Get Mystery Box with random crypto!

ሀገሬ የሀገር በቀል ዕውቀት በየሞች መንደር--- በሠራዊት ሸሎ ሐምሌ 17/2015(ዋልታ) አ | AddisWalta - AW

ሀገሬ

የሀገር በቀል ዕውቀት በየሞች መንደር---

በሠራዊት ሸሎ

ሐምሌ 17/2015(ዋልታ) አገር በቀል ዕውቀት ለማህበረሰብ ዕድገትና ለውጥ እንዲሁም ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ምጥቀት መነሻ ወይም መሠረት መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ለአንድ አገር ዕድገት ባህላዊ ወይም አገር በቀል ዕውቀት ያለው ሚና ቀዳሚ ሰለመሆኑም ይወሳል።

የአገር በቀል ዕውቀት ማህበረሰቡ የዕለት ተዕለት ኑሮን ለመምራት በሚያደርገው የእንቅስቃሴ ሂደት የሚገኝ ልምድ ወይም ክህሎት ሲሆን ሰዎች በኑሮ ዘየአቸው የሚለማመዱትና ወጤት የተመዘገበበት የለውጥ ምንጭ ነው።

የአገር በቀል ዕውቀተ በግብርና ፣በህክምና፣በዕደ ጥበብ፣ በሥነ ህንፃና በሌሎች ሳይንሳዊ ግኝቶች እንደመነሻ ሆኖ እንዳገለገለም ይጠቀሳል።

የአገር በቀል ዕውቀት በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ሲታገዝና ገቢራዊ ሲደረግ ለፈጣን ዕድገትና ለውጥ መንገድ ስለመሆኑም አብዛኛዎቹ የሚስማሙበት ሀቅ ነው።https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/683385503827782?ref=embed_post