Get Mystery Box with random crypto!

ሀገር ሰላም ብዬ የተቀመጥኩበት ታክሲ ውስጥ ጎኔ ያለችው ልጅ በሹክሹክታ ድምጽ ምን አለችኝ አባቱ | ወግ ብቻ

ሀገር ሰላም ብዬ የተቀመጥኩበት ታክሲ ውስጥ ጎኔ ያለችው ልጅ በሹክሹክታ ድምጽ ምን አለችኝ አባቱ ትወርድልኛለህ? ደሞ የአይኖቿ መስለምለምስ ትውልዱ አይን አውጥቷል ስትሉኝ አለማመኔ my dirty mind

ባለፈው አዳነች አቤቤ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በሀይል ለመናድ ከአንድ ክልል ብቻ የሚደረግ ከፍተኛ ፍልሰት አለ ስትል ዲቻ ምንም እንዳልመሰለው ሳስብ ብቻዬን ሳቄ ያመልጠኛል ጦሶ

ትናንት ምሳ የበላሁበት ስጋ ቤት ቆራጩ" የበሬን ምስጋና ወሰደው ፈረሱ" እያለ እየዘፈነ ነፍ ስጋ የሰጠኝ በደህና ነው ትላላችሁ አሁን በጠዋት ችክክም ችክክም ችከክም በል በል እያለኝ እኮ ነው

አርባ አመት ሙሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ለመሆን የታገለው ቀጨላ መርዳሳ የኦነግን የምስረታ በአል አብሮ ያከብራል ማለት ነው

በየ ለቅሶ ቤቱ ግን ከቀብር በኋላ የሚዘጋጅ የምሳ ግብአት ቀይ ምስር እና አልጫ አተር እንዲሆን ያወጁት ቀደምት እናቶች በማ ዘመነ መንግስት እንደነበሩ ዶክተር ሮዳስ ሲያብራራ ሰምቼው አላውቅም ወይስ አምልጦኝ ነው

ከአባታቸው ባገኙት አስር ሚሊየን ብር እና አምስት ተሽርካሪ ደሞ የሆነ የሆነ ሱቅ ተነስተው የሀብት ማማ ላይ የተቀመጡ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላቸው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ብለው ንግግር የሚጀምሩ  ቱጃሮች በወንጀል እንዲከሰሱልን ስል በትህትና አመለክታለሁ

በቀደም እለት ዶፍ ዝናብ እየዘነበ ጣራችንን እንደ አታሞ ሲደልቅ ከዛ የዝናብ ኳኳታ ጋር በሚታገል ጮክ ባለ ድምጽ እናቴ
"እስቲ አንድ ልጅ ወልደህ አምጣልኝ" ብላ ያሳቀቺኝ ሳቅ አመቱን ሙሉ ከሳቅኩት ይበልጣል እኔ እኮ እድሜዬን መቁጠር የረሳች መስሎኛል ለካ እስከዛሬ እየቆጠረች ነው Shame on you Mom እኔ ላንቺ ጊዜ ምን ብዬሽ አውቃለሁ

ያቺ በጣም ቆንጆ ሂጃቢ ያስሚን ወንድ አትጨብጥም 2 አመት እኮ አንድ መስሪያ ቤት አብረን ሰርተናል ሁሌም ስንገናኝ በርቀት እንደታቦት ብቻ ጎንበስ ቀና ብዬ ተሳልሜ ነበር ሰላም የምላት ምናል አንድ ቀን ከሀር የሚለዝብ የሚመስለኝ ለስላሷ እጇን ብታስነካኝ መዳፌ ላይ ያረፈ ጠረኗን ከሷ ተደብቄ አንድ ቀን ባሸተው ምነበረ

በቀደም መንገድ ላይ እየሄድኩ በሀሳብ ጭልጥ ከማለቴ የተነሳ የማስበው ጠፍቶኝ ወደራሴ ስመለስ 801, 802, 803, 804 እያልኩ አገኘሁት ራሴን ምን ለምን እየቆጠርኩ እንደነበረ ግን ስካሁን ትዝ አላለኝም። እየጨለልኩ ነው እንዴ

ከላይ ያልኩት ሁሉ አይረባም አውቃለሁ
አንዳንዴ እንዲ ነኝ
ወፈፍ ያደርገኛል እዘባርቃለሁ

By Binyam behaylu

@wegoch
@wegoch
@paappii