Get Mystery Box with random crypto!

የወደድከው ሁሉ አይጠቅምህም! ፨፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨፨ የህይወት ትምህርት ግሩም | Virtuous women💃💃let's learn

የወደድከው ሁሉ አይጠቅምህም!
፨፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨፨
የህይወት ትምህርት ግሩም ነው። አንዳንዴ አንድን ሰው ብትወደውም ምርጫህ ግን መለያየት ይሆናል፤ አንድን ሰው ብትናፍቀውም ከህይወትህ ስለወጣ ግን ደስተኛ ትሆናለህ፤ ትልቁን ስፍራ ብትሰጠውም ከእርሱ መራቅን ትመርጣለህ፤ አክባሪው፣ ወዳጁ ብትሆንም ቅርበቱን የማትፈልግበት ጊዜ ይኖራል። ይበልጥ የሚጠቅምህን ለማስቀደም የምትወደውን ትተዋለህ፤ የሚያስፈልግህን ለማግኘት የምትፈልገውን ትጥላለህ፤ መንገድህን ለማጥራት ከስሜትህ በላይ ታስባለህ፤ ለእራስህ ትጠነቀቃለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ የፈለከው ሁሉ ትክክለኛ ምርጫህ የማይሆንበት ጊዜ አለ። ፍላጎት ሌላ ምርጫ ሌላ ነው። ምርጫህ የምትፈልገውን፣ የወደድከውን፣ ልብህ የደነገጠለትን ሳይሆን የሚጠቅምህን፣ የሚበጅህንና የሚያስፈልግህን ነው። በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን ቅድሚያ የምትሰጠው ነገር ይኖራል። አንድን ሰው ከእራስህ በላይ ስለወደድከው ብቻ የእራስህ ልታደርገው አትችልም። ቀዳሚው ያንተ ህልውና ነው፤ ዋናው ጉዳይ የፍቅርህ ቅቡልነት ነው። ምንም እንኳን አንድን ሰው ከልብህ ብትናፍቀው፣ ብታስብለት፣ ብትሳሳለት የህይወት አጋርህ ስላልሆነ ደስተኛ መትሆንበት ጊዜ አለ። ምክንያቱም ያንተ ናፍቆትና ስስት የሰውየውን ማንነት የመቀየር ደረጃ ላይ ስላልደረሰ፣ ከናፍቆቱና ከሃሳቡ በላይ አብረሀው መሆንህ አብዝቶ ስለሚጎዳህ።

አዎ! የወደድከው ሁሉ አይጠቅምህም፤ የተመኘሀው ሁሉ አያሳድግህም፤ የምትለምነው ሁሉ አያሳልፍህም። በስሜትህ ልክ ብትወደውም፣ በግንዛቤህ አቅም ትጥለዋለህ። የወደዱትን ስራ መስራት ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ካመዘነና በህይወታችን ለውጥ ካላመጣ ምንም ዋጋ የለውም። ከውሳኔህ በፊት ስሜትህን አስተካክል። በስሜት የተጀመረ ህይወት በስሜት አይገፋም። ምርጫና ውሳኔህን ከጥቅምህ አንፃር ቃኛቸው። ብትወደውም ካልጠቀመህ የመተው አቅመን ተላበስ፤ ቢናፍቅህም ባለማግኘትህ ደስተኛ ከሆንክ ይቅርብህ። ከቻልክ የወደድከው እንዲጠቅምህ አድርግ ካልሆነ ግን በፍቅር ሳቢያ ከሚመጣብህ ጥቃት እራስህን ተከላከል፤ አንተ ከኖርክ ዳግም የሚጠቅምህን መውደድ ትችላለህና በውዴታ ፍቅርህን ለደህንነትህ ብለህ መሱዓት አድርገው።
ውብ ምሽት ይሁንልን!
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel