Get Mystery Box with random crypto!

Wollo University

የቴሌግራም ቻናል አርማ wollouniversity13 — Wollo University W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wollouniversity13 — Wollo University
የሰርጥ አድራሻ: @wollouniversity13
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.42K
የሰርጥ መግለጫ

This_is_an_official_Channel_of_Wollo _university.
#እንኳን በሰላም ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ መጣችሁ!!
የፍቅር እና የጥበብ ዩኒቨርሲቲ
University of Love and Wisdom!
#WOLLO_UNIVERSITY
#For_More_Info
👇
@Jsktybh
@Zigo77
#For_comment
👇
@wollouniversitycontactbot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 12:42:43 ውድ ተማሪዎች !!!
በአሁኑ ስዓት በግቢያችን ውስጥ ትምህርታችሁን እየተከታተላችሁ የምትገኙ ተማሪዎች በሙሉ እንደሚታወቀው ሃገራዊ ችግሩን ምክኒያት በማድረግ ውስጣችሁ እንደተረበሸ እንደሆነ በተማሪዎች ህብረት ቢሮ መጣችሁ ማመልከታችሁ ይታወቃል።
ስለሆነም ተማሪዎች ህብረት ጥያቄያችሁን ለሚመለከተው አካል አቅርቧል።

ስለዚህ ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ስዓት ስለጉዳዩ ውይይት እያደረገ በመሆኑ በአሁኑ ስዓት ግን ከተለያዩ ውዝግቦች ራሳችሁን አግላችሁ ተረጋግታችሁ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉና አስፈላጊ በሚሆን ስዓት ዩኒቨርስቲው ውሳኔውን ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ እየወጣችሁ ያላችሁ የአንደኛ አመት መደበኛ ተማሪዎች ግን ካለአግባብ ወጪና እንግልት ተቆጥባችሁ በዝግታ አጣራታችሁ ጉዞ እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ስለዩኒቨርስቲያችን አዲስ ነገር
መልሰን እናሳውቃለን።

የተማ/ህብ/ፅ/ቤት

@wollouniversity12
@wollouniversity12
2.1K views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 16:45:19
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ

በ25/09/2014 ዓ.ም አጠቃላይ ገለፃ( orentation) ስለሚሰጥ ሁሉም አንደኛ ዓመት ተማሪዎች
ደሴ ካምፓስ የምትገኙ በምግብ ቤት አዳራሽ
ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምትገኙ በአዲሱ መመረቂያ አዳራሽ ጧት 2፡00 ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

የፍቅር እና የጥበብ ዩኒቨርሲቲ

University of Love and Wisdom!

@wollouniversity12
@wollouniversity12
3.1K views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 16:39:54
ለሁሉም አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ።

@wollouniversity12
@wollouniversity12
2.7K views13:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 12:55:24
Official WOLLO UNIVERSITY Telegram Channel.

ትክክለኛው የወሎ ዩኒቨርስቲ ቴሌግራም ቻናል።

የሁሉንም ካምፓስ ያቀፈ Telegram Channel

Kombolcha, Dessie and ???? Campus

@wollouniversity12
@wollouniversity12
@wollouniversity12
@wollouniversity12
@wollouniversity12
3.0K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 10:22:45
ለሁሉም ደሴ ካምፓስ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ:-

ከላይ በማስታወቂያ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በመገኛት አጠቃላይ በዩኒቭርስቲ ቆይታችሁ ምን ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ለትምህርታችሁ ወሳኝ ምዕራፍ ማስጀመሪያ ውይይት ስለሚካሄድ ተሳታፊ እንድትሆኑ እናሳስባለን።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት


@wollouniversity12
@wollouniversity12
2.3K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 04:04:15 #መረጃ_ለ12ኛ_ክፍል_ተማሪዎች

#ወሎ_ዩንቨርሲቲ

መገኛ፡ደሴ( አማራ)
የግቢ ብዛትና የአየር ሁኔታ፡ ዩንቨርሲቲው ሁለት ግቢዎች ያሉት ሲሆን እነሱም ደሴ ከተማ እና ኮምበልቻ ከተማ ላይ ይገኛሉ፤ ሁለቱ ከተሞች በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ ከተሞች ቢሆኑም የአየራቸው ፀባይ ግን ለየቅል ነው።
ደሴ ከተማውም በመጠኑ ብርዳማ ሲሆን ግቢው ደግሞ ትንሽ ከከተማው ወጣ ብሎ ስለሚገኝና ሰፈሩም ዛፍ ነገር ስላካበበው የብርዱ መጠን ጠንከር ይላል በተለይ ምሽት ላይ ወዝወዝ ያስደርጋል ።
ኮምበልቻ ከተማ ደግሞ የኢንዱስትሪ ከተማ ስለሆነች መሰለኝ ሞቅ ትላለች ምናልባት የፋብሪካው ጢስ ይሆን?
ለማንኛውም ኮምቦልቻ ግቢ ለምትመደቡ ተማሪዎች ቀን ቀን ሞቃታማ ማታ ማታ ደግሞ ከዶርም ወጣ ሲሉ ብርዳማ ግቢ ነው ።
ኮቻ ግቢ ልክክ በልክ ነገር ናት ማለት ግቢው በጣም ሰፊ ሚባል ነገር አይደለም geographical አቀማመጡ ለተማሪዎች ሳይሆን ለወታደሮች ተብሎ design የተደረገ ሊመስላቹህ ይችላል ቢሆንም ግን ፍቅር ፍቅር ከሚሸቱት የግቢው ማህበረሰብ (ተማሪዎች) ተመጣጣኝ ካሳ ይጠብቃቹሃል።
፩ ደሴ campus (main campus)
ሁሉም የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች የሚገኙበት ሲሆን በተጨማሪም ከተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ውስጥ የጤናውን(medicine, nursing,HO..) እና የቲቺንግን(biology, physics, chemistry..) እና የቋንቋ ትምህርት (አረብኛ፣አማርኛ..)ክፍሎች የያዘ ግቢ ነው።
፪ kombolcha institute of technology
ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው ግቢው የቴክኖሎጂ ግቢ ነው
በውስጡም
Engineering, computer science, fashion design and architecture የመሳሰሉትን መስኮች አቅፎ የያዘ ግቢ ነው
Engineering
- Electrical and computer engineering
- Mechatronics Engineering (robotics)
- Software engineering
- Mechanical Engineering
- Civil engineering
- Textile engineering
- water resources and irrigation Engineering
- Hydrolics Engineering
- Industrial Engineering
- Cotem
- Garment Engineering
- Leather Engineering
- Chemical engineering...
በቀጣይ ምናልባትም Biomedical engineering ሊጀምር ይችላል።
Computer science
#CS
#IS
#IT
Fashion design and architecture
የትምህርት ሂደቱ አሪፍ የሚባል ነገር ነው ቢሆንም ግን ትንሽ ያጨናንቃል ።
በግ ተራ፣ኦቨር፣ጨብሲ ምናምን ለሚያበዛ ተማሪ የግቢው የክብር መሸኛ ደብዳቤ ይበረከትለታል ( ትምሮ ፊት ይነሳዋል)
በተረፈ ግቢያችን ከዘረኝነት የፀዳ ነው እንዳልል ከኢትዮ ውጭ ያለ ዩንቨርሲቲ ስለሚያስመስልብኝ በአንፃራዊነት ከሌሎች ግቢዎች በተሻለ መልኩ ሰላማዊ ግቢ ነው ለማለት ይቻላል።(ኮሽ ብሎ አያቅም )

ኮምቦልቻ ግቢ ለምትመደቡ ተማሪዎች ግቢው የሚገኘው አስፓልት ዳር በመሆኑ ግቢ በር ላይ በመውረድ ከመናሀሪያ ትርምስ ትድናላቹህ

ደሴ ግቢ ለምትመደቡም ሰርቪሶች ስለሚመደቡ ብዙ አታስቡ ፤ለማንኛውም ግን ንብረታችሁን ጠንቀቅ በሉ ምክንያቱም መናሀሪያ መግባታቹህ ስለማይቀር ብዬ ነው።
ወሎ ዩኒቨርሲቲ ስትደርሱ የተማሪዎች ህብረት ፣ የሰላም ፎረም ፣ የጸረ ሙስና ክበብ .. ወዘተ አባላት በር ላይ ባጅ አጥልቀው ስለሚቀበሏቹህ ምንም ዓይነት ሀሳብ አይግባቹህ ።

በተረፈ ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተመድባቹህ ለምትመጡ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ወደ ፍቅር ካምፓስ መጡ ብለን በወሎኛ እቅፍ አርገን ስመን እንቀበላቹሃለን

ወሎ ገራገሩ
ሸጋ ነው ሀገሩ

#ወሎ_ዩኒቨርሲቲ

#Striding_For_Quality

#የፍቅር_እና_የጥበብ_ዩኒቨርሲቲ

#university_of_love_and_wisdom

@wollouniversity12
@wollouniversity12


የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት ደሴ
2.6K views01:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 19:54:23 ለአንደኛ ዓመት ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች
የአንደኛ ዓመት ሁለተኛ ሴሚስተር ላይ ከምትወስዷቸው ኮርሶች ውስጥ Economics አንወስድም እየተባለ የሚወራው ከእውነት የራቀ ስለሆነ Economics ትምህርትን ጨምሮ 7 የትምህርት አይነቶች ትወስዳላችሁ። Economics Shade የተደረገው መምህር በሰዓቱ ተመድቦ ስላልተላከልን ስለሆነ ነው TBA ተብሎ የተገለፀው። TBA means to be assigned ለማለት ነው።

@wollouniversity12
@wollouniversity12
2.4K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 03:46:13
#WolloUniversity

ደሴ ግንቦት 14/2014 ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡ ከተመራቂዎች መካከል 293ቱ ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው በአሸባሪው ህወሓት ከወደመ በኋላ በቅንጅት መልሶ ተቋቁሞ መማር ማስተማር ስራውን ዳግም ጀምሮ ተማሪዎቹን ለዛሬው ምረቃ አብቅቷል።

ለዛሬ ምርቃ የደረሱ ተማሪዎች የሽብር ቡድኑ በፈጸመወ ወረራ ትምህርታቸው ቢስተጎጎልም ቅዳሜና እሁድ ጭምር አካክሰው ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ከተመረቁት ውስጥ 106ቱ ሁለተኛ ዲግሪ ናቸው።

በምርቃን ስነ ስርዓቱ ላይ የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የወሎ ዪኒቨርስቲ የአስ/ተማ አገ/ም/ፕ/ ዶ/ር አማረ ምትኩ እና የወሎ ዪኒቨርስቲ የአካ/ጉዳ/ም/ፕ/ ዶ/ር አወል ሰይድን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት ደሴ

@wollouniversity12
@wollouniversity12
2.9K views00:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 06:26:21 #Wollo_University

ወሎ ዩኒቨርስቲ የአዲስ ገቢ ተማሪዎችን የመግቢያ ቀን አሳወቀ። በዚህም መሰረት 2014 በወሎ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን #ግንቦት_21 እና 22 ,2014 ተብሏል።

Natural science --- ስማችሁ ከ A-K የሆናችሁ #ኮምቦልቻ ካምፓስ

Natural science --- ስማችሁ ከ L-Z የሆናችሁ #ደሴ ካምፓስ

All social science....Dessei Cumpas

የወሎ ዩኒቨርስቲ Group

Wollo University Dessie Campus
 
የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

@wollouniversity12
@wollouniversity12
2.5K views03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 06:04:16 Except apparent students

ብሎክ 28 የተመደባችሁ ተማሪዎች ዶርም ድልድል በእለቱ ፕሮክተር አማካኝነት ይሰጣችሃል

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት kiot
6.7K views03:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ