አይ የጴንጤ ወንድ መከራ Me - ሀይ Her - ሰላም Me - ሰላም ነሽ? Her - ሰላሜ እየሱስ ነው! Me - እውነት ነው። ጠፍተሻል ሰሞኑን ደግሞ Her - አልጠፋሁም፤ ከማይጠፋ ዘር ነኝ! Me - ልክ ነው እሱስ። እና ምን አዲስ ነገር አለ? Her - ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም! Me - ሃሃ...እኔ የምልሽ ቁርስ በልተሻል? Her - ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም! Me - ደግሞ የፖሰትሽውን ፎቶ አየሁት። በጣም ውብ ነሽ። Her - ውበት ሐሰት ነው፣ ደምግባትም ከንቱ ነው! Me - አይደል? የት ሰፈር ነሽ ግን? አድራሻሽን እኮ አልነገርሺኝም? Her - አድራሻዬ መስቀሉ ስር ነው! Me - ሃሃ...ኧረ የመኖሪያ አድራሻሽን ነው ያልኩሽ! Her - "መኖሪያዬ ጌታ ነው" የሚለውን መዝሙር ጋብዤሀለሁ Me - ስለመጋበዝ ካነሳሽ አይቀር ለምን አንድ ቀን አልጋብዝሽም ተገናኝተን? Her - ውይ በጣም አመሰግናለሁ! ጌታ ይባርክህ! ግን መጀመሪያ እኔ ነኝ የምጋብዝህ! Me - እውነትሽን ነው? በጣምም በደስታ ነዋ! Her - ከፊታችን እሮብ ከስራ መውጫ ሰአት ላይ ይመችሀል? Me - አዎን በደምብ [የትም ይመቸኛል! ] Her - ጥሩ! "ኤልዛቤል ትፈጥፈጥ ኢንተርናሽናል ቸርች" የነፃ መውጣት ፕሮግራም አለ እዛ ጋብዤሀለሁ! Me - ተባረኪ ! እና ከዛ ስንወጣ እራት አብረን እንበላለን በቃ እንደውም! Her- ውይ አልችልም! ከዛ ስወጣ የአዳር ፕሮግራም አለኝ። ባይሆን እራት በምትጋብዘኝ ብር "እጮኝነት እና ትዳር" የሚለውን መፅሐፍ ግዛልኝ። Me - በደስታ! ነገውኑ ገዝቼ አቀብልሻለሁ! Her - ውይ ነገ አልችልም! Me - እና መቼ ተገናኝተን ላቀብልሽ? Her - ኧረ አትቸገር ቸርች ዘበኛው ጋር አስቀምጥልኝ። ሲመቸኝ ሄጄ እወስደዋለሁ። Me - እሺ ካልሽ ምን ይደረጋል! Her - በቃ አሁን ከSocial media online ወጥቼ ወደመንፈሳዊው አለም online ልገባ ነው! Me - እሺ ውዴ ደህና እደሪ! ከእኔ ጋር ትንሽ ብትሆኚ ደስ ይለኝ ነበር። Here - የጌታ ፀጋ ከአንተ ጋር ይሁን። ደህና ሁን በጌታ የተወደድክ ወንድሜ! አስበው ከዚህ ሁሉ ጥረት በኋላ "ወንድሜ" ስትልህ የሚሰማህን የስሜት breakdown! ጴንጤ ወንዶች ተሰብስበን የአብያተክርስቲያናት ቢሮ በር ላይ ሄደን እየተንከባለልን "ኧረ ጆ ባይደን ኡኡኡኡኡ" I mean "ኧረ ፃድቁ አብዶ ኡኡኡኡኡኡ"ብለን እንጩህ እንዴ? ወይስ "ዳሪኝ ኳይኝ ሸንኮሬ" የሚለውን ዘፈን "ዳረኝ ኳለኝ ፓስተሬ" ብለን የመዝሙር ከቨር እንስራለት? "ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ ፥ ቆመን ስንቀር አይገድህምን From #face book @womensletlearn @womensletlearn 1.3K views14:52