ ቦታዎችን እንዲያመቻቹም ተናግረዋል።



ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት በዶ/ር ዘሩ በቀለ እየተሰጠ ይገኛል፡፡


መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication