Get Mystery Box with random crypto!

'የሩሲያ - አፍሪካ አጋርነትና ግንኙነት ጠንካራ ጥልቅ እና ፅኑ በመተማመን እና በበጎ ፈቃደኝነት | AddisWalta - AW

"የሩሲያ - አፍሪካ አጋርነትና ግንኙነት ጠንካራ ጥልቅ እና ፅኑ በመተማመን እና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ መመስረቱ መለያው ነው፡፡" የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን

ሐምሌ 17/2015 (ዋልታ) "የሩሲያ- አፍሪካ አጋርነትና ግንኙነት ጠንካራ ጥልቅ እና ፅኑ በመተማመን እና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ መመስረቱ መለያው ነው፡፡" ሲሉ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገልጸዋል፡፡

በሩሲያዋ ቅዱስ ፒተርስበርግ ከተማ ሐምሌ 20 እና 21 ሁለተኛው የሩሲያ -አፍሪካ የኢኮኖሚና የሰብዓዊ ፎረም ይካሄዳል፡፡ፎረሙን አስመልተው የሩሲያው ፕሬዝንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላኩት ፅሁፍ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን በዋናነት አገሮች እና አህጉራዊ ተቋማት ከሩሲ ጋር ስለሚኖራቸው ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ የሰው ኃይል ልማት በዓለም አቀፍ መድረክ ስለሚኖራቸው ትብብር እና መደጋገፍ ሰፊ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

የሩሲያ እና አፍሪካ ወዳጃዊ ግንኑነትን አስመልክተው ፕሬዝዳነቱ እንደገለጹት "በሩሲያና በአፍሪካ መካከል ያለው የአጋርነትና ግንኙነት ጠንካራ ጥልቅ እና ፅኑ በመተማመን እና በበጎ ፈቃደኝነት ላይ መመስረቱ መለያው ነው " ብለዋል፡፡
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/683408460492153?ref=embed_post