Get Mystery Box with random crypto!

#AddisAbaba በ2014 ዓ/ም 21 ሰዎች በስራ ላይ እያሉ ከህንፃ ወድቀው ሞተዋል ! በ20 | Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700

#AddisAbaba

በ2014 ዓ/ም 21 ሰዎች በስራ ላይ እያሉ ከህንፃ ወድቀው ሞተዋል !

በ2014 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ በግንባታ ሥራ ላይ ተገቢው የደኅንነት መጠበቂያ ግብዓቶችን ለሠራተኞቻቸው ባላሟሉ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ችግር 23 ሰዎች በሥራ ላይ እያሉ ከሕንፃ ወድቀው ከፍተኛ የአካል ጉዳትና ሞት እንዳጋጠማቸው ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

ከ23ቱ ሰዎች 21 ያህሉ የሞት አደጋ የደረሰባቸው መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለጋዜጣው በሰጠው ቃል ፤ በግንባታ ሥራ ላይ ተገቢውን የደኅንነት መጠበቂያ ግብዓቶችን ለሠራተኞቻቸው በማያሟሉ የኮንስትራክሽን ድርጅቶች ላይ ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፤ ግዴታቸውን በማይወጡ ድርጅቶች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ከደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።

በሌላ በኩል በ2014 የበጀት ዓመት ከተፈቀደላቸው የግንባታ ቦታ ውጪ የሚጠቀሙና በእግረኛ መንገድ ላይ የተለያዩ የግንባታ ዕቃዎች በማስቀመጥ የእግረኛ መንገድን በማጨናነቅ አካል ጉዳተኞችን ለከፍተኛ ችግር እያጋለጡ የሚገኙ ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ፣ ከደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ጋር ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ መዘጋጀቱን ባለስልጣን መ/ቤቱ አስታውቋል።

በ2014 ዓ.ም. ከላይ ከተጠቀሱት ችግሮች ጋር በተገናኘ በ136 ድርጅቶች ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ መወሰዱን ገልጿል።

በ136 ድርጅቶቹ ላይ የግንባታ ግብዓቶችን እንዲያነሱ ከማድረግ አንስቶ ንብረታቸውን የመውረስ እንዲሁም የመጨረሻ ጽሑፍ ማስጠንቀቂያና የዕገዳ ውሳኔ የማስተላለፍ ዕርምጃዎች መወሰዳቸውን ባለስልጣን መ/ ቤቱ ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልጿል።

@tikvahethiopia