Get Mystery Box with random crypto!

እናት ልባም ሴት እናት ስንል ወደ አይምሮዋችን ሊመጣ የሚችለ | Virtuous women💃💃let's learn

እናት ልባም ሴት



እናት ስንል ወደ አይምሮዋችን ሊመጣ የሚችለው ሩህሩህ፣ ደግ፣ ፣አዛኝ፣ካላት ለሌሎች ደራሽና ተቆራሽ፣ መጋቢ ፣ ለልጆቿ እጅጉን ተጨናቂና አሳቢ፣ ቤት እንዳይፈርስ ጥፋትን ሸፋኝ ገበናንም ደባቂ ብሎም ከማህበረሰብ ጋር ተግባቢ በአጠቃላይ የፍቅር ሴት ማለት ናት

ታዲያ እናት ማለት ከብዙ በጥቂቱ ይህችን ሴት ትመስላለች ከላይ የተዘረዘሩት ባህሪዎቿ ሙሉ ለሙሉ ማለት ይቻላል አንዲት ጠቢብ ልባም ሴት የምታደርጋቸው ነው አየሽ አንቺ ሴት ልባም ሴት ማለት "የእናትነት ባህሪን" የያዘች ሴት ማለት ናት

"እናትነት የሚገኘው በልባምነት ውስጥ ነው"

የአንቺ ልባምነት የእናትነትን ባህሪ ሊያመጣ ይችላል ታዲያ አንቺ ምን ያክል የእናትነት ባህሪ አለኝ ብለሽ ታስቢያለሽ እውነት ለሰው አዛኝ፣መጋቢ፣ለጋሽ፣ገበና ሸፋኝ… ነሽን ብዙ ጊዜ ሰው ይህ የእድሜ ጉዳይ ይመስለዋል እውነት አዎን ግን መብሰል የእድሜ ጉዳይ ብቻ አይደለም ራስን ለነገሮች ዝግጁ ማድረግም እንጂ

ዛሬ ሆነሽ የእናትነትን ባህሪ ለመላበስ ሩጪ ትጊም አንዳንድ ሴቶች ገና በወጣትነታቸው እድሜ ምናምን ሰዎች" ውይ ይህች ልጅ እንዴት ያለች እናት የሆነች ልጅ ናት " ሲል እንሰማለን ስለዚህ ለነገ ዛሬ ነውና የሚሰራው ዛሬ ላይ ራስሽን ለመልካም ነገሮች ዝግጁና የቀባይም ለመሆን እጅጉን ትጊ የሚጠቅመው ይህ ነውና

@behayluminilu
@behayluminilu