Get Mystery Box with random crypto!

ትዝታ ዘ Elementary (፰) _____ ወ/ሮ መስከረም ወደ ክፍል ገባች! ... 'አርት' አስ | ወግ ብቻ

ትዝታ ዘ Elementary (፰)
_____

ወ/ሮ መስከረም ወደ ክፍል ገባች! ... 'አርት' አስተማሪያችን (እድሜዋ በአንቺና አንቱ መሐል ሆኖ ተቸገርን!!) ... አጭር ወፈር ያሉ ሴትዮ ናቸው! ... አጭር ሰው ነገረኛ ነው ይባላል! እሳቸውም የተለዩ አይደሉም! ... በየሳምንቱ አዳዲስ የግርፋት አይነት ያስተዋውቃሉ። ... ግርፊያው በደረጃ የተደለደለ ነው፣ አርት ደብተር ረስቶ/ትቶ የመጣ፣ የተሰጠ የቤት ስራ ያልሰራ፣ እያስተማረች የሳቀ/ች፣ እያስተማረች ያወራ እያለ በቅደም ተከተል ይወርዳል! ...

ዛሬ እኔና ዮሐንስ አርት ደብተር ይዘን አልመጣንም! ... ከግርፋት እንዴት እንደምናመልጥ ከሰልፍ ላይ ጀምሮ እያውጠነጠንን፣ እየተከራከርን ነው የቆየነው! ... በስተመጨረሻ ተስማማን- "አሞናል ብለን እንውጣ" !! ...

⨳⨳

«አርት ደብተራችሁን አውጡ !!»
ክፍሉ ተንኮሻኮሸ ... ተማሪው ደብተሩን እያወጣ ጠረጴዛው ላይ ይዘረጋል! ...
እኔና ዮሐንስ ትወናችንን ልንጀምር ነው! ...
«ያላመጣችሁ ኑ ውጡ!»
ትወናችን ተጀምሯል ...
ዮሐንስ ጠረጴዛው ላይ ተኛ! ... እኔ ከዳሁት! ... ወ/ሮ መስከረም በሁለቱ መደዳ መሐል ሆነው ነው የሚያረጋግጡት ከፊት ወደኋላ ከመሄዳቸው በፊት ጎን ለጎን ያሉትን ቼክ ያደርጋሉ! ... ሀሳቡ ብልጭ ያለለኝ ድንገት ነው (ዮሐንስ ይቅር በለኝ!!) ... ወ/ሮ መስከረም ከኛ ፊት የሚቀመጡትን ዴስክ ቼክ አድርጋ ከጎን ወዳሉት ስትዞር ቼክ ተደርገው ከታለፉት ተማሪዎች ደብተር ተቀበልኩና ፊቴ ዘረጋሁት ! ...

⨳⨳

አሁን እኛ ጋር ደርሳለች!
«ተነስ አንተ ውሪ!» ዮሐንስን ነው!
ዝም ጭጭ! ወይ ፍንክች!
«ምናባቱ ሆኖ ነው?!» ጥያቄው ለኔ ነው ...
«አሞት ነው!»
«አሁን ነው ከቅድም ጀምሮ?»
«ከቅድም ጀምሮ!»
መምህሯ ዮሐንስን መነቅነቅ ጀመሩ ...
«ተነስ! ደብተርህን አሳይና ተኛ!»
አዪዪ! ... አይሁንልህ የተባለ ልጅ!
ዮሐንስ ሆዬ ወይ ፍንክች! ...
«ተነስ ነግሬሃለሁ! ... ተኝተህ ሞተሃል!»
ዮሐንስ ተነሳ ... ፊቱን አጨፍግጎ ዓይኑን እያሸ ነው ...
«ደብተርህን አውጣ!»
አሁንም ዓይኑን እያሸ ነው ...
«እስከወዲያኛው ሳላጋድምህ ደብተርህን አውጣ!»
የዮሐንስ "እንቅልፍ" ብን ብሎ ጠፋ! ...
«አ....ላ...መ...ጣ...»
ዷዷ! ... ቿቿ! ...ጯጯጯጯ! ...

@wegoch
@wegoch
@paappii

By abdu s aman