Get Mystery Box with random crypto!

Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700

የቴሌግራም ቻናል አርማ wuhalikconstructio — Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700 W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wuhalikconstructio — Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700
የሰርጥ አድራሻ: @wuhalikconstructio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K
የሰርጥ መግለጫ

A construction talk Show on Ethio FM 107.8 !!! A platform for Construction discussions!
👉"ውሃልክ" የሬዲዮ ፕሮግራም በአገራችን የኮንስትራክሽን ግንባታዎች ዙሪያ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ በሰከነ መደማመጥ በልክ እና በቁም-ነገር የምንጨዋወትበት የሁሉችንም የጋራ መድረክ ነው።
👉ይሣተፉ፣ ሰብስክራይብ ያድርጉ፣ ባለሞያዎችንም ይጋብዙ..

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-28 23:58:01 #በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ በወርሃ ሐምሌ፤ በቀን 09/2014 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በተደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ....

ከዕለቱ እንግዳችን አቶ ሽመልስ ተስፋዬ ጋር በመዲናችን አዲስ አበባ ተግባራዊ ስለሆነው እና በቀጣይ ሊሰራበት ስለታቀደው የ"ፈጣን አውቶቡስ መንገዶች" ዝርጋታ እያነሣሣን፤ ጅምር ሒደቱንም ከዓለም ዓቀፍ ተሞክሮዎች ጋር እያናፀርን እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር መጨዋወታችን ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ይህንኑ ፕሮግራም በዕለቱ ሳናጋራችሁ በመቅረታችን ከዝግጅት ክፍላችን ይቅርታችሁን እየጠየቅን፤ የፕሮግራሙን ጥቅል ፍሬ-ነገር ዳግም ታደምጡ ዘንድ በአክብሮት ስንጋብዛችሁ እንደወትሮው ሁሉ ደስ እያለን ነው።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ_መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።
612 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 20:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 20:38:52 #በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ ባሣለፍነው ወር ሰኔ 25/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በተደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ...

ከዕለቱ እንግዳችን አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ጋር በዋናነት በ"Import substitution" እና በ"Export Expansion" ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ በክፍል አንድ ቆይታችን እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር መጨዋወታችን ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የዚህኑ ፕሮግራም ሁለተኛ ክፍል በዕለቱ ሳናጋራችሁ በመቅረታችን የዝግጅት ክፍላችን ይቅርታ እየጠየቀ፤ በሐምሌ 02/2014 ዓ.ም ለስርጭት የበቃውን የፕሮግራሙን ሁለተኛ ክፍል ቢዘገይም ዳግም ታደምጡልን ዘንድ በአክብሮት እየጋበዝን፤ በሒደቱም ውድ ጊዜያቸውን ለሰጡን የውሃልኩ ቤተኛ አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ያለንን አክብሮት አከል ምስጋና ስናደርስ ደስ እያለን ነው።

#የውሃልክ_ሕንፀት #በውሃልክ_መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን_እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።
604 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 20:08:04
#ከኢመአ የማህበራዊ ትስስር ገፅ ባገኘነው መረጃ መሠረት...

"የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልልን፣ ከኦሮሚያና ጋምቤላ ጋር በአቋራጭ የሚያስተሳስረው የጎሬ፣ ማሻ~ቴፒ መንገድ ግንባታ በትኩረት እየተሰራ ነው።

የግንባታው አጠቃላይ አፈፃጸም ከ35 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፣ በቀጣይ ዓመት መጀመሪያ ወደ አስፋልት የማንጠፍ ሥራ ይሸጋገራል። ቀደም ብሎ ፕሮጀክቱ ከመንገድ ወሰን ማስከበር ጋር ተያይዞ ተግዳሮቶች የነበሩበት ሲሆን፣ የኢመአ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሥራ ተቋራጩ፣ የክልል የዞንና የወረዳ አመራር አካላት ከተለያዮ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመቀናጀት መቅረፍ ተችሏል።

140 ነጥብ 2 ኪ.ሜ የሚረዝመው ፕሮጀክቱ በእስከአሁኑ የግንባታ ሥራ፤ የአፈር ጠረጋና ሙሌት፣ የፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ፣ የሰብቤዝ ንጣፍ፣ የጠጠር መፍጨት እና የነባር መንገድ ለትራፊክ ምቹ የማድረግ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።

የደቡብ ኮሪያው ሃይንዳይ ዴቨሎፕመንት ካምፓኒ ግንባታውን በ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ እያከናወነ ነው። የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ሱሰንግ ኢንጅነሪንግና ዳሳን ኮንሰልታንት እንዲሁም ሀገር በቀሉ ኔት ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ በንዑስ ተቋራጭነት በጥምረት ይሰራሉ። ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ መንግስትና በኮሪያው ኤግዚም ባንክ ወጪ ይሸፈናል።

የመንገዱ መገንባት በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን የማር፥ ቡና፥ ቅመማቅመም እንዲሁም የሻይ ተክል ምርቶች በተገቢው ፍጥነትና ጥራት ወደ መሃል ገበያ ለማድረስ ያስችላል። በቀጣይ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን ከማሳለጡም ባሻገር፣ የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች ማሕበራዊ አገልግሎት ተቋማት ተደራሽነትን ያሰፋል። በሥፍራው የሚገኘውን ሰፊ የቱሪዝም ሃብት የሚነቃቃበትን ምቹ ዕድልም ይፈጥራል"፤ ተብሏል።
669 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 19:48:04
#Addis_Ababa_City...
Meskel Flower Street Views.
722 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 16:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ