Get Mystery Box with random crypto!

Remadan ረመዳን

የቴሌግራም ቻናል አርማ remadan1443 — Remadan ረመዳን R
የቴሌግራም ቻናል አርማ remadan1443 — Remadan ረመዳን
የሰርጥ አድራሻ: @remadan1443
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 563

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-15 22:00:28 የተለያየ አፕልኬሽኖችን በመጠቀም እውቀትን በቀላሉ እያገኘን ነው ማሻአላህ ግን ሁሉም ሰው አይደለም ስማርት ስልክም ያለው በተለይ የገጠሩ ማህበረሰቡ አርካኑል ኢስላም እንኳን በደብ ያልደረሰበት አህዋል ስላለ ይህን ስለ ረመዳን የተዘጋጀ ፁሁፍ በአንድ ገፅ ፊትና ኃላ ፕሪንትና ኮፒ አድርገን በሚዘጋጁ መድረኮች ብናሰራጭ በርከት ያለ ምንዳ እናገኛለን.
67 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 08:04:30
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

በኢባዳ ላይ በርታ ከሰዎች ሁሉ የተሻል ትሆናለህ; ባለህ ተብቃቃ ከሰዎች የተሻለ አመስጋኘ ትሆናለህ; ለራስ የምትወደውን ለሰዎችም ውደድ አማኘ ትሆናለህ;  ለጎረቤት መልካም ሁን ሙስሊም ትሆናለህ, ሳቅ አታብዛ ብዙ መሳቅ ቀልብ ያደርቃል.
ቢን ማጃህ 421
150 views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-13 21:05:47 ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

ወደ ጀሀነም የሚወስዱትን #ሰባት ወንጀሎች ተጠንቀቁ
ከአላህ ጋር   ሌሎች አማልክቶችን ማምለክ
አላህ እንዳትገደል የከለከላትን ነፍስ ማጥፋት
ወለድ መብላት
የየቲምን ገንዘብ መብላት
ከጅሀድ ሜዳ መሸሽ
የንፁህ ሴት ስም ማጥፋት
ጥንቁልና ድግምት መስራት ማሰራት ናቸው


إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ ضَلَّ ضَلَالًا بَعِيدًا

አላህ በርሱ #የማጋራትን (ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም #የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ. 4:116


يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَن يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِن يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَّا يَسْتَنقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ

እናንተ ሰዎች ሆይ! አስደናቂ ምሳሌ ተገለጸላችሁ፡፡ ለእርሱም አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) ዝንብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡ እርሱን (ለመፍጠር) ቢሰበሰቡም እንኳን (አይችሉም)፡፡ አንዳችንም ነገር ዝንቡ ቢነጥቃቸው ከእርሱ አያስጥሉትም፡፡ ፈላጊውም ተፈላጊውም ደከሙ፡፡ 22:73
104 views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-12 15:53:43 ከተከለከሉ ነገሮች ምን ያህሉን ርቀናል ራሶን ይተሳሰቡ በነዚህ ነጥቦች....

?...? በአላህ #ማሻረክ (ከአላህ ውጪ ያሉ ነገሮችን ማምለክ)
ጥቁልና ድግምት መስራት ማሰራት
ዝምድናን መቁረጥ
#ወላጆችን አለመታዘዝ
ወለድ መቀበል መስጠት
የቲሞችን ገንዘብ መብላት
በውሸት መስከር መማል
መጠጥ አደዛዠ እፅ መዉሰድ
#ዝሙት ሀራም የሆነ ግንኙነት
ቁማር መጫወት
የንፁህ ሴቶችን ስም ማጥፋት
ሃራም #መመገብ መስረቅ
ሰዎችን  መበደል በተለይ #የትዳር አጋርን, በስራችን የሚገኙትን
ውሸት 
#ሀሜት
ጉቦ መስጠት መቀበል
ለዩልኘ መስራት
ነገር ማዋሰድ
ቃል አለማክበር
ጎረቤትን ማስቸገር
ዘረኘነት
ሚዛንን ማጉደል
በማይጠቅመን ነገር #ጊዜን ማጥፋት ሙሰልሰል ኳስ...
176 viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 21:56:51 ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

ብልጥ ብሎ ማለት  ለምን እንደተፈጠረ አውቆ ለዛነገር የሚስራ ሲሆን ሞኘ ብሎ ማለት ለስሜቱ ወይም ለቁሳዊ ፍላጎቱ የሚኖር ነው.

የአመት ስራችን በተወሰነ መልኩ  እንገምግም

እቂዳችን ምን ያህል የጠራ ነው?  ከሽርክ  ምን ያህል የፀዳን  ነን? 

የስላት አፈፃፀማችን ምን ይመስላል? በተለይ የፈርድ ሰላት

ዘካ ወጅቦብን አውጥተናል

ዘጅ ለማድረግ አቅሙ ኖሮን ፈፅመናል

የወላጅ ሀቅ ምን ያህል ተወተናል

የባለቤትህን/ሽን  ሀቅ ምን ያህል ተወተናል

የልጆች ሀቅንስ በተለይ ዲን አውቀው እንዲያድጉ

ሰዎችን በጥሩ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል በተለይ የእስልምናን መልክት ላልደረሳቸው ሰዎች ማድረስስ 
በሚሉ ነጥቦች ዙሪያ ራሶን ይገምግሙና ለራሶ ውጤት ይስጡ
68 viewsedited  18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-09 21:18:18
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

ወርቅና ሀር ከህዝቦቼ ለሴቶች የተፈቀደ ሲሆን ለወንዶች ክልክል ነው. ነሳኢ 5148
141 viewsedited  18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 22:29:50 إِنَّ الْمُسْلِمِينَ وَالْمُسْلِمَاتِ وَالْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ وَالْقَانِتِينَ وَالْقَانِتَاتِ وَالصَّادِقِينَ وَالصَّادِقَاتِ وَالصَّابِرِينَ وَالصَّابِرَاتِ وَالْخَاشِعِينَ وَالْخَاشِعَاتِ وَالْمُتَصَدِّقِينَ وَالْمُتَصَدِّقَاتِ وَالصَّائِمِينَ وَالصَّائِمَاتِ وَالْحَافِظِينَ فُرُوجَهُمْ وَالْحَافِظَاتِ وَالذَّاكِرِينَ اللَّهَ كَثِيرًا وَالذَّاكِرَاتِ أَعَدَّ اللَّهُ لَهُم مَّغْفِرَةً وَأَجْرًا عَظِيمًا

ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ መጽዋቾች ወንዶችና መጽዋቾች ሴቶችም፣ ጿሚዎች ወንዶችና ጿሚዎች ሴቶችም፣ (ካልተፈቀደ ሥራ) ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ወንዶችና ጠባቂ ሴቶችም፣ አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም፣ አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል. 33:35


مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ኾኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን.16:97


እንዲህ አይነት እሳቤ ከ1400 አመት በፊት የያዘ ብቸኛው መፀሀፍ ቁርአን ነው  የተባበሩት መንግስታት እንኳን በ1975 አከባቢ ነው የሴቶች ቀን እውቅና የሰጠው

እስልምና የሴቶችን መብት በቀዳሚነት እንደሚያከብ  በምእራቡ አለም   በብዛት  እስልምናን የሚቀበሉት  ሴቶ መሆናቸው ቀላል ማስረጃ ነው
199 views19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 21:21:59 በግለሰብ ደረጃም ይሁን በድርጅት ለዝች አጭር ህይወት ውጤታማ ለመሆን ሰዎች ስትራቴጂ ነድፈው እቅድ አውጥተው ይተገብራሉ ውጤታቸውንም በየወሩ በየአመቱ እየገመገሙ እሄን ያክል አተረፍን ወይም  ውጤት አመጣን እያሉ በየጊዜው ሪፓርት ያወጣሉ.

ለእውነተኛው አገርም ስዎች ከዚህ በተሻለ መልኩ ስራችን ልንተሳሰብ ይገባል

የሰው ልጅ ስራ በሳምንት ሁለት ጊዜ ሰኞና ሀሙስ ረፓርት ይቀርባል እንዲሁም የአመት የስራችን ሪፓርት  አላህ ዘንድ በዚህ  ባለንበት ሸአባን ወር በየአመቱ ይቀርባል.

ባለፈው  ከረመዳን በኋላ እንፈፅማቸዋለን ብለን ያሰብናቸው መልካም ስራዎች ምን ያህሉ እንደተሳካልን እንመልከት እስቲ

ከሃራም ነገር ለመቆጠብ አስበን ምን ያህል ተሳክቶልናል
የፈርድ ስላት አፈፃፃማችን ምን ይመስላል

በተደጋጋሚ ቁርአን ለማክተም አስበን ምን ያህል ተሳክቶልናል

ቁርአንም ያልቀራን ለመማር አስበን ምን ያክል ፈፀምን

ፈርድ ነገሮችን ሳንቸገር የምንከው ለይል ለመስገድ አስበን ምን ያህል ተሳክቶልና

በአጠቃላይ ከባለፈው ረመዳን በኋላ ያለው  የአመት አፈፃፀማችን መገምገም ብልህነት  ነው.
245 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 22:00:06 ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ፡፡

«የምናበላችሁ ለአላህ ውዴታ ብቻ ነው፡፡ ከእናንተ ዋጋንም ማመስገንንም አንፈልግም፡፡

«እኛ (ፊትን) የሚያጨፈግግን ብርቱ ቀን ከጌታችን እንፈራለንና፤» (ይላሉ)፡፡

አላህም የዚያን ቀን ክፋት ጠበቃቸው፡፡ (ፊታቸው) ማማርንና መደሰትንም ገጠማቸው፡፡
76:8-11


ነብዩ (ሰዐወ)  አላህ(ሰወ)  የትንሳኤ ቀን ይላል የአደም ልጅ ሆይ ምግብ ጠይቄህ ነበር አልመገብከኘም እሱም ይላል አተ የአለማት ጌታ ሆነህ እንዴት እመግበሀለው? አላህም ይላል  የኔ አገልጋይ ምግብ ጠይቆህ አልመገብከውም ብትሰጠው ኖሮ  እኔ ዘንድ ምንዳህን  ታገኘው ነበር. (ሙስሊም)
82 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 10:50:23
' ሰላተል ኢስትስቃ '

ነገ በመላ ሀገሪቱ "ሰላተል ኢስ ትስቃ" እንዲሰገድ  የኢትዮጵያ  እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጥሪ አቅርቧል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ  በቦረና ዞን በዝናብ እጥረት ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ  " ሰላተል ኢስ ትስቃ " እንዲሰገድ ለመላው ምዕመን ጥሪ አድርጓል።

ነገ ሰኞ በመላው ሀገሪቱ እንዲሰገድ ጥሪ የቀረበው " ሰላተል ኢስትስቃ " ዝናብ በሚርቅበት ጊዜ የሚሰገድ ሰላት.

በሌላ በኩል ፤ ጠቅላይ ም/ቤቱ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን ዕርዳታ የሚውል ድጋፍ ማሰባሰቢያ የባንክ ቁጥሮችን ይፋ አድርጎ ድጋፍ  እያሰባሰበ ነወ።

ጠቅላይ ም/ቤቱ ይፋ ያደረጋቸው የባንክ ቁጥሮች ፦
የኢትዮጵያ ንግድ - 5582 
ዳሸን ባንክ - 795571270973
ዘምዘም - 222255
ሂጅራ ባንክ - 308010
ኦሮሚያ ህብረት - 1000093406226
269 views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ