Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተቋሙን የ2016 የትምህርት ዘመን የ6 ወራት እቅድ | Addis Ababa Education Bureau

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተቋሙን የ2016 የትምህርት ዘመን የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት ገመገመ።

(ቀን ጥር 6/2016 ዓ.ም) ሪፖርቱ ቀደም ሲል በቢሮው የማኔጅመንትና የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የተገመገመ ሲሆን በዛሬው መርሀ-ግብር የ2016 የትምህርት ዘመን የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቢሮው የእቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታሁን ለማ እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ የተከናወኑ ቅንጅታዊ ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እና ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት በሪፎርምና የአገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ዳዊት ከበደ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።


በ2016 የትምህርት ዘመን በ6 ወራት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ልማት ስራው ውጤታማ እንዲሆን በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን እና ቢሮው ላስመዘገበው ውጤት የሁሉም ሰራተኞች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በመርሀ-ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ጠቁመው የተለዩ የመልካም አስተዳደር እና የብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ የተወሰዱ የተለያዩ የመፍትሄ እርምጃዎች የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ እንዲሆን ማስቻሉን ገልጸዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ቢሮው በበጀት አመቱ ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ