Get Mystery Box with random crypto!

Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700

የቴሌግራም ቻናል አርማ wuhalikconstructio — Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700 W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wuhalikconstructio — Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700
የሰርጥ አድራሻ: @wuhalikconstructio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K
የሰርጥ መግለጫ

A construction talk Show on Ethio FM 107.8 !!! A platform for Construction discussions!
👉"ውሃልክ" የሬዲዮ ፕሮግራም በአገራችን የኮንስትራክሽን ግንባታዎች ዙሪያ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ በሰከነ መደማመጥ በልክ እና በቁም-ነገር የምንጨዋወትበት የሁሉችንም የጋራ መድረክ ነው።
👉ይሣተፉ፣ ሰብስክራይብ ያድርጉ፣ ባለሞያዎችንም ይጋብዙ..

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 11:58:02
በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ በአዲስ አበባ መስተዳድር ስለተፈረሙ በከተማ መስተዳድሩ በጀት እና በአለም ባንክ ብድር የሚከናወኑ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ወጪ ስለሚደረግባቸው 3 የመንገድና የድልድይ ግንባታ የተመለከተ መረጃ ነው እነዚህም

1. የመጀመርያው ከአፍሪካ ጎዳና - ኤድናሞል አደባባይ - 22 ማዞሪያ - እንግሊዝ ኢምባሲ

2. ሁለተኛው የአየር ጤና - ወለቴ ሱቅ - አለም ገና አደባባይ

3. የአቃቂ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ናቸው ።
ስለሚሰሩት መንገዶች ያለው እውነታ

• በአጠቃላይ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው መንገድ ነው፡፡
• ከ15 - 30 ሜትር የጎን ስፋት ያላቸውን 3 የመንገድና የድልድይ ግንባታ ያካተተ ነው፡፡
• ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነውን Intelligent Transport System (ITS) ያካተተ ዲዛይን የተሰራለት ነው፡፡

• የትራፊክ ፍሰትና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን በመከናወን ላይ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡
• ከ2.4 – 4 ሜትር ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ አለው፡፡
• 2 ሜትር ስፋት ያለው የብስክሌት ብቻ መሄጃ መንገድ አለው፡፡
• 9 የሳይክል ማቆሚያና 3 የሳይክል መከራያ ቦታዎች አሉት፡፡

• ዘመናዊ የመንገድ መሰረተ ልማትን ታሳቢ ያደረጉ የብልህ የትራንስፖርት ስርዓት አለው።
•10 የመንገድ መጋጠሚያዎች ላይ ሲሲቲቪ ካሜራዎች አሉት።
• 2 ቦታዎች ላይ ዲጂታል የትራፊክ መቁጠሪያዎች አሉት።
• ቅፅበታዊ የአውቶቡስ መረጃ ማግኛ ስርዓቶች አሉት።

• ኦፕቲክ ፋይበርና ዲጂታል ዋይፋይ ባክአፕ አለው።
• መዝናኛ ቦታ ተካቷል።
የህዝብ መጸዳጃ ቤቶች ግንባታ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታ ማሻሻያ
• የፈጣን አውቶብስ መስመር (BRT B-7) አካቷል፡፡
......................
@bbc_amharic1
126 viewsAselefe Bogale, 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:57:12
የሲሚንቶ ግብይት መመሪያ ከወጣ በኋላ ምርቱ ገበያ ላይ አለመኖሩ ተገለጸ

የሲሚንቶ ምርቶችን ግብይት እና ስርጭት ስርዓት የሚደነግገው መመሪያ ከወጣ በኋላ በብዙ ከተሞች የሲሚንቶ ምርቶች አለመኖራቸውን አዲስ ማለዳ ከተጠቃሚዎች እና ከምርት አከፋፋዮች አረጋግጣለች።

ይህ የሆነውም በመመሪያው የተላለፈው የሲሚንቶ ምርቶች ጊዜያዊ የመሸጫ ዋጋ ለነጋዴዎች አዋጭ አይደለም በሚል እንደሆነም ተገልጿል።

ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ለሥርጭቱ የተመረጡ አንድ ወኪል ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ እኔ እንዳከፋፍል የተመረጥኩት ከዞን ከተማ 80 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላለው ማኅበረሰብ ነው።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3e6n14c
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
116 viewsAselefe Bogale, 08:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 15:56:14 በስምንት ቢሊየን ብር ወጪ በግንባታው ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ

ለልህቀት ማዕከሉ ግንባታ በለገጣፎና በሰንዳፋ መካከል ባለ በረክ በሚባል ወረዳ ውስጥ 14 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት መፈቀዱ ተነግሯል

ሰኞ ነሐሴ 23 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በግንባታው ዘርፍ የሚታየውን የአቅም ውስንነት በዘላቂነት ለመፍታት በስምንት ቢሊየን ብር ወጪ በመጪው ህዳር ወር የልህቀት ማዕከል ሊገነባ መሆኑን የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ ለኢፕድ እንደገለፁት፤ በተደጋጋሚ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የሚታዩና አገርን የሚጎዱ ክፍተቶችን በማያዳግም መልኩ ለማረም እየተሠራ ነው፡፡ ከሚወሰዱ እርምጃዎች መካከልም በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚታየውን የአቅም ውስንነት በዘላቂነት ለመፍታት በመጪው ህዳር ወር የልህቀት ማዕከል ይገነባል፡፡

የልህቀት ማዕከሉ የተለያዩ ጠቀሜታዎች ቢኖሩትም፤ በተለይ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የሚታየውን የአቅም ውስንነት ይቀርፋል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ የኮንስትራክሽን ታሪክ ቢኖራትም በዘርፉ ተወዳዳሪ አለመሆኗ የሚያስቆጭ መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ኢንጂነር ታምራት ገለፃ፤ ትላልቅና ውስብስብ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ በአገሪቱ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ግብዓቶች ጥራት የሚረጋገጠው ወደ ውጭ አገር ናሙና ተልኮ ነው፡፡ ይህ ለብዙ አደጋዎች የሚያጋልጥና የአገሪቱንም የኮንስትራክሽን ታሪክ የማይመጥን ነው። ስለሆነም ይህን የልህቀት ማዕከል በመገንባት ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ሌሎች የጥራት ማረጋገጫ የሚፈልጉ የግንባታ ግብዓቶችን በአገር ውስጥ እንዲሠሩ የሚያስችል ይሆናል፡፡

በአገራችን የኮንስትራክሽን ዘርፍ ብዙ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም፤ በሚገባው ልክ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን ያልቻለው መሰል ማዕከላት ባለመኖራቸው መሆኑን ጠቁመው፤ አሁንም ድረስ በአገሪቱ የሚከናወኑ ትላልቅና ውስብስብ የሚባሉ ፕሮጀክቶች በውጭ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ መሆናቸው አሳሳቢና ሊቀረፍ የሚገባ ነው ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የልህቀት ማዕከላት አለመኖራቸው የዘርፉ ኢንዱስትሪ በውጪ የግንባታ ምርቶች፣ ኮንትራክተሮች እና የግንባታ ዕቃዎች ጥራት መለኪያዎች ላይ ጥገኛ እንዲሆን ማድረጉን ገልፀው፤ ማዕከሉ ከውጭ ጥገኝነት ለመላቀቅና የባለሙያዎች አቅም ከመገንባት አንፃር ጉልህ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የልህቀት ማዕከሉን መገንባት ከላይ የተጠቀሱትን የኮንስትራክሽኑን ዘርፍ ችግሮች ለመቅረፍ ይረዳል። በመሆኑም መንግሥት ለግንባታው የሚሆን መሬት ከመስጠቱም ባሻገር የዲዛይን ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ኢንጅነሩ ጠቁመዋል፡፡ በመንግሥት አስፈላጊው በጀት ተይዞለታልም ነው ያሉት፡፡

ለልህቀት ማዕከሉ ግንባታ በለገጣፎና በሰንዳፋ መካከል ባለ በረክ በሚባል ወረዳ ውስጥ 14 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት መፈቀዱንና በአካባቢው ላይ ለልማት የሚነሱ አርሶ አደሮችም ተገቢው የካሳ ክፍያ ተከናውኖ መሬቱን መረከባቸውን ተናግረዋል፡፡

የዲዛይን ሥራው ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ቁጥጥር ሥራዎች አማካኝነት እየተሠራና መገባደድ ላይ መድረሱን እንዲሁም ለመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ከ300 ሚሊየን በላይ ብር መመደቡን ጠቁመዋል፡፡

የልህቀት ማዕከሉ የግንባታ ግብዓቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የሚረዱ ላቦራቶሪዎች የሚኖሩት፤ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ልምምድ የሚደረግበት፤ ጥናትና ምርምር የሚካሄድበት እና የምህንድስናና የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች የሚከናወኑበት ይሆናል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በተለያዩ ምዕራፎች ተከፋፍለው እንደሚሠሩ የገለፁት ኢንጂነር ታምራት፤ በ2015 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎች ይጀመራሉ ብለዋል፡፡ የመጀመሪያው ምዕራፍ በሦስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፤ ቀሪው ደግሞ በኹለት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል ተብሏል፡፡ በአጠቃላይም የልህቀት ማዕከሉ ግንባታ ስምንት ቢሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚፈጅም ተገልጿል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
159 viewsAselefe Bogale, 12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 15:29:14 #በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ በዛሬው ዕለት ቅዳሜ ነሐሴ 21/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በቀጥታ ስርጭት በተመደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ....

የውሃልክ የኮንስትራክሽን ሬዲዮ ፕሮግራም መሥራች እና ዋና አዘጋጅ ብሎም በምህንድስና የሞያ ዘርፍ በካበተ እውቀት፣ ተግባር ተኮር በሆነ የመስክ ልምድ እና ተሞክርዎ ከሃያ አራት [24] ዓመታት በላይ በማገልገል ላይ ከሚገኘው አቶ አሠለፈ ቦጋለ ሙሉ ጋር በ"ግንባታ ፈቃድ አሠጣጥ እና ተያያዥ ችግሮች" ዙሪያ እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር ተጨዋውተናል።

በተለያዩ ግለ ምክንያቶች፤ ይኸው ፕሮግራም ያመለጣችሁ የውሃልክ ቤተኞች፤ የፕሮግራሙን ጥቅል ፍሬ-ነገር ዳግም ታደምጡልን ዘንድ ስናጋብዛችሁ፤ እንደወትሮው ሁሉ ደስ እያለን ነው።

ውድ_አድማጮች... በልዩነት ከምታደርሱን መካር አስተያየት እና ጥቆማ ባለፍ ሁሌም ቢሆን የማድመጥ ሚናችሁ አይለየን።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።
449 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 15:52:45 የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
_____________
ፈተናው ከነሀሴ 23 - 27/2014 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የፈተና ፕሮግራሙም እንደሚከተለው ይሆናል፡-
ፋርማሲ፣ አንስቴዥያ እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ----------------- 23/12/2014 ዓ.ም
ነርሲንግ --------------------------------- 24/12/2014 ዓ.ም
ህክምና እና ጤና መኮንን ------------- 25/12/2014 ዓ.ም
ሚድዋይፈሪ፣ ዴንታል ሜድስን እና ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ ------------- 26/12/2014 ዓ.ም
ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ ፔዲያትሪክ ነርሲንግ እና ሳይካትሪ ነርሲንግ---- 27/12/2014 ዓ.ም
ተመዛኞች ነሀሴ 22/2014 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል እንዲሁም የመፈተኛ ክፍላችሁን መለየት ይኖርባችኋል፣
በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ)፣ የፈተና መስሪያ ግብዓቶች (እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ) እና ስትመዘገቡ ሲስተሙ የሰጣችሁን ስሊኘ ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፣
ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ ስማርት ሰዓት፣
ኤሌክትሮኒክስ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፣
በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም ይኖርባቸዋል፣
የመፈተኛ ከተማ አዲስ አበባ የመረጣችሁ ተመዛኞች በአዲስ አበባ ከተማ ከተዘጋጁ አምስት /5/ የፈተና ማዕከላት በአንዱ፣ ሀዋሳ የመረጣችሁ ተመዛኞች በሀዋሳ ከተማ ከተዘጋጁ ሁለት /2/ ማዕከላት በአንዱ እንዲሁም አምቦ የመረጣችሁ ተመዛኞች በአምቦ ከተማ ከተዘጋጁ ሁለት /2/ ማዕከላት በአንዱ የተመደባችሁ ሲሆን ከዚህ በታች በቀረበው የማስፈንጠሪያ ዝርዝር ላይ የተመደባችሁበትን የፈተና ማዕከል መመልከት ይኖርባችኋል፡፡
ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ የመፈተኛ ከተሞችን የመረጣችሁ ተመዛኞች በመረጣችሁት ከተማ ፈተናው የሚሰጥበትን የፈተና ማዕከል ከታች ካለው ዝርዝር ላይ መመልከት ይኖርባችኋል፡፡
የመፈተኛ ከተሞችና ማዕከላት፡
አዳማ …………………………… ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ ካምፓስ)
አሰላ……………………………… አርሲ ዩኒቨርሲቲ
አሶሳ ……………………………… አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
አምቦ……………………………… አምቦ ዩኒቨርሲቲ & ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ ካምፓስ)
ባህር ዳር ………………………… ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ደብረ ማርቆስ …………………. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
ደሴ…………………………………ወሎ ዩኒቨርሲቲ
ሐረር ……………………………… ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ (ሀረር ጤና ሳይንስ ካምፓስ)
ሀዋሳ ……………………………… ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ & ሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ጅማ ……………………………… ጅማ ዩኒቨርሲቲ
ባሌ ጎባ…………………………… መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
መቱ ……………………………… መቱ ዩኒቨርሲቲ
ጎንደር …………………………… ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
አርባ ምንጭ…………………… አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ወልቂጤ ………………………… ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ፣ ሀዋሳ እና አምቦ ከተሞችን የመረጣችሁ ተመዛኞች ከላይ የተያያዘውን ማስፈንጠሪያ በመጫን የተመደባችሁበትን የፈተና ማዕከል መመልከት ትችላላችሁ፡፡
አዲስ አበባ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተመዛኞች የፈተና ማዕከሉ አፍንጮ በር 3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ ተስፋሁን ህንፃ ላይ ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ:
https://t.me/ayuzehabesha
281 viewsJemal Ali, 12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 15:34:42
#AddisAbaba

በ2014 ዓ/ም 21 ሰዎች በስራ ላይ እያሉ ከህንፃ ወድቀው ሞተዋል !

በ2014 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ በግንባታ ሥራ ላይ ተገቢው የደኅንነት መጠበቂያ ግብዓቶችን ለሠራተኞቻቸው ባላሟሉ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ችግር 23 ሰዎች በሥራ ላይ እያሉ ከሕንፃ ወድቀው ከፍተኛ የአካል ጉዳትና ሞት እንዳጋጠማቸው ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ከ23ቱ ሰዎች 21 ያህሉ የሞት አደጋ የደረሰባቸው መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለጋዜጣው በሰጠው ቃል ፤ በግንባታ ሥራ ላይ ተገቢውን የደኅንነት መጠበቂያ ግብዓቶችን ለሠራተኞቻቸው በማያሟሉ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ላይ ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፤ ግዴታቸውን በማይወጡ ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ከደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።

በሌላ በኩል በ2014 የበጀት ዓመት ከተፈቀደላቸው የግንባታ ቦታ ውጪ የሚጠቀሙና በእግረኛ መንገድ ላይ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች በማስቀመጥ የእግረኛ መንገድን በማጨናነቅ አካል ጉዳተኞችን ለከፍተኛ ችግር እያጋለጡ የሚገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ፣ ከደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ መዘጋጀቱን ባለስልጣን መ/ቤቱ አስታውቋል።

በ2014 ዓ.ም. ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች ጋር በተገናኘ በ136 ድርጅቶች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ መወሰዱን ገልጿል።

በ136 ድርጅቶቹ ላይ የግንባታ ግብዓቶችን እንዲያነሱ ከማድረግ አንስቶ ንብረታቸውን የመውረስ እንዲሁም የመጨረሻ ጽሑፍ ማስጠንቀቂያና የዕገዳ ውሳኔ የማስተላለፍ ዕርምጃዎች መወሰዳቸውን ባለስልጣን መ/ ቤቱ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጿል።

@tikvahethiopia
219 viewsAselefe Bogale, 12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 12:09:25
በመዲናዋ መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ የኪራይ ቤቶች መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የመሳለሚያና አካባቢው የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ይበቃል ጠመረ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ዛሬ ከሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው መርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ ባጋጠመ የሕንጻ መደርመስ አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

እንዲሁም ሰባት ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመው÷ ህብረተሰቡ ከተገነቡ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ቤቶችን ሁኔታ በማየት ለሚመለከተው አካል እንዲጠቁም አሳስበዋል።
FBC
220 viewsJemal Ali, 09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 12:02:35 ቤት ሸጦ መኪና በመግዛት ራይድ የሚሰራ ሰው ለራሱ ስራ እንደፈጠረ ቢሰማው! ምክንያታዊ ነው?

አንድ ልጅ እያደረሰኝ ሲያወራኝ "ተመርቄ ቤተሰቦቼ ላይ ከምቀመጥ ብዬ! ቤተሰቦቼ የገዙልኝን እድሳት የሚቀረው ሁለት መኝታ ኮንደሚኒየም ቤት (የዛሬ ዓመት ከምናምን የገዙት 600ሺ ነበር ብሏል) ሸጨው መኪና በመግዛት ለራሴ የስራ እድል ፈጥሬ እየሰራሁ ነው!" አለኝ፡፡

በኢኮኖሚክስ አስተምሮት ውስጥ የቢሆን ስሌት (Assumption) ታዋቂ ነው! ስለዚህ ቢሆን ወይም let assume እያልኩ ነው የማቀርብላችሁ ስለዚህ አመክንዮው ላይ እንወያይበት (ሊሆንም ላይሆንም መቻል አለ ማለቴ ነው!)። ሃሳቡ የትችት ሳይሆን የውይይት መነሻ ብቻ ነው!

ቤቱን ስንት ሸጥከው? ስለው "2 ሚሊየን ብር!" መኪና ስንት ገዛህ ስለው "1.6 ሚሊየን ብር! የቀረውን ብር አንዳንድ ነገሮች ገዝቼበት የተረፈውን በባንክ አስቀመጥኩ" አለኝ፡፡

በመኪናው በቀን ስንት ትሰራለህ ብዬ ጠየኩት? "ወጪዬን ችዬ 1,500 ብር አለኝ!" እና ከቤት እራስህን ችለህ ወጣህ? ስለው "ቤተሰብ ላይ ነው አሁንም ያለሁት" አለኝ!

ስራ እንዴት ነው? አልኩት! "ከጠዋት እስከ ማታ ዘራፊ እንዳያጋጥም እየተመኘን እየታገልን ነው" አለኝ! እስከ አሁን በአካውንትህ ስንት አስቀመጥክ? ስለው "ማጠፋፋት አይቀርም....ብር" አለኝ።

Let assume!

አሁን የሰርቪስ እና ሌሎች ወጪዎች እንደሌሉ ብናስብ (ቤተሰቦቹ እየመገቡት! ከቤት ባያባርሩት ብንል!) ይህ ሰው በወር 45ሺ ብር ቢያስቀምጥ በዓመት 540ሺ ብር ይኖረዋል! በቀላል ስሌት የመኪናው ዋጋ በሶስት ዓመት ውስጥ ምንም ባይጨምር (1.6 ሚሊየን ብር እንደሆነ ቢቆይ) የመኪናውን ወጪ ለመሸፈን ሶስት ዓመት ያስፈልጋል፡፡

ምሳሌ 1፡- በቀን 1,500 ብር አስገብቶ በሶስት ዓመት ውስጥ በመኪናው የሰራውን 1.6 ሚሊየን ብር ይዞ ሲጠቀምባት የነበረችውን መኪናውን ከሶስት ዓመት በኋላ 1.5 ሚሊየን ብር ቢሸጣት ብንል ይህ ሰው ያካበተው ሃብት 3.1 ሚሊየን ብር ይሆናል! ዘንድሮ 2 ሚሊየን የሸጠውን ቤት ከሶስት ዓመት በኋላ 3.1 ሚሊየን ብር መልሶ ሊገዛው ይችላል?

ቤቱ ከሶስት ዓመት በኋላ 10 ሚሊየን ብር ሊደርስ ይችላል (አዲስ አበባ ውስጥ የቤት/ቦታ ዋጋ እራሱን እጥፍ ለማድረግ ዓመት እየፈጀበት አይደለም!) ቤቱን እንደዘጋ ለሶስት ዓመት ቢያስቀምጠው 10 ሚሊየን ብር ያገኝ ነበር (10 ሚሊየን ብር #አንፃራዊ መኪናም ቤትም ሊገዛለት ይችላል!)፡፡

ምሳሌ 2፡- የተወሰነ ተበድሮም ይሁን ቤተሰብ አስቸግሮ ቤቱን አድሶ በወር 10ሺ ብር አከራይቶ ቢሆን በዓመት 120ሺ ብር አለው (የቤት ኪራይ ዋጋ በዓመት በ30 ከመቶ እያደገ ቢሄድ እና የቤቱ ዋጋ በዓመት 100-150% ቢያድግ) በሶስት ዓመት በኋላ ቤት ኪራዩ በወር 20ሺ (በዓመት 240ሺ ብር) የቤቱ የሽያጭ ዋጋ 10 ሚሊየን ብር ሊደርስ ይችላል፡፡

ስራ መፍጠር ማለት የሚውሉበት ምክንያት ማዘጋጀት ማለት አይደለም! እቤት ያለምንም አይነት ስራ መቀመጥ ከብዙ ጉዳዮች አንጻር መጥፎ እንደሆነ እረዳለሁ! ነገር ግን ትርፍ እና ኪሳራ ከመጪው ጊዜ ሁኔታ ጋር መሰላት አለበት! ሶስት ዓመት መኪና ገዝቶ እየሰሩ እንደሆነ ከሚሰማቸው ሶስት ዓመት የወደዱትን ተጨማሪ ትምህርት እየተማሩ ዛሬ ላይ 2 ሚሊየን ብር የሚሸጥ ቤታቸው 10 ሚሊየን ብር እስኪደርስ የዋጋውን መጨመር መጠበቅ አይሻልም?

አንዳንድ ወላጆች ስራ እንዳይፈታ ለልጄ መሬቴን/ቤቴን ሸጬ መኪና/ባጃጅ ገዝቼለት! ሱቅ ከፍቼለት፤ ወዘተ ይሉ እና ግን ልጆዎት ምን ለወጠ ሲባል መልስ ይጠፋል (መሬቴን ሸጬ አስመርቄው ወይም ሰርግ ደግሼለት የሚሉም አሉ!)፡፡

ስለዚህ አሁን ላይ ወላጆችም ሆኑ ወጣቶች በገቢ፤ በወጪ እና በአዋዋላቸው ላይ በሚያደርጉት ውሳኔ ከሁለቴ በላይ በማሰብ የቀደሙ፤ የአሁን እና የመጪው ጊዜ ሁኔታዎችን ከግምት የከተተ ውሳኔ ለመወሰን ቢሞክሩ መጥፎ አይደለም!

Telegram:- https://t.me/wasealpha
199 viewsJemal Ali, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 15:15:13 #በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ በዛሬው ዕለት ቅዳሜ ነሐሴ 14/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በቀጥታ ስርጭት በተመደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ....

የአንሎክ ኮንስልተንሲ እና ኢንጂነሪንግ ማኔጂንግ ዳይሬክቶር፣ በIFRS ስታንዳርድ በኢትዮጲያ የተመከረላቸው የአቻ ግምት ወይም የ"Asset Valuation" ባለሞያ እና የቢዝነስ አማካሪ ከሆኑት አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ጋር በ"Asset Management" ዙሪያ እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር ተጨዋውተናል።

ይኸው ፕሮግራም ያመለጣችሁ ውድ አድማጮች የፕሮግራሙን ጥቅል ፍሬ-ነገር ዳግም ታደምጡልን ዘንድ ስናጋብዛችሁ፤ እንደወትሮው ሁሉ ደስ እያለን ነው።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።
599 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ