Get Mystery Box with random crypto!

ፖለቲከኛ ጀዋር መሐመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው አስተያየት እንደሚከተለው በአማርኛ በፋስት መረ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

ፖለቲከኛ ጀዋር መሐመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው አስተያየት እንደሚከተለው በአማርኛ በፋስት መረጃ ይቀርባል።
#FastMereja
እውነት ለመናገር ባለፉት አራት አመታት የተገደሉት የኦሮሞ ልጆች ቁጥር በወያኔ እና በደርግ ዘመን ሁለቱ ተደምረው የአሁኑ ይበልጣል። ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀያቸው ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። ኦሮሚያን ለማልማት የተማሩ ወጣቶች ታጥቀው እርስ በርስ እየተገዳደሉ ነው። ይህ ለመናገር የሚሳፍር ነው።

ዛሬም እንደትናንቱ እንጮሃለን፣ የዚህ ጦርነት መነሻ የፖለቲካ ግጭት ነው። በውይይት እንጂ በመድፍ አይፈታም። በሰሜን እንዳየነው ይህ ጦርነት የቱንም ያህል ቢቆይ በድርድር ይጠናቀቃል። ለማይቀር ነገር ደሆችን አትጨርሱ።

በሰሜን ያለውን የኢትዮጵያን ችግር በሰላማዊ መንገድ እንፈታዋለን በኦሮሚያ ያለው በጦር እናስወግደዋለን ማለት ራስን ማታለል ነው። የቤቱን አንድ ጎን በማቃጠል ከሌላው ጎን መስራት የማይሆን ነገር ነው።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን  መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም 
@wektawi_Merej