Get Mystery Box with random crypto!

Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700

የቴሌግራም ቻናል አርማ wuhalikconstructio — Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700 W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wuhalikconstructio — Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700
የሰርጥ አድራሻ: @wuhalikconstructio
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.06K
የሰርጥ መግለጫ

A construction talk Show on Ethio FM 107.8 !!! A platform for Construction discussions!
👉"ውሃልክ" የሬዲዮ ፕሮግራም በአገራችን የኮንስትራክሽን ግንባታዎች ዙሪያ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ በሰከነ መደማመጥ በልክ እና በቁም-ነገር የምንጨዋወትበት የሁሉችንም የጋራ መድረክ ነው።
👉ይሣተፉ፣ ሰብስክራይብ ያድርጉ፣ ባለሞያዎችንም ይጋብዙ..

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-19 09:17:29
Life is short... Enjoy it before it melts.
622 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 19:45:46
#በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_የውሃልክ_አድማጮቻችን...

በኮንስትራክሽን የሞያ ዘርፍ ከሃያ[20] ዓመታት በላይ ያገለገሉት ኢንጂኒየር ታደለ ቁሜ በማኔጅመንት ሲስተም አሰልጣኝ፣ አማካሪ እና የተመሰከረላቸው የማኔጅመንት ጥራት ኦዲተር ከመሆናቸውም በላይ በዳበረ እውቀት፣ ተግባር ተኮር ልምድ እና ዘርፈ ብዙ ተሞክሮ ያካበቱትን ልምድ በማቀናጀት ለዘርፉ ተዋንያን ይጠቅማል በሚል በቅርቡ በ"Construction Planning, Scheduling, Monitoring and Controlling" ዙሪያ የሚያተኩር ቅፅ አንድ መፅሐፍ ለንባብ አብቅተዋል።

ይህንኑ መፅሐፍ....
በ"ጃዕፈር መፅሐፍት መሸጫ" [ለገሃር ኖክ ነዳጅ ማደያዉ አጠገብ፤ ተወልደ ሕንፃ ስር)።
መገናኛ [ዲያስፖራ አደባባይ] "ኤደን መፅሐፍት ወይም ማራቶን ሕንፃ 6ኛ ፎቅ BeGet ኢንጅነሪንግ።
አራት ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት "ዩኒቨርሳል መፅሐፍት" መደብር።
ገርጂ [መብራት ኃይል ፋዉንቴን ሕንፃ ጎን 100ሜ ወረድ ብሎ "በለጠ መፅሐፍት መደብር።
ገርጂ [ታክሲ ተራ ፊት ለፊት] "እዉቀትን ፍለጋ" መፅሐፍት መደብሮች መፅሐፉን የሚያገኙ መሆኑን እንጠቁማለን ።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።
854 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 17:02:13 #በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ ባሣለፍነው ሣምንት ዕለት ቅዳሜ ነሐሴ 7/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በቀጥታ ስርጭት በተመደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ....

የአንሎክ ኮንስልተንሲ እና ኢንጂነሪንግ ማኔጂንግ ዳይሬክቶር፣ በIFRS ስታንዳርድ በኢትዮጲያ የተመከረላቸው የአቻ ግምት ወይም የ"Asset Valuation" ባለሞያ እና የቢዝነስ አማካሪ ከሆኑት አቶ ከፈለኝ ኃይሉ ጋር..

በመዲናችን ሰማይ ጠቀስ ሕንፃዎችን የመገንባቱ ፍላጎት ከመቼውም ጊዜ በላይ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ ፕሮጀክቶቹ ከሚጠይቁት ከፍተኛ ወጪ እና በሒደት ከሚሰጡት አገልግሎት አንፃር የአዋጭነታቸው ጉዳይ እስከምን ድረስ የተጠና እና ይበል የሚያሰኝ ነው?፤
በእነዚህ ግንባታዎች ውስጥስ ምን አይነት ኢኮኖሚያዊ ምርት እና አገልግሎቶች ይገኝባቸዋል?፤
ድምር የአገልግሎት ፋይዳቸው በወጉ ሲሰላም በእነኚህ ሕንፃዎች ውስጥ ምንስ ጠብ የሚል ነገር ይሰራል?፤
ለመሆኑ ግንባታቸው ያልተጠናቀቀቁ ፕሮጅክቶችስ ምን ይበጃቸዋል?" የሚሉ ጉዳዮችን እያነሣሣን እንደተለመደው በልክ እና በቁምነገር ተጨዋውተናል።

ይኸው ፕሮግራም ያመለጣችሁ ውድ አድማጮች የፕሮግራሙን ጥቅል ፍሬ-ነገር ዳግም ታደምጡልን ዘንድ ስናጋብዛችሁ፤ እንደወትሮው ሁሉ ደስ እያለን ነው።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።
736 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 22:42:28 #በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ በነገው ዕለተ ቅዳሜ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በቀጥታ ስርጭት በሚደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ....

በማኔጅመንት ሲስተም አሰልጣኝ፣ አማካሪ እና የተመሰከረላቸው የማኔጅመንት ጥራት ኦዲተር አቶ ታደለ ቁሜ ካሴ ጋር በሚኖረን ፕሮግራማችን ስለ ስለ ኮንስትራክሽን ፕሮጀክት ማኔጅመንት ለሁለት ሳምንታት ያስደመጥናችሁ ችግሮችና መፍትሔዎች አካል በሆነው Quality Management System መሠረታዊ ዓላማዎች፣ ጥቅሞች እና ተዛማጅ ጉዳዮች እያነሣሣን እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር እንጨዋወታለን።

ይህንኑ ተከትሎ ጠቃሚ አስተያየት አጋዥ ሐሣብ እና ተያያዥ ጥቆማዎችን ማድረስ የምትሹ አድማጮች ካላችሁ በስቱዲዮ አጭር የፅሑፍ መልዕክት መቀበያችን #6321 እንዲሁም በውሃልክ የቴሌግራም ገፃችሁ ብሎም በ09 41 43 17 00 የእጅ ስልካችን ብታደርሱን በአክብሮት የምናስተናግድ መሆናችንን ከወዲሁ እንጠቁማለን።

#የውሃልክ_ሕንፀት በውሃልክ መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።
106 viewsAselefe Bogale, 19:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 09:31:05 https://www.facebook.com/100000434685760/posts/5895510770473354/?flite=scwspnss&mibextid=192uatMs8A9iwEcc
413 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 07:51:13
Japan.
506 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 14:11:37 https://vm.tiktok.com/ZMNV7J9Ms/?k=1
641 viewsAselefe Bogale, 11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 17:26:08
ያልታደሉት የአዲስ አበባ ቅርሶች

ከሦስት ዓመት ገደማ በፊት አንድ ጥንታዊ የሆነ የአንድ አርበኛ ቤት መፍረሱን ተከትሎ፤ አፍራሹ ቅርስ መሆኑን አላውቅም ነበር አለ። ነገሩ በጊዜው ውዝግብና ክርክርን አስነስቶ በኋላ ላይ ጭራሽ ተዘነጋ። ይህም በግልጽ ቅርስ የሆኑ ግንባታዎችን ከማፍረስ የጀመረ ተግባር ቀጥሎ፣ የቅርስ ያህል ዋጋ ያላቸውና የሕዝብ የጋራ ትዝታ የተሸከሙ ግንባታዎችም እንደቀላል እየፈረሱ ይገኛሉ።

ይህም ሕንጻዎቹንና ቦታውን በገዙት በግል ባለሀብቶች የተፈጸመ ነው ቢባልም፤ የፌዴራል መንግሥት ይልቁንም የከተማ አስተዳደሩ ከተጠያቂነት የሚድኑበት እንዳይደለ እሙን ነው። የአዲስ ማለዳዋ ሊድያ ተስፋዬ ኢትዮጵያ ሆቴል አጠገብ የሚገኘው የበጎ አድራጎት ሕንጻ/ራይቲዮር ሕንጻ መፍረሱን መነሻ በማድረግ፤ የአዲስ አበባ ቅርሶችን ነገር የተለያዩ ባለሞያዎችን በማነጋገርና መዛግብትን በማጣቀስ ጉዳዩን የሐተታ ዘ ማለዳ ርዕሰ ጉዳይ አድርጋዋለች።

ለተጨማሪ ንባብ -> https://bit.ly/3JitB31
______________________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n
303 viewsAselefe Bogale, 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 15:15:51
#በአዲስ_አበባ-ጅቢቲ የባቡር መንገድ ላይ በተገነቡት አዳዲስ የመዳረሺያ ጣቢያዎች ቅፅር ግቢ የምናስተውላቸው የኪነ-ሕንፃ ስራዎች አካላዊ ቁመና ወይም የመልከ ገፅታቸው ውክልና እስከምን ድረስ ለአገራችን የቀረበ ነው?...

ለዕይታ ጥበብ ባለሞያዎች የተብራራ ምላሽ የድሮውን የባቡር ጣቢያ ምሥል ከዚሁ ጋር አያይዘናል።
483 viewsAselefe Bogale, 12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 13:50:06 #በመላው_ዓለም_የምትገኙ_ውድ_አድማጮቻችን ...

በውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን እየተዘጋጀ በኢትዮጵያውያን ቤተ-ሬዲዮ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የዓየር ሞገድ ላይ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 23/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 እስከ 3 ሰዓት በተደመጠው ውሃልክ የኮንስትራክሽን ፕሮግራማችሁ....

ከዕለቱ እንግዳችን አቶ እንዳወቅ ፈንታ ጋር ባደረግነው ክፍል ሁለት የፕሮግራም ቆይታ ከባለፈው ሳምንት የቀጠሉ በዋናነትም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አስተዳደርን የተመለከቱ ርዕሰ-ጉዳዮችን እና አዋጭ የተሰኙ የመፍትሔ ሐሣቦችን እያነሣሣን እንደተለመደው በልክ እና በቁም-ነገር ተጨዋውተናል።

#ውድ_አድማጮች... የዝግጅት ክፍላችን ውድ ግዜያቸውን ለሰጡን የዕለቱ እንግዳ ያለውን ልባዊ ምስጋና እያቀረበ፤ የፕሮግራሙን ጥቅል ፍሬ-ነገር ዳግም ታደምጡልን ዘንድ በዚሁ ገፅ ስንጋብዛችሁ ከአክብሮት ጋር ነው።

#የውሃልክ_ሕንፀት_በውሃልክ_መሠረት!
#ሕይወትን_በኮንስትራክሽን እንገንባ!
ውሃልክ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን።
489 viewsምታቸው@ጌታቸው @የዓይንዋጋ ቸኮል ልጅ, 10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ