Get Mystery Box with random crypto!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 25 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ ድጋፎችን ለትግራይ ክል | AddisWalta - AW

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 25 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የተለያዩ ድጋፎችን ለትግራይ ክልል አስረከበ

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጥሬ ገንዘብን ጨምሮ 25 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ምርጥ ዘርና የምግብ እህል ድጋፎችን ለትግራይ ክልል አስረከበ።

ድጋፉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ፀጋዬ ማሞና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ኃላፊ ማስረሻ በላቸው አስረክበዋል።

ድጋፉ 10 ሚሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብና 15 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው 2 ሺሕ ኩንታል ምርጥ ዘር፣ ዱቄትና ቦቆሎ መሆኑን የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ፀጋዬ ማሞ ገልጸዋል።

የክልሉ ሕዝብና መንግስት ለትግራይ ክልል ያደረገው ድጋፍ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አለመሆኑን ገልጸው በቀጣይ ክልሉን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች የተረከቡትን ድጋፍ በፍጥነትና በፍትሃዊነት ለተጠቃሚው እንደሚያደርሱ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ እያሱ አብረሃ (ዶ/ር) ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የተደረገው ድጋፍም የክልሉ ህዝብና መንግስት የትግራይ ህዝብ አለኝታ መሆኑን ያሳየበት እንደሆነ ገልጸዋል።