Get Mystery Box with random crypto!

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ቀይ ጨረቃ ማህበር በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የአይነት ድጋ | AddisWalta - AW

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ቀይ ጨረቃ ማህበር በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የአይነት ድጋፍ አደረገ

ሐምሌ 17/2015(ዋልታ) የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ቀይ ጨረቃ ማህበር በጎርፍ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ከ100 ሺህ ዶላር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ኢምባሲ ምክትል አምባሳደር ሚስተር ሱዑድ አልቱናይጁና ለአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አይደሩስ ሀሰን አስረክበዋል።

ማህበሩ ድጋፉን ያደረገው በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ ኢምባሲ በኩል ነው።

የተደረገው ድጋፍ ዱቄት፣ ሩዝ፣ የህፃናት አልሚ ምግብ እና ዘይት ሲሆን፤ ይህ በገንዘብ ሲተመን ከ100 ሺህ ዶላር በላይ እንደሚሆን መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።