Get Mystery Box with random crypto!

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል-የሀረሪ ትም | AddisWalta - AW

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል ዝግጅት ተደርጓል-የሀረሪ ትምህርት ቢሮ

ሐምሌ 17/2015 (ዋልታ) በክልሉ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቋል፡፡

የክልሉ የትምህርት ቢሮው ኃላፊ ሙክታር ሳሊህ ባለፈው ዓመት በክልሉ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 10 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚያስገባቸውን ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቅሰው በዘንድሮው አመትም ከባለፈው አመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትኩረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

የቢሮ ኃላፊው ተማሪዎች ሰፊ ሰዓታቸውን ለትምህርታቸው እንዲሰጡ በማድረግ የማብቃትና የመደገፍ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።

በተለይም ከመደበኛ የትምህርት ጊዜ ባሻገር በተቃራኒ ፈረቃ እና በእረፍት ቀናት የማጠናከሪያ ትምህርት ሲሰጥ መቆየቱን ጠቁመው ሞዲል ፈተናዎችን በመስጠትና የቤተመፅሐፍት ጊዜን በማሳደግ እንዲሁም ሌሎች ድጋፎች ሲደረገ መቆየቱን ተናግረዋል።

ከዚህ ባሻገር ከወላጆች ጋር ውይይት የማድረግና ተማሪዎችን በስነምግባር የማዘጋጀት ስራ ሌላው ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ የቆየ ተግባር መሆኑን አብራርተዋል።

በክልሉ በሚገኙ 14 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 2510 ተማሪዎች የዘንድሮውን የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደሚወስዱ ነው ኃላፊው የተናገሩት።
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/683259340507065?ref=embed_post