Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን መንግሥት የውጭ ረድዔት ድርጅቶች በኢትዮጵያ አዋሳኝ ከሚገኘው ሐምዳይት የኢትዮጵያዊያን ስደ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

የሱዳን መንግሥት የውጭ ረድዔት ድርጅቶች በኢትዮጵያ አዋሳኝ ከሚገኘው ሐምዳይት የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መቀበያ ጣቢያ እንዲወጡ ማዘዙን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል። መንግሥት ትዕዛዙን ያስተላለፈው፣ በድንበር አቅራቢያ "በኢትዮጵያ መንግሥትና በሕወሃት ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ መባባሱን" ተከትሎ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል። ሱዳን ተጨማሪ ጦር ወደ ድንበር ማስጠጋቷንም ዘገባው ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። በሐምዳይት የስደተኞች መቀበያ ጣቢያ ከሚሰሩት ዓለማቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች መካከል፣ ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድንና የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን ይገኙበታል።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01