Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከእስራኤል ግብረ-ሰናይ ድርጀት ጋር የመግባቢያ ስምምነ | AddisWalta - AW

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከእስራኤል ግብረ-ሰናይ ድርጀት ጋር የመግባቢያ ስምምነት አደሱ

ሐምሌ 17/2015 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሴቭ ዘ ችልድረንስ ኸርት (save the children’s heart) ከተባለ የእስራኤል ግብረ-ሰናይ ድርጀት ጋር የመግባቢያ ስምምነት አድሰዋል፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በፈረንጆቹ 2014 የተፈረመ ሲሆን ለ28 ዓመታት የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ በልብ ህመም የሚሰቃዩ ህፃናትን ለመታደግ የሚውል የህክምና ድጋፍ እንዲሁም ለባለሙያዎች ልምድ ለማካፈል የሚያስችል እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ህፃናት ወደ እስራኤል ሀገር በመጓዝ ዎልፍሰን ሜዲካል ሴንተር በተሰኘ ማዕከል ውስጥ የልብ ህክምና የሚያገኙበትን ሂደት ለማመቻቸት የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

እስካሁንም 1000 የሚሆኑ ህፃናት በዚሁ ማዕከል ውስጥ የልብ ህክምና ማግኘታቸው በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

ዩኒቨርስቲው ለሚያደርገው የህፃናት የልብ ህክምና ሆስፒታሉ ያሉበትን ችግሮች ለማሻሻል እና ለመፍታት እንደሚያግዝም ነው የተገለፀው፡፡

በመቅደስ የኔሁን