Get Mystery Box with random crypto!

Virtuous women💃💃let's learn

የቴሌግራም ቻናል አርማ womensletlearn — Virtuous women💃💃let's learn V
የቴሌግራም ቻናል አርማ womensletlearn — Virtuous women💃💃let's learn
የሰርጥ አድራሻ: @womensletlearn
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.16K
የሰርጥ መግለጫ

Let's learn girls
#be strong 💪
#be wisely 👌
#be clever😙
#be discerning😑
You r number one😘
Created date april22/2021

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 22:59:10 #መራር_እውነታዎች

#ምንም ነገር ለዘላለም አይቆይም፡፡ ችግሮችህ፣ የከበቡህ ሰዎች፣ ስራህ፣ ትዳርህ እና ግንኙነቶችህ ሁሉ ለጊዜዉ ነዉ፡፡ የሁሉም ነገር ፍፃሜ የሆነ ቀን ላይ ሲሆን ታየዋለህ፡፡ በህይወቴ ሁሉ አብረዉኝ ይኖራሉ ያልካቸዉ ነገሮች እንኳን ሳይቀሩ ሲፈረካከሹ ታያቸዋለህ።

#ለሁሉም ነገር ተራ አለዉ፡፡ ሰዉን ብትጠቅም ጊዜዉን ጠብቆ አምላክህ ይከፍልሃል፡፡ ብትጎዳም እንዲሁ። በሰፈርከዉ ማንነት ጊዜዉ ሲደርስ ትሰፈራለህ።

#ማንም ሰዉ ስላንተ አይጨነቅም፡፡ 20 ፐርሰንቱ ብቻ ስላንተ ሲጨነቁ (እነሱም የቅርብ ጓደኞችህና ቤተሰቦችህ መሆናቸዉን አትዘንጋ) 80 ፐርሰንቱ ግን ኑር አትኑር አንዳች ቅንጣት ስላንተ አያስቡም፡፡ ችግሮችህን ለነዚህ ለ 80 ፐርሰንት መናገር እራስህን ማባከን ነዉ ምክንያቱም ችግርህ ለነሱ ምናቸዉም አይደለምና! የራሳቸዉ ጉዳይ ብቻ ያሳስባቸዋልና ቆጠብ በል።

#ሰዎች በህይወትህ ይመጣሉ ደግሞም ይሄዳሉ፡፡ አንድ ቀን ለብቻህ ሰዉ በሌለበት ልትሞት ትችላለህና ሰዎችን አትደገፍ።

#ከ5-6 የልብ የምትላቸዉ ሰዎች በቀር ፌስቡክ ላይ ያሉት የጓደኛ ጋጋታ ምንም አይጠቅሙህም፡፡ ብትሞት እንኳ ቀብርህ ላይ የማይመጡ ብዙዎች መሆናቸዉን እወቅ።

#የስራ አለቃህ እንድታድግና የተሻለ ቦታ እንድትይዝ ሊመኝ ይችላል ግን መቼም እንድትበልጠዉ አይፈልግም፡፡ ምንም ሽልማትና ጭብጨባ ቢበዛልህ ከሱ እንደምትበልጥ ካሰበ አንተን ለመገፍተር ወደኋላ አይልም።

#98 ፐርሰንቱ ሰዉ መቼ እንደተወለድክ እንኳን አያዉቅም (2 ፐርሰንቱ መቼም እነማን እንደሆኑ መገመት አያቅትህም)፡፡ ካላመንከኝ ሞክረህ እየዉ!

#የዉሸት ጓደኞችህ የተሻለ ህይወት እንድትመራ በፍጹም አይፈልጉም፡፡ ነገሮች መልካም ሲሆኑ የሚሰበሰቡ ሰዎች ሊያስገርምህ አይገባም! አንድ ቀን ህልምህ 'ወለም' ብሎ ካዩ እጃቸዉን ቀስረዉ ይስቁብሃል፡፡ የዛኔ ያልሳቁብህን የልብ ጓደኞችህ አድርጋቸዉ።

#ገንዘብ ያለዉና ፀዳ ብሎ የሚመላስን ሰዉ ብዙዎች ሲያከብሩት ትመለከታለህ ፡፡ የማያዉቅህ እንኳን ቢሆን ፀዳ ካልክበት ሊያከብርህ ሲዳዳዉ ታየዋለህ።

#ለሰዎች ምክር መስጠት በጣም ቀላል ነዉ ነገር ግን ምክርን ወደተግባር መቀየር ከባዱና አስቸጋሪዉ ነገር ነዉ፡፡ አንዳንዴ ሰዉን ካለበት ማጥ ለማዉጣት ካሰብክ ከምክር በላይ የሆነ ስብዕና ሊኖርህ ይገባል፡፡

#አንድ ዉሸታም ጓደኛህ ከ 100 ጠላትህ ጋር እኩል ጥፋት ያደርሳል፡፡ ጠላቶችህን ተከታተላቸዉ ጓደኞችህን ደግሞ በጣም ተከታተላቸዉ።

#ነገሮች መልካም እንዲሆኑና እንዲሳኩ ያለ የሌለ ጥረትህን አድርገህ ሳይሳካልህ ቀርቶ ይሆናል፡፡ ይሄ ያንተ ደካማነት ሳይሆን ህይወት እንዲህ አይነት ገፅታም ስላላት ነገሩን ተቀበለዉ።

#ለመወደድ ልዩ ሰዉና ሁሉንም ሞካሪ መሆን አይጠበቅህም፡፡ እንዳንዴ ሰዉ ሁሉ ባይወድህ እንኳን ይሄ ምንም ማለት እንዳልሆነ ተረዳ፡፡

#በሰዎች መጠላትንም ቀለል አድርገህ ዉሰደዉ ምክንያቱም እንዴት እራስህን ማሳደግ እንዳለብህ ማጤን ወሳኙ ነገር ሲሆን የሰዎችን ስሜት እያዳመጥክ ከፍና ዝቅ እያልክ መኖር አይጠበቅብህም፡፡

#የራስህ አስተሳስብ ይኖርሃል፡፡ ሌሎችም እንዲሁ...ሰዎች በሀሳብህ አለመስማማታቸዉ አንተነትህ ላይ የሚያመጣዉ ነገር የለም፡፡ ሃሳብህን ለማሳመን የሰዎችን አስተሳሰብ ረጋግጠህ አትዉጣ፡፡ የሰዎችን ሃሳብ አክብር ሰዎችም ሃሳብህን እንዲያከብሩ አድርግ።

#ይቺ አለም የምትፈልግህ ጠቃሚ ነገር አንተ ጋር እንዳለ ስታምን ብቻ ነዉ፡፡ ባጠቃላይ አለም እራስ ወዳድ ናት።

#ሰዎች ስለ ደስታ አጋነዉ ሲያወሩ ትሰማ ይሆናል፡፡ በኣጭሩ ደስታ ማለት ስሜትህ ሳይሆን አእምሮህ ያለበት ሁኔታ ነዉ፡፡ ደስተኛ ሆነህ በሰዎች ልትጎዳ ትችላለህ፡፡

#ህይወት እኩል አይደለችም፡፡በሆነ ነገር ጎበዝ ብትሆን ካንተ የበለጠ በጣም ጎበዝ ሰዉ አለ...እኩልነት ዉሸት ነዉ፡ ስለዚህ በመኖርህ ብቻ ተደሰት፡፡
@womensletlearn
225 views19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:53:56 ጋዜጠኘዋ ጠየቀቻት ፊልም ላይ ብዙም አትታዪም ምክንያቱ ምንድ ነው?
ሳያትም መለሰች፦ ፊልሞቻችን ሴትን ልጅ አጭር ቀሚስ ከማስለበስ ና ውበቷን ከማስተዋወቅ ያለፈ ቦታ የላቸውም እኔ ደሞ ሴት ቆንጆ ፀጉሯ ረጅም ተቀባብታ ምተኛ ሀብታም የሚያፈቅራት ደሀን ምታፈቅር ብቻ ነች ብዬ አላምንም ጠንካራ ፈተናዎቿን በድል ምትወጣ ለሌሎች ምሳሌ ምትሆን ሊፃፍላት ሊሰራላት ሚገባት በሞላችበት ሀገር ቆንጆ ብቻ ሆኖ መተወኑን ስላልፈለኩ ነው የስሪልኝ ጥያቄዎችን ማልቀበለው።

@womensleearn
126 views17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 17:29:53 #በህይወት ሰልፍ ውስጥ ሳለህ ልብ ልትላቸው የሚገቡ እነኚህን 19 ነጥቦች በአጽንኦት አንብቧቸው!

#ያለፈ ነገር እንደማይቀየር አትርሳ!

ላወቀበት ሰው ግን ያለፈው ለወደፊቱ የራሱ የሆነ ትምህርት አለው፣
ካለፈው ነገርህ ተማር እንጅ በፍፁም አታማርር፣
ማማረር ነገህን በጎ አያደርገውም።

#የሰዎች ሃሳብ የአንተን ማንነት አይገልፅም!

ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው፣
መልካም አድርግ ሌላውን እርሳው የሁሉም ሰው የህይወት መንገድ (ጉዞ) ይለያያል ፣
ለሁሉም ጊዜ አለውና ጊዜው በደረሰ ሰው ሁኔታ አትቅና።

#መኪና ገዛ ብለህ "እኔስ" አትበል!

ጊዜህ ሲደርስ መኪናዎች ወይም ‘አውሮፕላን’ ትገዛለህ ፣ ያውም ለመኖር አስፈላጊ ከሆነ ፣ ደግሞስ እንዴት እንደገዛው የት ታውቃለህ?
እርሱን ተወውና በራስህ ላይ አተኩር ፣ ያለህ ነገር በቂ ነው።

#ለሰዎች ለደስታቸው እንጂ ለሀዘናቸው መንስዔ አትሁን!

በሰዎች ደስታ→ደስ ይበልህ!
ለሰዎች→ክፉ አትመኝ፣
በሃዘናቸውም→አብረህ እዘን፣
ሰዎች ሲያዝኑ→አትደሰት፣
ሰው ከሆንክ→የሰው ነገር ይሰማህ፣
ይህ ማለት ግን ተንኮል እየሰሩ ከሚደሰቱ ሰዎች ጋር ተደሰት ማለት አይደለም።
ሰው እያስከፋ ብሎም እየገደለ የሚደሰት አለ ፣ አንተ ከተጎዳው ሰው ጋ ሁን፣ አስተውል።

#በጊዜ ስራ እንጂ ጊዜ ባንተ ላይ አይስራ!

ጊዜ የማይፈውሰውና የማይቀይረው ነገር የለም።
አንተንም ጊዜውይ ቀይርህ ዘንድ ፍቀድለት፣
በተሰጠህ ጊዜ ለመልካም ነገር ሱሰኛ ሁን።

#መክሊትህን ፈልግ!

ውስጥህ የሚችለውና የሚያምንበት ተሰጥኦ ምን አለህ?
ምን አይነት ስራ መስራት ትችላለህ?
አስተውል ጓደኛህን አትመልከት ፣ ትለያያላችሁና።
አለማችን በትምህርት ብቻ ወይም በጥበባት ብቻ ወይም በተወሰኑ ዘርፎች አይደለም እየኖረች ያለችው።
በጣም ብዙ ነገሮች ናቸው እየደገፏት ያቆሟት።
አንተም ጥቂትም ብትሆን ያለህን ችሎታ ፈልገውና አውጣው።
ቁፋሮ ነው ወይስ ቾክ ይዞ ማስተማር ነው ወይስ መምከር መገሰፅ ነው?
ቆንጆ ሽሮ ወጥ እየሰሩ መሸጥ ነው?፣
የድንጋይ ቅርፅ (ኮብልስቶን) እየሰሩ መኖር ነው?
ምንድነው ???
እባክህ ፈልገው አጎልብተው ጀምረው፣
ምን ይሻለኛል ?" እያልክ ጊዜህ እንዳያልቅ።
በእርግጥ ጊዜህ ሳይሆን አንተ ነህ የምታልቀው።

#መልካም ነገር ሁሉ ከፈጣሪ መጥፎ ነገር ሁሉ ደግሞ ከሰይጣን እንዳልሆነ አስተውል!"

ፈጣሪ መጥፎን ወደ መልካም የመቀየር ብቃት አለው።
ሰይጣንም ያጠፋህ ዘንድ መልካም የሚመስል ነገር ሊያዘጋጅልህ ይችላል።
መልካም ማሰብና መልካም መሆን መልካም ነገር እንዲገጥምህ ማመቻቸት ነው፣
መጥፎነት ከአንተ ይራቅ፣
ለአንተም ሆነ ለሰዎች ጉዳት እንጅ ጥቅም የለውም።

#ሰው_የዘራውን_ያጭዳል" የሚለውን አባባል አስታውስ፣

የሰራኸውና የምትሰራው ነገር የሆነ ጊዜ ላይ ዞሮ ያገኝሃል፣
መጥፎ ከሰራህ እንደስራህ፣ መልካም ከሰራህም እንደዚያው ይገጥምሃል።
ክፉ ነገር እየዘራህ መልካም ነገር አትጠብቅ ፣ ራስህን አትሸውድ።
ጤፍ ዘርተህ ባቄላ አትጠብቅ፣ ጤፍ የዘራ ገበሬ ጤፍ እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አንተም የዘራኸውን በእጥፍ ታጭዳለህ።

#ለራስህ ስትል መልካም ሁን፣ በጎውንም አስብ!

ለራስ ማሰብ ማስተዋል እንጅ ራስ ወዳድነት አይደለም።
ራሱን የማይወድ ሰው ሌላውን አይወድም።

#በማንም ላይ አትፍረድ!

የመፍረድ ሃላፊነት በፍፁም የለህም።
ፍርድ የፈጣሪ ነው።
ለመፍረድ እንከን አልባ መሆን ያስፈልጋል፣
ፍጥረት ሁሉ ፍጥረት በመሆኑ ብቻ እንከን አለበት ፣ ጎደሎ አለበት።
የተሻለ ሀሳብ አለኝ ብለህ ካሰብክና ከቻልክ ምከር ካልሆነ
ዝም በል።

#መልካም ጓደኛ ከፈጣሪ የሚሰጥ ጸጋ መሆኑን አትርሳ!"

የጓደኛህን ስሜት ለመራዳት ሞክር!"
መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት፣
አበረታታው፣
እንደማይጠቅም አትንገረው፣
ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን፣
ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ አትሁን።

#መልካም ጓደኛ ሁን!

መልካም ጓደኛ፦ የማይቀና አሳቢና መካሪ ፣ ከእኔ ይልቅ ለአንተ የሚል ካለህ አንተ ተባርከሃል ታድለሃል።
ከሌለህ ደግሞ አንተ ራስህ መልካም በመሆን ጀምር ፣ ባህሪህንና ስራህን አይተው ይመጣሉ።
ነገር ግን ያለምክንያት ከሄድክ በምክንያት አትምጣ።
በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ በሕይወትህ ውስጥ ጉዳት እንጂ ጥቅም የሌላቸው ሰዎች በራሳቸው ሰዓት ከህይወትህ ሲወጡ እጅግ መታደል ነው።

#ካጓጉል ሀሳብና ጭንቀት ራስህን ጠብቅ!

ያለ መጠን ማሰብ ጭንቀትንና፣ ሀዘንን ያስከትላል።
ከአቅምህ ከምትችለው በላይ አታስብ፣
መመለስ በማትችለው ነገር ላይ አትወጠር፣
የተመለሱ ነገሮችህ ላይ ትኩረት አታድርግ፣
አንዳንድ መልሶች በድጋሚ ጥያቄወች ሆነው እንደሚመጡ አትዘንጋ።
ባልገባን ሳይሆን በገባን ነገር ላይ እናተኩር።

#ደግነት አይለይህ!

ደግነት ዋጋ አያስከፍልም ነፃ ነው፣
"ያስከፍላል" ብለህ ካሰብክም ምላሹ እጥፍ እንደሚሆንልህ አትዘንጋ።
እናም ዘወትር ደግ ሁን፣
ደግ ሆነው የተጎዱ የሉም ፣ ቢኖሩም ከጉዳታቸው ይልቅ በረከታቸውና ሰላማቸው ልክ የለውም።

#ደስታህንና ሰላምህን ካንተ ዘንድ አኑራቸው!

ደስታህንና ሰላምህን የሆነ ሰው ወይም ነገር ላይ አታስቀምጥ!"
ያነገር ወይም ሰው ከአጠገብህ ሲርቅ ወይም ሲጠፋ ደስታህም አብሮ ይጠፋል።
ደስታና ሰላም በአንተ ውስጥ ናቸው።
በራስህ በአፈጣጠርህ→ደስ ይበልህ፣
ውለህ በመግባትህ→ደስ ይበልህ፣
በአለህ ትንሽ ነገር→ደስ ይበልህ።

#ፍቅርን ፈልጋት!

ለፍቅር ለመውደድ እንጅ ለጥላቻ ለዛቻ ለምቀኝነት ጊዜ አይኑርህ።
በመውደድ የተጠመደ ሰው ለመጥላት ጊዜ የለውም።

#ዘመንህን ከርኩሰት ጠብቀው!

እድሜህን በተመለከተ፣ የፈጣሪ ፈቃድ ከሆነ ካለፈው ከተቃጠለው ጊዜህ ይልቅ ወደፊት የምትኖረው ብዙ ነው።
ዋናው ደግሞ የኖርክበት የእድሜ ብዛት ሳይሆን በኖርክበት ዘመን ያሳየኸው መልካምነትና የሰራኸው ደግነት ነው።

#መኖርህ ማንንም ካልጠቀመ መሞትህ ማንንም አይጎዳም የሚለውን አባባል አስታውስ!

የየኖሩበት እድሜ ትንሹም ቢሆን በቂ ነው ይባላል።
የማቱሳላ እድሜው እንጅ የሰራው ስራ አይታወቅም፣
"ኖሮ ሞተ" ብቻ ከመባል ፈጣሪ አምላክ ይጠብቅህ፣
መኖርህ ሰዎችን ካልጠቀመ መሞትህ ላይጎዳቸው ይችላል፣
መኖር ማለት መጥቀም መጠቃቀም ነው።

#ከማማረር ማመስገንን ልመድ!

የምናማርረው የተሰጠንንና የሆነልንን ’ረስተን፣ ያልጎደለን ነገር ላይ "ጎደለን" ብለን በጥያቄ ስለምንሞላ ነው፣
ባለው ነገር አመስጋኝ የሆነ ይጨመርለታል።
በማማረር መባረክ የለም።
ሰላምና ጤና፣ ከመልካም አስተሳሰብና በጎ ህሊና ጋር ምንጊዜም ከዘመንህ አይለይ።
ለውጥ ከራስ ይጀመራል! እናም አሁኑኑ መለወጥን ጀምር።

@womensletlearn
አስተማሪ ሆኖ ካገኙት ሼርርርር
527 views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 19:13:01 አንዳንዴ ህይወት የማትችለውን እንድትጋፈጥ ታደርግሀለች
#ትልቁ__ፈተና ግን

ትልቁ ፈተና መሞት አይደለም አለመኖር እንጂ!

ትልቁ ፈተና መፀለይ አይደለም አለማመን እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማፍቀር አይደለም አለመፅናት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መደመር አይደለም አለማካፈል እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማጣት አይደለም ተስፋ መቁረጥ እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማግባት አይደለም አለመግባባት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መደሰት አይደለም ደስታን አለመቆጣጠር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማሰብ አይደለም የሚያስቡትን አለማጤን እንጂ!

ትልቁ ፈተና ችግር አይደለም ትዕግስት ማጣት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማዘን አይደለም ማማረር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ሃይማኖተኛ መሆን አይደለም መንፈሳዊ መሆን እንጂ!

ትልቁ ፈተና ስልጣን አይደለም አጠቃቀሙን አለማወቅ እንጂ!

ትልቁ ፈተና እውቀት አይደለም እያወቁ መሳሳት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ስደት አይደለም የተሰደዱለትን አላማ መርሳት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ወደራስ ማየት አይደለም ዘረኝነት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ስኬታማ መሆን አይደለም ራዕዩን መርሳት እንጂ!

ትልቁ ፈተና የፀለዩትን ማግኘት አይደለም ያገኙትን ማማረር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ዝምተኛ መሆን መቻል አይደለም በዝምታ ውስጥ መረጋጋት ማጣት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ቤተክርስትያን ወይም መስጊድ መሄድ አይደለም የሚሄዱበት ምክንያት መዛባት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ገንዘብ አይደለም በገንዘቡ የምናደርግበትን ነገር አለማስተዋል እንጂ!

ትልቁ ፈተና ልጅ መውለድ አይደለም ልጅን መቅረፅ እንጂ!

ትልቁ ፈተና ዜግነት መቀየር አይደለም ማንነትን መርሳት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መጣላት አይደለም ለበቀል ማቀድ እንጂ!

ትልቁ ፈተና ይቅርታ ማድረግ አይደለም ይቅርታውን ማመን እንጂ!

ትልቁ ፈተና መለያየት አይደለም እንደሚገናኙ አለማሰብ
እንጂ!

ትልቁ ፈተና ፈጣሪን ማሰብ አይደለም ፈጣሪን ማመን እንጂ!

ትልቁ ፈተና መማታት አይደለም ቅፉ ቃል መናገር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ተሰሚነትን መጨመር አይደለም ለሚሰሙን መልካም አርአያ መሆን እንጂ!

ትልቁ ፈተና አብሮ ስራ መጀመር አይደለም አብሮ ስራውን መፈፀም እንጂ!

ትልቁ ፈተና አለማቀድ አይደለም ለማቀድ አለመሻት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ሞክሮ መበላሸት አይደለም ድጋሚ አለመሞከር እንጂ!

ትልቁ ፈተና ጓደኛ ማጣት አይደለም ወዳጅ ማግኘት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ማሸነፍ መቻል አይደለም አሸንፎ መፅናት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ተመስገን ማለት አይደለም አመስግኖ መርካት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መደንገጥ አይደለም ግራ መጋባት እንጂ!

ትልቁ ፈተና መሸነፍ አይደለም ተሸንፎ መቅረት እንጂ!

ትልቁ ፈተና እንደ እዮብ መውደቅ አይደለም እንደ እዮብ መፅናት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ከልብ ማልቀስ አይደለም ተሰብሮ መቅረት እንጂ!

ትልቁ ፈተና ሃገርን መውደድ አይደለም ሃገርን መስበክ እንጂ!

ትልቁ ፈተና ሰው ሆኖ መፈጠር አይደለም ሰው ሆኖ መኖር እንጂ!
ሟርርርር
@womensletlearn
314 views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 06:16:21 አንድ አንዱ ዛሬ የሚያስደስተው ሲያገኝ ትላንት መስዋእት የሆነለትን ይረሳል

ቃል የእምነት እዳ ነው ፍቅርም ልክ እንደ ማህተም ነው ከቃልም በላይ እውነት እና እምነት ነው፡፡
አትበሳጭ ብስጭት የስይጣን ነውና
አትዘን ''አምላክ ያልፈቀደው አይሆንምና
አትቸኩል ላንተ ያለው አይቀርምና
ፍቅርማለት በሀብት ብዛት ያልታጠረች በድህነት ወሰን ያልተገደበች በወርቅ ሚዛንላይ ያልተቀመጠች በግለስቡ ማንነት ብቻ የምትገለፅ ጥበብ ነች።

ሴት ልጅ የማይቻለውን ነገር አድርግልኝ ብላ አትጠይቅህም ነገር ግን አንት ለእህትህ የምትመኘውን አይነት ወንድ ሁንላት ይሄ ብቻ በቂዋ ነው፡፡

ፍቅር እንኳዋን ርቀት መከራንም ይታግሳል
ዓለም ሙሉ ጎድቶህ አንድ ስው ሊያስደስትህ ይችላል ያው ሰው አንድ ቀን ይጎዳህና ዓለም ሙሉ አንተን ማስደስት ያቅተዋል
ከድብቅ ጓደኛ ግልፅ ጠላት ይሻላል

ወዳጄ ሆይ!

ልብህ ለፍቅር
ህሊናህን ለእውነት
ነብስህን ለፀሎት አድርገው!@womensletlearn
@womensletlearn
@womensletlearn

ሟርርርር
860 viewsedited  03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 18:54:42 ስለ #እረኛዬ ድራማ በጥቂቱ... በደንብ አንብቡት!

እረኛው ወንድ ነው እርሱም:- #ኢየሱስ ነው!

በእረኛዋ ውስጥ እረኛችሁን ኢየሱስን እዩት!!!

#እረኛዬ ድራማ ድንቅ አገርኛ ፊልም ነው! ድራማው 4 ምዕራፎች 48 ክፍሎች ነበሩት! "እናናን" ገድሎ ይጨርሳል ብዬ አላሰብኩም! እረኛዬ ድራማ በእረኛዋ ሞት መደምደሙ ከለመድነው መንገድ ወጣ ይላል!

ደራሲዎቹ እናናን እና ዳዊትን፣ መንግሥቱን እና የጌጤን እናት አጋብተው፣ ወግዬን እና ሽፈራውን አዋደው፣ የሰፈሩን ሰው አያይዘው ... ቢጨርሱ ማናችንም አንቀየማቸውም! እነርሱ ግን ሌላ እይታ ሰጥተውን ተሰናበቱን!

ይህኛው እይታ ድራማውን የበለጠ ትክክል ያደርገዋል! እረኛዬ ተብሎ እረኛዋ ሰብሳቢ ብቻ ብትሆን አይገርምም! የቱንም ያህል ቢያስለቅሰን የእረኛዋ መሞት ትክክለኛ ነው! የተሟላ ትርጉም የሰጠው መሞቷ ነው!

እረኛችን ኢየሱስ ያደረገው ይህን ነበረ! የቱንም ያህል ብናዝንለት መሞቱ ነበረ ትክክል! ደራሲዎቹ የእናና ሞት ላይ እንደ ፈረዱ አብም ኢየሱስ ላይ ፈርዷል! ትክክለኛ ፍርድ ነበረ!

እረኛዋ በሞቷ ተስማምታ ነበረ! እረኛችን ኢየሱስም ለእኛ ለመሞት ፈቃዱ ነበረ!

“መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል።” — ዮሐንስ 10፥11

ደግሞ ተዘራን እዩት ሞያተኛ እረኛ ነው፤ በጎቹን ለጥቅም ለመሸጥ አልከበደውም ነበረ!

“ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።” — ዮሐንስ 10፥13

እረኛዋ ከበጎቿ እንዲታረድ አትፈቅድም ነበረ! ትንሿን በግ ተዘራ ገደል እንዳይጥል እንዴት እንደለመነችው አስታወሳችሁ? ሲጥላት ገደል መግባቷስ? ጥጋቡ ያለችውን በግ አጋልጣ ላለመስጠት ምክንያቷ ምን ነበረ? ያርዱታል! ኢየሱስ እንዲህ ነው!

እረኛዋ በሞቷ አንድ እንዳደረገቻቸው ኢየሱስም በሞቱ አንድ አድርጎናል!

“ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ።” — ዮሐንስ 10፥16

የአባባ በቃሉ ቤተሰብ አይሁዳውያን ይወክላል!
ጌጤ ከዚህ በረት አልነበረችም፥ እኛን አሕዛብን ትወክላለች! መጥታ አሮጊቷን መሪ ነው የሆነችው! አሁን የእግዚአብሔር ምስጢር በቤተክርስቲያን በኩል ነው እየተገለጠ ያለው!

ለእናና የተቀኙት ሙሾ፦

"ያንቺ ደም ዝም አይበል ከቶ እንዳይቀር ባክኖ፣
ይጠበው መንደሩን አስታራቂ ሆኖ"

እስኪ ግጥሙን በወንድ ጾታ አስቡት!?

ያንተ ደም ዝም አይበል ከቶ እንዳይቀር ባክኖ፣
ይጠበው መንደሩን አስታራቂ ሆኖ

የኢየሱስ ደም ነው ማጠብ የሚችለው!

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።” — 1ኛ ዮሐንስ 1፥7

የኢየሱስ ደም ነው የእርቅ መሠረት የሆነን! ከእግዚአብሔርም ጋር፥ እርስበርሳችንም!

“ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቍጣው እንድናለን።” — ሮሜ 5፥9

“አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።” — ኤፌሶን 2፥13

በአንድ ወቅት ኢየሱስ በጾታ ሴት ሆኖ መጥቶ ቢሆን? በቀላሉ እንቀበለው ይሆን? ብለን አስበን እናውቃለን! አያችሁ የጌታ እናት ማርያምን የወደድናት በእናት በኩል ስለሰበኩን ነው! እናቶቻችንን ስለምንወድ!

እስኪ #በእረኛዋ #ውስጥ #እረኛችሁን ኢየሱስን #እዩት!!!

መልካም ቀን

--ፀሃፊ #በርናባስ #ዘመነ Barnabas Zemene
@womensletlearn
583 views15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 07:34:41 ጭር ያለ ቦታ እንገናኝ

ብዙ ወጣቶች በወሲባዊ ሃጢያት #ለመውደቃቸው እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት ከፍቅር ጓደኛቸው ወይም ከተቃራኒ ፆታ ጓደኛቸው ጋር ሰው የሌለበት ፣ ጭር ያለ ፣ ጨለም ያለ ቦታ መገናኘታቸው እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡

"ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።"
              (የዮሐንስ ወንጌል 3:19)

ጥንዶቹ ሳያስተውሉ አልያም ደግሞ ከሁለቱ አንዳቸው በሌላኛቸው ተታለው ወይም #ተገፍተው ሊሆን ይችላል ጭር ወዳለ ቦታ የሚሄዱት ፡፡

መፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ ሰው እጅግ አፀያፊና ህይወትን ከሚያመሰቃቅል ከዝሙት ሃጥያት ማምለጥ የሚችለው #በመሸሽ ብቻ እንደሆነ ይናገራል ፡፡

ስለዚህ የእጮኝነት ጎዳና ውስጥ ለመግባት ብቁ የሆናችሁ ወጣቶች ከእጮኛችሁ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የግድ ነው ነገር ግን ጊዜ ለማሳለፍ ጨለማንና ጭር ያለ ቦታን መምረጥ የለባችሁም ፡፡ እንደ ካፌ እና ሰዎች የሚንቀሳቀሱባቸው መናፈሻዎችን መጠቀም ይገባችኋል ።

           SHARE    SHARE 


@biblicalmarriage
@biblicalmarriage
438 views04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 17:52:39 አይ የጴንጤ ወንድ መከራ

Me - ሀይ
Her - ሰላም
Me - ሰላም ነሽ?
Her - ሰላሜ እየሱስ ነው!
Me - እውነት ነው። ጠፍተሻል ሰሞኑን ደግሞ
Her - አልጠፋሁም፤ ከማይጠፋ ዘር ነኝ!
Me - ልክ ነው እሱስ። እና ምን አዲስ ነገር አለ?
Her - ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም!
Me - ሃሃ...እኔ የምልሽ ቁርስ በልተሻል?
Her - ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም!
Me - ደግሞ የፖሰትሽውን ፎቶ አየሁት። በጣም ውብ ነሽ።
Her - ውበት ሐሰት ነው፣ ደምግባትም ከንቱ ነው!
Me - አይደል? የት ሰፈር ነሽ ግን? አድራሻሽን እኮ አልነገርሺኝም?
Her - አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው!
Me - ሃሃ...ኧረ የመኖሪያ አድራሻሽን ነው ያልኩሽ!
Her - "መኖሪያዬ ጌታ ነው" የሚለውን መዝሙር ጋብዤሀለሁ
Me - ስለመጋበዝ ካነሳሽ አይቀር ለምን አንድ ቀን አልጋብዝሽም ተገናኝተን?
Her - ውይ በጣም አመሰግናለሁ! ጌታ ይባርክህ! ግን መጀመሪያ እኔ ነኝ የምጋብዝህ!
Me - እውነትሽን ነው? በጣምም በደስታ ነዋ!
Her - ከፊታችን እሮብ ከስራ መውጫ ሰአት ላይ ይመችሀል?
Me - አዎን በደምብ [የትም ይመቸኛል! ]
Her - ጥሩ! "ኤልዛቤል ትፈጥፈጥ ኢንተርናሽናል ቸርች" የነፃ መውጣት ፕሮግራም አለ እዛ ጋብዤሀለሁ!
Me - ተባረኪ ! እና ከዛ ስንወጣ እራት አብረን እንበላለን በቃ እንደውም!
Her- ውይ አልችልም! ከዛ ስወጣ የአዳር ፕሮግራም አለኝ። ባይሆን እራት በምትጋብዘኝ ብር "እጮኝነት እና ትዳር" የሚለውን መፅሐፍ ግዛልኝ።
Me - በደስታ! ነገውኑ ገዝቼ አቀብልሻለሁ!
Her - ውይ ነገ አልችልም!
Me - እና መቼ ተገናኝተን ላቀብልሽ?
Her - ኧረ አትቸገር ቸርች ዘበኛው ጋር አስቀምጥልኝ። ሲመቸኝ ሄጄ እወስደዋለሁ።
Me - እሺ ካልሽ ምን ይደረጋል!
Her - በቃ አሁን ከSocial media online ወጥቼ ወደመንፈሳዊው አለም online ልገባ ነው!
Me - እሺ ውዴ ደህና እደሪ! ከእኔ ጋር ትንሽ ብትሆኚ ደስ ይለኝ ነበር።
Here - የጌታ ፀጋ ከአንተ ጋር ይሁን። ደህና ሁን በጌታ የተወደድክ ወንድሜ!

አስበው ከዚህ ሁሉ ጥረት በኋላ "ወንድሜ" ስትልህ የሚሰማህን የስሜት breakdown! ጴንጤ ወንዶች ተሰብስበን የአብያተክርስቲያናት ቢሮ በር ላይ ሄደን እየተንከባለልን "ኧረ ጆ ባይደን ኡኡኡኡኡ" I mean "ኧረ ፃድቁ አብዶ ኡኡኡኡኡኡ"ብለን እንጩህ እንዴ? ወይስ "ዳሪኝ ኳይኝ ሸንኮሬ" የሚለውን ዘፈን "ዳረኝ ኳለኝ ፓስተሬ" ብለን የመዝሙር ከቨር እንስራለት?
"ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ ፥ ቆመን ስንቀር አይገድህምን
From #face book
@womensletlearn
@womensletlearn
1.3K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ