Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን በሰላምና፣ በጤና ወደ ቅድስት ሀገርዎ ኢትዮጵያ ተመለሱ ! #Ethiopia | የቅዱስነትዎ | 🗣 ወቅታዊ_መረጃ 🇪🇹

እንኳን በሰላምና፣ በጤና ወደ ቅድስት ሀገርዎ ኢትዮጵያ ተመለሱ !

#Ethiopia | የቅዱስነትዎ ቡራኬ አይለየን

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ሕክምናቸውን አጠናቅቀው ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በብፁዓን አባቶች ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።

ቅዱስነታቸው ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሀገረ አሜሪካ በማቅናት ሕክምናቸውን ሲከታተሉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 1:00 ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ ካህናትና ምዕመናን እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአሁኑ ወቅት የቅዱስነታቸው መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም መድረሳቸውን ተከትሎ የአቀባበል መርሐግብሩ በደማቅ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው ።

ሼር በማድረግ ትክክለኛዉን መረጃ ለሌሎች ተደራሽ ያድርጉ። ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም
https://t.me/Merja01