Get Mystery Box with random crypto!

የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር #Ethiopia | የእንግሊዝኛ ቋን | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የእንግሊዝኛ ቋንቋን
ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር

#Ethiopia | የእንግሊዝኛ ቋንቋን ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ ለመማር የሚያስችል መማሪያ  የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የኢትዮ-ቴሌ ኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ በተገኙበት ይፋ ሆኗል

መማሪያው በትምህርት ሚኒስቴር የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ሲሆን ከተማሪዎችና መምህራን በተጨማሪ ሁሉም የማህበረሰብ አካል ሊጠቀምበት እንደሚችል ተጠቁሟል

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መተግበሪያው በትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት የበለጠ በማጠናከር በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ የተማሪዎችን የመረዳት አቅም ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል

ፕሮፌሰሩ ከዚሁ ጋር አያይዘው እንደገለጹት የሀገራችን የትምህርት ስርአት ከሰባተኛ ክፍል ጀምሮ የመማሪያና ማስተማሪያ ቋንቋ በአብዛኛው እንግሊዝኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመረዳት የሚገጥማቸውን ችግር ለማቃለል እየተሰራ ነው ብለዋል

ከተለያዩ ሀገራት በጎ ፈቃደኛ  የእንግሊዘኛ መምህራንን  እና የዲያስፖራ አባላትን  ወደ ሀገር ቤት በማስመጣት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ለማሰማራት ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የጠቀሱት ፕሮፌሰር ብርሃኑ መተግበሪያው ይፋ መሆኑ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል

የስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ በበኩላቸው ትውልድን የመገንባት ሃላፊነት የጋራ በመሆኑ መማሪያው ያለምንም የበይነ መረብ ክፍያ አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረጋችን ማህበራዊ ሃላፊነታችንን የምንወጣበት አንዱ ማሳያ ነው  ብለዋል
ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም ቀሪው የማህበረሰብ ክፍል የእንግሊዝኛ ቋንቋን ለመማርና ለማሻሻል እንዲጠቀምበት ጥሪ መቅረቡን ከሚኒስቴሩ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
@wektawi_Merej