Get Mystery Box with random crypto!

ጅሩ… አንድ ሰንጋ 650 ሽህ ብር ተጠርቷል።ሌላው 550 ሽህ ጥሪ ተሰምቷል። በአማራ ክልል ሰሜ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

ጅሩ…

አንድ ሰንጋ 650 ሽህ ብር ተጠርቷል።ሌላው 550 ሽህ ጥሪ ተሰምቷል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሬ ከተማ አስተዳደር በአመት አንድ ጊዜ የሚውለው የሆሳዕና ገበያ ዘንድሮም የተለየ ነገር ታይቶበታል።
ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ሰንጋ 650 ሽህ ብር ተጠርቷል ።የሰንጋው ባለቤት ወጣት ሚጥዬ ታደለ ይባላል።650 ሽህ ብር የተጠራው የጅሩ ሰንጋ ገና አልተሸጠም።

ሌላው በዚሁ ገበያ የሞረትና ጅሩ ወረዳ የማንጉዶ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ አበበ በፍቃዱ ለ1 አመት ያክል እንደ ልጄ ስንከባከበው ነበር ያሉትን ሰንጋ በ550 ሽህ ብር ሲሉ ጠርተዋል ሲል የከተማ አስተዳደሩ ሚዲያ አስነብቧል።የሁለቱም ሽያጭ ገና አልተፈፀመም።

===========================
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed