Get Mystery Box with random crypto!

'ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ' መጋቢት 18 በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ እንደሆነ ተገለ | Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

"ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ"

መጋቢት 18 በመስቀል አደባባይ ሊካሄድ እንደሆነ ተገለፀ።

"ኢፍጣራችን ለአንድነታችን" በሚል ሃሳብ መጋቢት 18ቀን 2016 ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በመስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከሀላል ፕሮሞሽንና ከነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት በጋራ በመሆን ዝግጅቱን አስመልክተው በአዲስ አበባ እስልምና ከፍተኛ ጉዳዮች ቢሮ መግለጫ ሰጥተዋል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፀሃፊ ሸይኽ ሁሴን በሽር እንደገለጹት ዝግጅቱ አንድነትን ማጎልበት ፣አብሮነትን ማስቀጠል፤ ህብረትን በማጉላት ለመሻገር ሚናው የጎላ ነው፡፡

ረመዷን የእዝነት ወር በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለጋስ በመሆን ለተቸገሩ ዜጎች ድጋፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

የዝግጅቱ መስራችና አስተባባሪ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በበኩላቸው በተለያዩ አከባቢዎች ተፈናቅለው በየመጠለያ ካምፕ በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ የሚሰባሰብበትና አብሮነታችንን የምናሳይበት ይሆናል ብለዋል።

የዳበረ በጎ የኢትዮጵያዊያን መልካም እሴትን አጠናክሮ በማስቀጠል ለሀገር ሰላም ፈጣሪን የምንለምንበት መድረክ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡

ሁሉም የአዲስ አበባ ነዋሪ ወደ ዝግጅቱ በመምጣት ከወገኖቻችው ጋር በመቆም በድርቅና በተለያዩ ሰው ሰራሽ ምክኒያቶች ለተቸገሩ ወገኖቻችን የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ አጋርነቱን እንዲያሳይ ኡስታዝ አቡበክር መልዕክታቸውን አስላልፈዋል።
      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
Join
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ መቀበያ
https://t.me/wasumohammed