Get Mystery Box with random crypto!

ኩርፊያህን ለምን እንደምናፍቀው ይገባህ ይሁን…… የምልህ አለአይደል ስትነጫነጭ ጊዜ …… ወይ ስትቆ | ወግ ብቻ

ኩርፊያህን ለምን እንደምናፍቀው ይገባህ ይሁን…… የምልህ አለአይደል ስትነጫነጭ ጊዜ …… ወይ ስትቆጣ ንዴትህን ግልፅ ስታደርግልኝ…… ትኩረቴን ፈልገህ ልክ እንደህፃን ሲያደርግህ በሆነው ባልሆነው ስታኮርፍ ኩርፊያህ ታስፈልጊኛለሽ የሚል መልዕክት ያለው ይመስለኛል እንክብካቤ ፈልገህ ትኩረቴን ሽተህ ይመስለኛል …… ሰዎች ፊት የነበረህን ኩራት አሽቀንጥረህ እኔ ዘንድ ብሶትህን ስትነፋረቅ…… ከጉያዬ ሽሽግ ስትል ፀጉርህን በጣቶቼ ዳበሳ ስበታትናቸው ጭንቀትህም አብሮ ቢበተን ……ትኩስ እንባህን በፈገግታዬ ባብስልህ…… እኚህን ሁሉ ሁነቶች እወዳቸዋለሁና ኩራትህን አሽቀንጥረህ መሸሸግን ፈልገህ ናልኝ…… በዚህች በጠበበችህ አለም ሳይታክትህ ትሸጎጥበት ዘንዳ እቅፌ ላንተ ሰፊ ነውና መሰልቸትን እኔ ጋር አታስበው…… የነፍስህ ጭንቀት ሲራገፍ የስስት አይኖችህ በፈገግታ ሲያበሩ እኔነቴን አንተው ውስጥ አየዋለሁ እናም አለም ሁሉ ብትጠብህ እቅፌ ላንተ ሰፊ ነው

@wegoch
@wegoch
@paappii

By Fereha nuraddis