Get Mystery Box with random crypto!

Wollo Addis

የቴሌግራም ቻናል አርማ wolloaddis04 — Wollo Addis W
የቴሌግራም ቻናል አርማ wolloaddis04 — Wollo Addis
የሰርጥ አድራሻ: @wolloaddis04
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.50K
የሰርጥ መግለጫ

➦ ⓌFor More Information Join Wollo Addis Social Media Channels
➤ 𝒀𝒐𝒖𝑻𝒖𝒃𝒆 :- https://yt6.pics.ee/53apjt
➤ 𝑻𝒆𝒍𝒆𝒈𝒓𝒂𝒎 :- https://t.me/wolloaddis04
➤ 𝑭𝒂𝒄𝒆𝑩𝒐𝒐𝒌 :- https://www.facebook.com/wolloenter01/

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-06-09 23:04:41

1.4K views20:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 22:22:45

1.3K views19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 20:59:45
1.4K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 20:59:38 ከ፩ ዐማራ ፋኖ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

እናት ሀገር ኢትዮጵያ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች የተለያዩ ውብ ባህሎች እና የእምነት ብዝኻነት ያላት ከመሆኗም በላይ ሁሉም ዓይነት ብዝኻነቶችም ተቻችለው፣ ተፈቃቅደውና በፈርሃ አምላክ ተዋደን የሚኖሩባት የምድር ገነት መሆኗ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ እናት ሀገር ኢትዮጵያ ሀገራዊ ስሪቷ ፀንታ የኖረችውም በሁሉም ኢትዮጵያውያን ክቡር ተጋድሎና ሰማዕትነት መሆኑን ለማስታወስ ብዙ የውጪ ወረራዎችን ያከሸፉበት ብሎም አሳፍረውና አዋርደው የመለሷቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ህያው ምስክሮቻችን ናቸው።
ታሪካዊ እና ሀገራዊ የውጪ ጠላቶቻችን በወረራና በጦርነት ያልተሳካላቸውን የማንበርከክ፣ ሀገራዊና ስነ ልቦናዊ ውቅራችንን ለመፈታተን የመረጡት መንገድ "የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ" የሚለውን ብሒል ሲሆን፦ በተለያዩ ጊዚያትም ሀገር በቀል ባንዳዎችን በመመልመል፣ በመደገፍ፣ በማሰልጠን፣ ብሎም ለሀገራዊ በትረ ስልጣን በማብቃት የኖረውን እና ፅኑውን የሀገር ፍቅር ስሜቶቻችንን ሲፈታተኑ መቆየታቸውን ማሳያው ዘርፈ ብዙ ቢሆንም አሁናዊ የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታችን ህልው ምስክራችን ነው!
ይባስ ብሎም በስመ መንግስት የመንግስት ስም ያለው ስብስብ ከፕሪቶሪያው ስምምነት ማግስት ዐማራ ክልልን ህግና ስርዐት አልባ በማስመሰል፣ ክልሉንና መላው የዐማራ ህዝብን ባለፉት ዐመታት ያሳለፍናቸው ፍዳና መከራ ያነሰን ይመስል በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጪ ያሉ የንፁኻን ዜጎችን በደል፣ ስደት መፈናቀል፣ የጅምላ ፍጅትና መንግስታዊ ሽብርን በመፈጸም ላይ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ቢሆንም ምንም ዓይነት የመገናኛ ብዙኻን ሽፋን እንዳያገኝ እያደረገ ያለበት ሁኔታ እብሪቱንና ማናለብኝነቱን ያስመሰከረበት ሁኔታን ታዝበናል።
ይባስ ብሎም ከሚያዚያ/ 2015 ዓ.ም ጀምሮ እየወሰደ ባለው በስመ 'ህግ ማስከበር' ስም ሀገሪቱ ያላትን ውሱን የሰለጠነ የሠው ሃይሏን፣ ቁሳዊ ሀብቷንና ተቋማዊ መዋቅሮችን በሙሉ በነቁ እና ህዝብን እያነቃቁ ባሉ አካላት ላይና ሀገራዊ ስሜታቸው ጠንከር ያሉትን አፍኖ በመሰወር፣ ኢ ሰብኣዊ ድርጊት በመፈፀም ትክክለኛውን የህዝብን ጥያቄዎችን ለማፈንና ዝም ለማስባል እየሰራ እንደሆነ በግልጽ ታይቷል።
ነገር ግን ትግሉን ከማፈን እና ከመሰወር ይልቅ ይፋዊ፤ ከማዳከም ይልቅ ያጠናከረን፤ የበተነን ሲመስለው ደግሞ በተሻለ አስተሳሰብ እያሰባሰበን እንደሆነ ወራት ያስቆጠረው ትግል ደረጃውን በማሻሻል ህዝባዊ ከማድረጉም በላይ በንፁሓንና ሀገር ወዳድ ብሔር ብሔረሰቦችም ዘንድ ለምን እንዲሉ በማድረጉ የማዕከላዊ መንግስቱን ቀጣይነት ጥያቄ ውስጥ አስገብቶታል።
ከዚህም ጋር በተያያዘ 'መንግስት ነኝ' ባዩ የወንበዴዎች ስብስብ "ካፈርኩ አይመልሰኝ" በሚል የወራዶች ሀሳብ የሀይል ጥቃቱን በማጠናከር በንጹሓን ዜጎች፣ በእምነት ተቋማትና ምንም ዓይነት ዐለማ እና ተሳትፎ በሌላቸው የገዳማት ገዳሚያን ላይ እየፈጸመ ያለው እኩይና ዘግናኝ ተግባርን ከክልሉ ነዋሪዎችም ባሻገር በ'መንግስት' ይደግፉኛል በሚላቸው ስብስቦቹም ጭምር እየተወገዘ መሆኑን ታዝበናል።በታላቁ ገዳም ደብረ ኤልያስ እና አንዋረ መስጊድ ላይ ያደረሰው ጥቃት ማሳያ ነው ።
ስለሆነም፦
፩ኛ/ ውድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና እንቁ የተቋሙ ወታደራዊ መኮንኖች እኔ ኢትዮጵያዊ ስሜቱ ያላችሁ ሓላፊዎች አሁን ላይ ሀገራችን የገጠማት ሁለንተናዊ ችግር መነሻው ፖለቲካዊ መሆኑን ታውቃላችሁ፤
የእናንተ ተቀዳሚው ተግባራችሁም ሀገርን ከውጪ ወራሪ መከላከልና የመላው ኢትዮጵያውያንን ሠላምና ደህንነትን ከማረጋገጥ በመለስ በወረዳና በጎጥ ደረጃ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ግብግብ ስትገጥሙ ላስተዋለ የትልቁን ሀገራዊ ተቋምነት ትዝብት ውስጥ ጥሎታል፤ አልፎ ተርፎም ታላቁን የሀገር መከላከያ ተቋሙን ተራ የፓርቲና የግለሰብ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ አስመስሏችሗል። እናም እየተሰራባችሁ ያለውን ፖለቲካዊ ሸፍጥና ሴራን በውል በመረዳት ወደ ታላቁ እና ሀገራዊ ተልኳችሁ ዘንድ በማተኮር የጀመራችሁትን የመንደር ሚሊሻና የቀበሌ ፖሊስ ተግባራችሁን ለሚመለከታቸው ባለድርሻዎች በመተው ከታሪካዊ ስህተታችሁ እንድትታቀቡ፤ በተጨማሪም ህዝብ ላይ ከመተኮስ ይልቅ ባለውለታ ህዝብን ከችግርና ወረራ በመታደግ ተግባራችሁ ላይ በማተኮር ከፍታችሁን እንድታስጠብቁ።
፪ኛ/ በየአካባቢያችሁ የምትገኙ የፀጥታ መዋቅር አባላት በፖለቲካዊ ፍላጎት የተበላሸውን ዘመቻ በመቀልበስና በመጠቆም፤ በመምራት፤ በተኩስ በመግጠም በጋራ የምንከፍለውን አላስፈላጊ ውድሙቱን በማቆም ታሪካዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እያሳወቅን ከዚህ እኩይና ፀረ ግብ ከሆነው ድርጊታችሁ እማትቆጠቡ ከሆነ ግን ለሚደርስባችሁ ማንኛውም ዓይነት ማህበራዊም ይሁን ሠዋዊ ኪሳራ ሓላፊነቱን እንደምትወስዱት ልናሳስባችሁ እንወዳለን።
፫/ ወቅቱ አመቸን፤ ጊዜ ዘመመባቸው ብላችሁ ከፍ ሲልም እነሱ እስካሉ ድረስ የ'እኛ ህልውና' አደጋ ላይ እንወድቃለን በሚል ሰንካላ ፍርሃት የ'ፋኖ' አባላትን፣ አስተባባሪዎችን፣ ባለ ሀብቶችን እና ማህበረሰብ አንቂዎችን በስመ "ህግ ማስከበር" ስም እያደረሳችሁብን ያለውን ማሳደድ በአፋጣኝ አቁሙ፤ አስቁሙም!
በስህተት መረጃ እና በበሬ ወለደ ታላቁን የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን በማሳት፤ ባልተገባ መልኩ ስምሪት ከመስጠት እንድትቆጠቡ ጥሪያችንን እያስተላለፍን፤ ከዚህ በሗላ ግን በሚደርስብን ማናቸውም ዓይነት ጥቃትና በደል እዳውን እንደምታወራርዱት ልናረጋግጥላችሁ።
፬ኛ/ ውድ የዐማራ ክልል ማህበረሰብና መላው ኢትዮጵያን አሁን ላይ እየደረሰብን ላለው መሳደድን፣ መገደልን፣ መታሰርን እና ታፍኖ መሰወርን እንደ ህዝብ መጥፋት የታወጀብንን በማውገዝ ለገጠሙን ችግሮች በጋራ በመጋፈጥ እና ለአለም ማህበርሰብ በማሳወቅ ከጎናችን እንድትሰለፉ ጥሪያችንን እናቀረባለን ።
፭ ኛ ታላቁ እስክንድር የመሰረተውን የአማራ ህዝባዊ ግንባር የምንቀበል እና በጋራ የምንታገል መሆኑን እየገለፅን ታላቁ መሪያችን ላይ የታቀደውን ሴራ በጋራ እንታገለዋለን ይህንንም የግብረሶደም መንግስት እናሰወግዳለን።
፮ ኛ አረበኛ ዘመነ ካሴ እንኳን ከማይገባህ ወህኒ ቤት በሰላም ወጣህ እያልን ወደፊት አንተን ይዘን የአማራን እና የኢትዮጲያን ጠላቶች እናሸንፋቸዋለን ።
በመጨረሻም
መላው የአማራ ወጣት ሁልህም በመክሊትህ ተነስ ታገል በሰፈረህ ባለው የፋኖ አደረጃጀት ተቀላቀል ይህ ካልሆነ በባረነት እንኳን የምትኖረባት ሃገር አትኖረህም ።

ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለኢትዮጲያ
ድል ለፋኖ
አንድነት ሃይል ነው !!!
ሠኔ/ 01/2015 ዓ . ም.
1.4K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 20:01:15




ጥያቄ ከትግራይ
ሸኔ እየፈነጨ ነው
ሩሲያ ከባድ ው*ጊያ
1.4K views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 18:51:23

1.4K views15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 17:45:01

1.4K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 16:59:47

1.4K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 16:11:13




ለህዝበ ሙስሊሙ ጥሪ
ኤርትራ ዘጋች
ትራምፕ ሌላ ክስ
1.4K views13:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 17:33:22

113 views14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ