Get Mystery Box with random crypto!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ ሐምሌ 17/2015(ዋልታ) የ | AddisWalta - AW

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

ሐምሌ 17/2015(ዋልታ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 16ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ በአሶሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የጽህፈት ቤታቸውን የ2015 በጀት የስራ አፈጻጸም ዝርዝር ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ።

የክልሉ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በበጀት ዓመቱ ያከናወኗቸው ስራዎች ሪፖርት በምክር ቤቱ ለውይይት የሚቀርቡ አጀንዳዎች ናቸው።

የክልሉ የ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ የመደበኛ እና ካፒታል በጀት ረቂቅ አዋጅም በምክር ቤቱ ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎም ይጠበቃል።

በተጨማሪም የክልሉ የአስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና በርዕሰ መስተዳድሩ የሚቀርቡ የዳኞች እና ሌሎች ሹመቶችን ምክር ቤቱ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ለጉባኤው ከተዘጋጀው መርሐ-ግብር ማወቅ ተችሏል። መረጃ የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ነው።