Get Mystery Box with random crypto!

Excellence Life Faith Church

የቴሌግራም ቻናል አርማ excellencelifefaithchurch — Excellence Life Faith Church E
የቴሌግራም ቻናል አርማ excellencelifefaithchurch — Excellence Life Faith Church
የሰርጥ አድራሻ: @excellencelifefaithchurch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 210
የሰርጥ መግለጫ

#ራዕይ
ሰዎች ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ የተደረገላቸውን እንዲያውቁ ማድረግ።
📖 ፪ኛ ቆሮ ፰ ÷ ፯
<<እናንተም በሁሉ ነገር ይኸውም በእምነት፣ በቃል፣ በዕውቀት፣ በፍፁም ትጋትና ለእኛም ባላችሁ ፍቅር #ልቃችሁ_እንደተገኛችሁ...>>
💒 For any additional Info and feedback Contact Us:
👉 @LeeYeshua 👈
👉 0911645877 👈 Pr.Kasse

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-22 21:38:26
ከፊታችን ባለው እሁድ ልዩ የእግዚአብሔርን ህያው ቃል የምንማርበት እና ጌታን በመዝሙራችን የምናመልክበት ድንቅ ጊዜ ስለሚኖረን በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል !

:-መፀሀፍ ቅዱስ እና አጀንዳዎትን መያዝ አያዘንጉ !

አድራሻ :- አየር ጤና,ቻይና ካምፕ ከድልድዩ 100m ወረድ ብሎ በሚገኘው የመጀመሪያ ህንፃ ላይ ወደ ሚካኤል በሚወስደው አቅጣጫ በስተግራ በኩል
33 viewsAbel Resom, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 10:03:44
መልካም ዜና በአዳማ እና ዙሪያዋ ለምትገኙ ሁሉ !
*******************************************
"የአዲስ ፍጥረት እውነታዎች" በሚል ርዕሰ ከፊታችን ባለው ማክሰኞ የሚጀምር ለ 3 ተከታታይ ሳምንታት የሚቆይ የትምህርት ኮንፍረንስ በ "ሔብሮን የእምነት ህይወት ቤተክርስቲያን" አዳማ አጥቢያ ስለተዘጋጀሎት በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል !
47 viewsAbel Resom, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 14:28:57 የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ

አንድ ምሽት ላይ አባት ልጁን ወደ ሲኒማ ቤት ሊወስደው ውጪ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እየጠበቀው ነው፡፡ ልጅ ከቤት እንደወጣ በጣም ስለጨለመበት ስልኩን አውጥቶ አባቱ ጋር ደወለ፡፡

• ልጅ፡- “አባዬ እንዴት ልምጣ? ጨለማ ስለሆነ አይታይም”፡፡
• አባት፡- “ምን ያህል ይታይሃል?”
• ልጅ፡- “አምስት እርምጃ ያህል ብቻ ነው የሚታየኝ”
• አባት፡- “አምስት እርምጃ ተራመድ”
• ልጅ፡- “እሺ” (አምስት እርምጃ ተራመደ)
• አባት፡- “አሁንስ ምን ያህል ይታይሃል?”
• ልጅ፡- “አሁንም ሌላ አምስት እርምጃ ያህል ርቀት ይታየኛል”
• አባት፡- “በፊትህ የሚታይህን አምስት አምስት እርምጃ እያልክ ከመጣህ እኔ ጋ ትደርሳለህና የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ”

ልጅ ብዙም ሳይቆይ አባቱ ጋር ደረሰ፡፡

ሁሉም ነገር ጥጉ ድረስ እስኪታይህ አትጠብቅ፡፡ በሚታይህ መጠን ተራመድ፡፡ የሚታይህን ያህል ስትራመድ፣ ከመራመድህ በፊት ያልታየህን ማየት ትጀምራለህ፡፡

ሁሉንም ነገር እስከምታውቅ አትጠብቅ፡፡ በምታውቀው ልክ ስራን ጀምር፡፡ በምታውቀው እውቀት መጠን ስራን ስትጀምር፣ ያንን ከመጀመርህ በፊት ያልነበረህ ልምድና እውቀት ወደ አንተ ይመጣል፡፡

ሁሉም ሰው እስኪቀበልህ አትጠብቅ፡፡ የሚቀበሉህ ላይ በማተኮር ተሰማራ፡፡ በሚቀበሉህ ላይ ስታተኩርና ደስተኛ ስትሆን፣ ቀድሞ የማይቀበሉህ ሁሉ አንተን ከመቀበል ውጪ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡

የጠየከው ነገር ሙሉ በሙሉ እስኪሰጥህ አትጠብቅ፡፡ የተሰጠህን ተቀበልና በዚያ በመጀመር የምትችለውን አድርግ፡፡ በተሰጠህ በጥቂቱ የምታደርገው ጥረትና የምታከናውነው ነገር የቀረው እንዲለቀቅልህ መንገድ መክፈቱ አይቀርም፡፡

አትቀመጥ! የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ! ስራ!
64 viewsKasse, 11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-17 23:00:34
69 viewsAbel Resom, 20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 11:18:37
ከፊታችን ባለው እሁድ ልዩ የእግዚአብሔርን ህያው ቃል የምንማርበት እና ጌታን በመዝሙራችን የምናመልክበት ድንቅ ጊዜ ስለሚኖረን በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል !

:-መፀሀፍ ቅዱስ እና አጀንዳዎትን መያዝ አያዘንጉ !

አድራሻ :- አየር ጤና,ቻይና ካምፕ ከድልድዩ 100m ወረድ ብሎ በሚገኘው የመጀመሪያ ህንፃ ላይ ወደ ሚካኤል በሚወስደው አቅጣጫ በስተግራ በኩል
118 viewsAbel Resom, 08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 10:23:49
ከፊታችን ባለው እሁድ ልዩ የእግዚአብሔርን ህያው ቃል የምንማርበት እና ጌታን በመዝሙራችን የምናመልክበት ድንቅ ጊዜ ስለሚኖረን በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል !

:-መፀሀፍ ቅዱስ እና አጀንዳዎትን መያዝ አያዘንጉ !

አድራሻ :- አየር ጤና,ቻይና ካምፕ ከድልድዩ 100m ወረድ ብሎ በሚገኘው የመጀመሪያ ህንፃ ላይ ወደ ሚካኤል በሚወስደው አቅጣጫ በስተግራ በኩል
80 viewsAbel Resom, 07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 15:55:27
81 viewsKasse, 12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 04:01:09 እምነት ከመስማት ነው፤ መስማትም ከእግዚአብሔር ቃል ነው።


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የጸለያችሁትን የለመናችሁትንም ሁሉ እንዳገኛችሁት እመኑ፥ ይሆንላችሁማል። (የማርቆስ ወንጌል 11፥24)

ዓለም "ማየት ማመን ነዉ" የሚል ተፈጥሮአዊ የእምነት ትርጓሜ አላት። ይህም በመዳሰስና በመዳበስ የሚገኝ የስሜት እምነት ነዉ። እንደዚህ አይነቱ የስሜት እምነት፣ ከክርስቶስ ትንሳኤ በኋላ ቶማስ የተመላለሰበትና ክርስቶስም ያወገዘዉ ተፈጥሮአዊ እምነት ነዉ።

የእግዚአብሔር ቃል የእግዚአብሔር እዉነት ነዉና፣ እዉነትም የእግዚአብሔር ቃል የሚነግረን ነዉና፣ ስለ እምነትም እዉነት የሆነዉ ቃለ እግዚአብሔር የሚናገረዉን መስማት በጣም ተገቢ ነዉ።

ክርስቶስ ብፁህ ናቸዉ ብሎ ያለዉ ሳያዩ ያመኑትን እንጂ አይተዉ ያመኑትን አይደለም። በዚህም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት፣ በማመን የሚገኝ ማየት እንጂ በማየት የሚገኝ ማመን እንዳልሆነ እንረዳለን።

ከእግዚአብሔር የተቀበሉትም ሆነ የሚቀበሉት በቁስ ደረጃ እጃቸዉ ሳይገባ በእምነት ግን እንደ ተቀበሉ እርግጠኛ ሆነዉ የኖሩት ናቸዉ።

አንድ የቤት ባለቤት፣ ስለቤቱ ጉዳይ ቤቱን ማሳየት ሳይጠበቅበት የቤቱን ካርታ ካሳየ ታማኒነት እንደሚኖረዉ ልክ እንደዝያዉ በነገሮቻችን ፈንታ የነገሮቻችን ምንጭ የሆነዉን የእግዚአብሔርን ቃል ማሳየትና በቃሉም እዉነት ላይ መጽናት መጽሐፍ ቅዱሳዊ እምነት ነው ::
115 viewsKasse, 01:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:23:34 ፍቅር ሲመዘን

የሰዉ ልጅ ህይወት ዋና ክፍል ፍቅር ነው
ሰዉን በአምሳሉ የፈጠረዉ እግዚአብሔርም ፍቅር ስለሆነ፤ በምድር ላይ እንድንማረው የተፈለገው፣ ከሁሉ የሚበልጠውን ፍቅርን ነዉ :: ስለሆነም ፍቅር ጌታ ,ለሰጠን ትእዛዛቶች ሁሉ መሰረት በመሆኑ <<ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ተጠቅልሏል ይኸውም "ባልጀራህን እንደራስህ ውደድ የሜል ነው።"ገላ 5:-14 በውነቱ ራስ ወዳድ ሳይሆኑ ሌላን መውደድን መማር እንዲህ ቀላል ነገር አይደለም ፤ምክንያቱም ራስ ወዳድነት የተፈጥሮ ባህሪያችን ስለሆነ፤ለዚህም ነው ከራስ አልፎ ሌሎችንም ለመውደድ ዕድሜያችንን ሁሉ የምንማረው ትምህርት ሆኖ የተሰጠን።ለዓለም በቀላሉ የሚታየው የህይወት ምስክርነታችን(ምሳሌነታችን)የዶክትሪን አቋማችን ወይንም ሌላ የሐይማኖት ስርአታችን ሳይሆን፤እርስበርስ ያለንን ፍቅር መሆኑን ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ብሏል<<እርስበርሳችሁ ብትዋደዱ ሠወች ሁሉ የእኔ ደቀመዝሙር መሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።ዮሐ 13:-35>>ከአስርቱ ትእዛዛት አራቱ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግኑኙነት ሲያመለክቱ ስድስቱ ግን ከሠወች ጋር የሚኖረንን ግንኙነቶች ናቼው። በእውነቱ ይህንን ትልቅ ሀሳብ ለመዘርዘር ጌዜ ያንሳል ቢሆንም ግን ባጭር ቃል ለመናገር አስሩንም ግንኙነቶች ኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ዋና የሆነውን ነገር በሁለት አረፍተነገሮች አጠቃሎቴል ""እግዚአብሔርን መውደድ""
""ሠወችንን መውደድ ""
<<ጌተ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ በፍጹም ሐሳብህ ውደድ።ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል>> ይህም ባልንጀራህን እንደራስህ (እንደነፍስህ)ውደድ የሜለው ነው።ማቴ 22:-37-40ትእዛዛቶች ሁሉ በእነዚህ ሁለት handle(ማንጠልጠያ)እጀታ ተይዘዋአል።እግዚአብሔር መንፈሳዊ እድገታችንን ከሚመዝንበት አንዱ መንፈሳዊ ስርአታችንን ሳይሆንእግዚአብሔርን መውደዳችንን እና ባልንጀራችንን እንደራሳችን የምንወድበት ህይወታችንን ነው።
76 viewsAbel Resom, 18:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 12:59:44
FOUNDATION CLASS
"RIGHTEOUSNESS"
ክፍል-5
ከ 3:00-4:00

አድራሻ :- አየር ጤና,ቻይና ካምፕ ከድልድዩ 100m ወረድ ብሎ በሚገኘው የመጀመሪያ ህንፃ ላይ ወደ ሚካኤል በሚወስደው አቅጣጫ በስተግራ በኩል
101 viewsAbel Resom, 09:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ