Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐበሊክ ሰርቨስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሪፎርም ክትትል እ | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐበሊክ ሰርቨስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሪፎርም ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት የትምህርት ቢሮን የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት አቅድ አፈፃፀም ምዘና አካሄደ።

(ቀን ጥር 8/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐበሊክ ሰርቨስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የማስፈፀም አቅም ግንባታ ዘርፍ የሪፎርም ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት የቢሮዉን የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተቋማት ሪፎርም የአገልግለት አስጣጥና አሰራር ውጤታማነትን ምዘና አካሄዳል፡፡


ምዘናውም በስምንት ዋና ዋና የምዘና ነጥቦች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን እነዚህም በየደረጃው የሚገኘው አመራር የተሰጠውን ተልእኮ እና ሀላፊነት የማስተባበርና የመምራት ብቃት፣ የተቋሙ እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የሰራተኛ ተሳትፎና ምቹ የሥራ ከባቢ ከመፍጠር አንፃር፣ የተገልጋይ እና የባለድርሻ አካላት አጋርነት የትኩረት መስክ ፣ የግልፀኝነትን ተጠያቂነት ስርዓት ፣ ተቋማዊ መማማር እና አቅምን ከማጎልበት ረገድ የተካሄደበት መንገድ፣ የፈፃሚ ውጤታማነት ያለበት ደረጃ እና ተቋማዊ ውጤታማነት ዙሪያ ትኩረት በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡ ያለበትን ደረጃን በመመዘን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ምዘናው ተካሄዳል፡፡



መረጃዎችን ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc