Get Mystery Box with random crypto!

𝙞𝙨𝙡𝙖𝙢𝙞𝙘 𝙠𝙣𝙤𝙬𝙡𝙚𝙙𝙜

የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_knwoledg — 𝙞𝙨𝙡𝙖𝙢𝙞𝙘 𝙠𝙣𝙤𝙬𝙡𝙚𝙙𝙜 𝙞
የቴሌግራም ቻናል አርማ islamic_knwoledg — 𝙞𝙨𝙡𝙖𝙢𝙞𝙘 𝙠𝙣𝙤𝙬𝙡𝙚𝙙𝙜
የሰርጥ አድራሻ: @islamic_knwoledg
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.86K
የሰርጥ መግለጫ

#የቴሌግራም_ቻናላችን_ሊንክ👇
https://t.me/joinchat/AAAAAEgolEJ2Rl3gT_bmuA
የፌስቡክ ግሩፓችን 👇
#ፊዳካ_ኣቢ_ወዑሚ_ያረሱልለህ
👇
https://facebook.com/groups/3118579678388903/
#የፌስቡክ_ፔጅ👇
Facebook peg link
https://www.facebook.com/323366755034719?referrer=whatsapp

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-28 03:59:50 ጀናባን የሚመለከቱ ህግና ደንቦች
አንብባችሁ ለወንድሞቻችሁና እህቶቻችሁ አስተላልፉ በጣም
ጠቃሚ እና አስፈላጊ እውቀት ያስጨብጣል።
የቃላት መፍቻ፡-
1. መኒይ (የዘር ፈሳሽ)፡-
- በስሜት ተስፈንጥሮ ከእርካታ ጋር የሚወጣ ፈሳሽ ነው፡፡
- ለወንድ ወፍራምና (ወደ ቢጫነት የሚያደላ) ነጭ ፈሳሽ
ሲሆን ለሴት ደግሞ ቀጭንና ቢጫ ነው፡፡ [ሙስሊም፡ 311]
ሽታው ወደሊጥ ሽታ የቀረበ ነው፡፡ በሆነ ምክንያት እነዚህ
መታወቂያዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡
- ከወጣ በኋላ የሰውነት መቀዝቀዝ ዘና ማለት (ፉቱር)
ይከተላል፡፡
- ፈሳሹ ሚዛን በሚደፋው የዑለማእ እይታ ጦሀራ እንጂ ነጃሳ
አይደለም፡፡ ይህን የሚደግፉ ሶሒሕ ማስረጃዎች መጥተዋል፡፡
[ሙስሊም፡ 694] [አልኢርዋእ፡ 1/197]
- በውንም ይሁን በህልም ከወጣ ገላን መታጠብ ግዴታ ነው፡፡
2. መዚይ፡-
- ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግ
(የሚያጣብቅ)፣ ቀለም አልባ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡
- አወጣጡ ከእርካታ ጋር አይደለም፡፡ ተስፈንጥሮ ስለማይወጣ
መውጣቱ ላይስተዋል ይችላል፡፡
- ነጃሳ ስለሆነ የነካውን አካል ማጠብ ይገባል፡፡ ልብስን ግን
የነካው ቦታ ላይ ውሃ በመርጨት ማፅዳት በቂ ነው፡፡
- የነካውን ቦታ እንጂ ገላን መታጠብ ግን ግዴታ አይደለም፡፡
ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡
3. ወዲይ፡-
- ከሽንት በኋላ የሚወጣ ነጭ ሽታ አልባ ፈሳሽ ነው፡፡
- የሚያጣብቅ አይደለም፡፡
- ብይኑ ከሽንት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
4. ከሴቶች ብልት የሚወጣ ፈሳሽ፡-
- ከማህፀን የሚወጣ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡ መጠኑ ከሴት ሴት
ይለያያል፡፡
- ሴቷ መውጣቱንም ላታስተውለው ትችላለች፡፡
- አካልንም ልብስንም ቢነካ አይነጅስም፣ ጦሃራ ነው፡፡
- ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡ ከሁለቱም መፀዳጃዎች በኩል
የሚወጣ ነገር ውዱእ ያፈርሳልና፡፡ አወጣጡ ቋሚ ከሆነ ግን
ለያንዳንዱ ሶላት ወቅቱ ከገባ በኋላ ውዱእ እያደረገች መስገድ
ይገባል፡፡ ውዱእ ካደረገች በኋላ ቢወጣ ቦታም አይሰጠውም፡፡
ገላን መታጠብ ግዴታ የሚሆነው መቼ ነው?
1. በውኑ ግንኙነት ከተፈፀመ የዘር ፈሳሽ (መኒይ)
# ቢፈስም_ባይፈስም ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
2. ግንኙነት # ባይፈፀምም የዘር ፈሳሽ (መኒይ) # ከእርካታ ጋር
ከወጣ ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
3. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ የዘር ፈሳሽ (መኒይ)
ካገኘ በማያሻማ መልኩ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡
4. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ ነገር ግን ሲነቃ ምንም
አይነት የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካላገኘ በማያሻማ መልኩ
የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ኡሙ ሱለይም የተባለችዋ
ሶሐቢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዲት
ሴት ኢሕቲላም ከሆነች (በህልሟ ግንኙነት ስትፈፅም ካየች)
የመታጠብ ግዴታ አለባትን?” ብላ ስትጠይቅ “ፈሳሽ ካየች አዎ”
ሲሉ መልሰውላታል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
5. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡
ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ
የመታጠብ ግዴታ አለበት፡፡
6. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡
ነገር ግን ሲነቃ ፈሳሽ አገኘ፡፡ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) እንዳልሆነ
እርግጠኛ ከሆነ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ የነካውን ግን
ሊያጥብ ይገባል፡፡ ብይኑ የሽንት ብይን ነውና፡፡
7. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡
ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን
# መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘ በ ሽታ ወይም በቻለው
መንገድ ለመለየት ይሞክርና ጥርጣሬው መኒይ ወደመሆኑ
ካደላ ይታጠብ፡፡ ጥርጣሬው መዚይ ወደመሆኑ ካደላ ግን
በተለይም ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት አስቦ ከነበር እንደ
መዚይ ይቁጠረውና የነካውን ቦታ ብቻ ይጠብ፡፡ ገላውን
የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ
ነው፡፡
8. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡
ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን
# መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘና ግምቱ ወደየትኛውም
ካላደላ፣ ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት # ያላሰበ ከሆነ ጉዳዩ
አወዛጋቢ ቢሆንም ትክክለኛው ትጥበት የለበትም የሚል ነው፡፡
ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡ [ፈታዋ
ኢብኑልዑሠይሚን፡ 11/161]
የጀናባ አስተጣጠብ ሁለት አይነት ነው፡፡
1. የሚያብቃቃ ማለትም ግዴታውን ለማውረድ የሚጠበቅ ሲሆን
እሱም ሙሉ አካልን በውሃ ማዳረስ ነው፡፡ ባይሆን
መጉመጥመጥና በአፍንጫ ውሃ መሳብ (ኢስቲንሻቅ)
እንዳይረሳ፡፡ ለትጥበት ኒያ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ አንድ ሰው ጀናባ
ማውረድን ሳያስብ እንዲሁ ውሃ ውስጥ ዋኝቶ ቢወጣ መላ
አካላቱ ውሃ መንካቱ ብቻ ጀናባው ለመውረዱ በቂ አይሆንም፡፡
ይስተዋል! ይህን ትጥበት ካደረጉ በኋላ ውዱእም ባያደርጉ
መስገድ ይቻላል፡፡ ባይሆን ከትጥበቱ መሀል ውዱእ የሚያፈርስ
ነገር መፈፀም የለበትም፡፡
2. ሌላኛውና በላጩ ግን በቅድሚያ ሁለት እጆችን መታጠብ፡፡
ከዚያም ኢስቲንጃእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ውዱእ ማድረግ፡፡
ከዚያም ከእራስ ጀምሮ ቀሪ አካላትን ውሃ ማዳረስ፡፡ እግርን
ከውዱእ ጋር ማጠብም ይቻላል፤ መጨረሻ ላይ ማጠብም
ይቻላል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
ማሳሰቢያ፡-
ሴቷ ለትጥበት ስትል የፀጉር ጉንጉኗን የመፍታት ግዴታ
የለባትም፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም: ኡሙ ሰለማህ
ለጀናባህ ወይም ለሐይድ ትጥበት ፀጉሯን “ልፍታው ወይ?” ብላ
ስትጠይቃቸው “አይ! የሚበቃሽ ከእራስሽ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ
ማፍሰስ ብቻ ነው” ብለዋታል፡፡ [ሙስሊም] ስለዚህ ፀጉር
ሳይፈታ ውሃ መድረስ ከቻለ መፍታት አይጠበቅም፡፡
ለማጣቀሻነት የተጠቀምኩት
1. ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን
2. ፈትሑልዐላም ፊn ዲራሰቲ አሓዲሢ ቡሉጊልመራም እና
ሌሎችም
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡
Please share it
#እበኮን_ለወዳጅ_ዘመዶ_ሊንኩን_ሼር
#በማድረግ_ይተበበሩን
Telegarm |
https://t.me/joinchat/AAAAAEgolEJ2Rl3gT_bmuA
182 viewsj̷e̷l̷a̷l̷u̷d̷i̷n̷ i̷b̷n̷u̷ a̷l̷i̷ , 00:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 03:59:49
166 viewsj̷e̷l̷a̷l̷u̷d̷i̷n̷ i̷b̷n̷u̷ a̷l̷i̷ , 00:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:46:41 አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀሙባቸው ፡፡

ወጣትነትህን     ከማርጀትህ በፊት
ጤንነትህን       ከመታመምህ በፊት
ሀብትህን         ከመደህየትህ በፊት
ትርፍ ጊዜህን    ከመጨናነቅህ በፊት
ህይወትህን         ከመሞትህ በፊት

የአሏህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)  ሲናገሩ " ሕዝቦች አምስት ነገሮችን በመውደድ ከአምስት ነገሮቺ ይዘናጋሉ"  ካሉ በኀላ ሲዘረዝሯቸው እንዲህ አሉ:

   ሕይወትን ያፈቅሩና - ሞትን ይረሳሉ:

ዱንያን ያፈቅሩና -አኼራን ይዘነጋሉ፡

  ህንፃ መገንባት ይወዱና - ቀብር  መኖሩን ይዘነጋሉ፡

  ገንዘብ ይወዱና - ከሒሳብ ( በቂያማ ግዜ መተሳሰቡን ) ይዘነጋሉ ፡

ፋጡራንን ያፈቅሩና - ፈጣሪን ይዘነጋሉ ፡፡
አሏህ ከዚህ ተግባር ይጠብቀን ኣሚን ፡፡
372 viewsHayate Hayate, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:45:30
325 viewsHayate Hayate, 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 17:37:12 #በሰለፎችህ_ተመከር፡
#ከጠማሞች_አትከራከር፡
<~~~~~~~~\\~~~~~~~~>
①#አብደላህ<ኢብኑ_መስዑድ[ረደሏሁ አንሁ]እንዲህ ይላሉ፡–
#አንድ_ሰው_ለአኼራውም_ይሁን_ለዱንያው ምንም ነገር ማይሰራ ስራ ፈት ሆኖ ሳየው እጠላዋለሁ
صفة الصفوة ١/١٢٠

②#ኢብኑ_ጀውዚ_[ረሒመሁሏህ]_እንዲህ ይላሉ፡–
#አንድ_ሰው_በጣም_ወሳኝ_የሆኑ_ጉዳዮቹ ሁለት እንደ ሆኑ ሊያውቅ ይገባዋል።
#እነርሱም_ልቡ_እና_ጊዜው ናቸው።
#በጊዜው_ተጫውቶ_ልቡን_ያበላሸ_የሆነ ሰው ያለ ምንም ጥቅም ይቀራል።

[[حفظ العمر ٥٩]]
③#ሱፍያን_አል_ሰውሪ_ረሒመሁሏህ_እንዲህ ይላሉ፡–
በእድሜው የተጫወተ የሆነ ሰው የሚዘራበት ቀን እንዳባከነ ይቆጠራል።
የሚዘራበት ቀን ያባከነ የሆነ ሰው ደግሞ የአጨዳ ቀን ይፀፀታል።
حفظ العمر لابن الجوزي ٦٥

ብዙ ሰዎች ጊዜያቸውን በሚገርም ሁኔታ ሲጫወቱበት አያለሁ።
=]>#ለሊቱ_ከረዘመ_በማይጠቅም_ወሬ ያሳልፉታል።
=]>#ቀኑ_ከረዘመ_በእንቅልፍና_ገበያ በመዟዟር ያሳልፉታል።
#የመኖርን_ትርጉም_የተረዱት_ግን_በጣም ጥቂቶች ናቸው።
#እነርሱም_ለማይቀረው_ጉዞ_ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ናቸው።
صيد الخاطر ص١٥٧

#የህይወት_ትርጉሟ_ምን_እንደሆነ_ማያውቁ ብዙ ሰዎች አይቻለሁ።
=]>#ከነሱ_ውስጥ_አላህ_ገንዘብ_ሰጥቶት ከስራ ያብቃቃው አለ
#እሱ_ግን_ዝም_ብሎ_አብዛኛው_ቀኑን_ገበያ ላይ ያሳልፈዋል።
#እዛ_ቦታ_ቁጭ_ብሎ_ግን_ስንትና_ስንት ወንጀሎች ይመለከታል።
=]>ከነሱም ስለ ፖለቲካ እያወራ ጊዜውን ሚፈጀው ብዙ ነው።
=]>#ከነሱም_በጨዋታ፣
#በጭፈራ
#በሌሎችም_ነገሮች ጊዜውን ሚፈጀው ብዙ ነው።
#በዚህም_ጊዜ_የጊዜ_አስፈላጊነት_የእድሜ ጥቅምና ደረጃው አላህ ለወፈቀው እንጂ እንዳላሳወቀው ተረድቻለሁ………።
صيد الخاطر ٢٤١

#የቴሌግራም_ቻናላችን_ሊንክ

https://t.me/joinchat/AAAAAEgolEJ2Rl3gT_bmuA

የፌስቡክ ግሩፓችን

#ፊዳካ_ኣቢ_ወዑሚ_ያረሱልለህ

https://facebook.com/groups/3118579678388903/

#የፌስቡክ_ፔጅ

Facebook peg link
https://www.facebook.com/323366755034719?referrer=whatsapp
385 viewsj̷e̷l̷a̷l̷u̷d̷i̷n̷ i̷b̷n̷u̷ a̷l̷i̷ , 14:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 17:32:42
356 viewsj̷e̷l̷a̷l̷u̷d̷i̷n̷ i̷b̷n̷u̷ a̷l̷i̷ , 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 19:21:34
766 views@እማ ጀነቲ , 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 16:43:07
خُذِ الْعَفْوَ وَأْمُرْ بِالْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ الْجَاهِلِينَ

[ ሱረቱ አል-አዕራፍ - 199 ]
ገርን ጠባይ ያዝ፡፡ በመልካምም እዘዝ፡፡ ባለጌዎቹንም ተዋቸው፡፡
750 viewsj̷e̷l̷a̷l̷u̷d̷i̷n̷ i̷b̷n̷u̷ a̷l̷i̷ , edited  13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 17:30:00 قال النَّبيَّ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم : "مَن حَفِظَ عَشْرَ آياتٍ من أوَّلِ سورةِ الكَهفِ، عُصِمَ من فِتنَةِ الدَّجَّالِ" .

أخرجه مسلم .
ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ እንዲ ብለዋል
ከሱረቱል ካህፍ አስር አያዎችን የሀፈዘ ከደጃል ፈትና ይጠበቃል ሙስሊም ዘግበውታል

ለሌሎቹ share ማድረግ አትርሱ

https://t.me/joinchat/AAAAAEgolEJ2Rl3gT_bmuA
783 viewsj̷e̷l̷a̷l̷u̷d̷i̷n̷ i̷b̷n̷u̷ a̷l̷i̷ , 14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ