Get Mystery Box with random crypto!

ህውሃት በዝግ ካደረኩት የ60 ቀናት ስብሰባ መረጃ ያወጡ የነበሩትን ለመለየት ኮሜቴ አቋቁሚያለው ማ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

ህውሃት በዝግ ካደረኩት የ60 ቀናት ስብሰባ መረጃ ያወጡ የነበሩትን ለመለየት ኮሜቴ አቋቁሚያለው ማለቱ ተሰምቷል።

ከዝግ ስብሰባው ላይ መረጃዎችን የሚያጋሩ ጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች ማስፈራሪያ እና ዛቻ እየደረሰባቸው ነው ተብሏል።

ህወሓት በቅርቡ ያካሄደውን 60 ቀን የፈጀ ዝግ ስብሰባን ጨምሮ በሌሎች ስብሰባዎች የተነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ከውስጥ መረጃ ለጋዜጠኞችና ለአክቲቪስቶች ማን ነው አሳልፎ እየሰጠ ያለው የሚለውን ለማወቅ ያለመ ኮሚቴ በማቋቋም ምርመራ ጀምሯል።

በትናንትናው ዕለት አንድ የቀድሞ የድምፂ ወያነ ጋዜጠኛና የተለያዩ ህወሓትን የተመለከቱ ጉዳዮች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በማጋራት የሚታወቅ ጋዜጠኛ በዚሁ መርማሪ ኮማቴ ጥሪ ቀርቦለት በመቀለ ከተማ በመገኘት ከኮሚቴው አባላት ጋር ቆይታ ተሰምቷል።

በቆይታውም በቅርቡ የተካሄደው 60 ቀናት የፈጀውን ስብሰባ ላይ የተነሱ ጉዳዮች የተመለከቱ መረጃዎች እንዴትና ከማን ነበር ስታገኝ የነበረው የሚሉ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት የገለፀ ሲሆን ጥያቄዎቹም ከትብብር ይልቅ በማስፈራራትና ለማወጣጣት በመሞከር የተቃኙ እንደነበሩ ተናግሯል።
===========================
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ       
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed