Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካ | Wuhalek Ethiopian Construction Talk Show. 0941431700

በመዲናዋ መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ የኪራይ ቤቶች መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የመሳለሚያና አካባቢው የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ይበቃል ጠመረ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ዛሬ ከሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው መርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ ባጋጠመ የሕንጻ መደርመስ አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

እንዲሁም ሰባት ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመው÷ ህብረተሰቡ ከተገነቡ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ቤቶችን ሁኔታ በማየት ለሚመለከተው አካል እንዲጠቁም አሳስበዋል።
FBC