Get Mystery Box with random crypto!

ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ ሰኔ 5/2015 | AddisWalta - AW

ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የቀድሞ የአየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ግርማ ዋቄን በመተካት የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ነው የተገለጸው፡፡

ሌተናል ጄነራል ይልማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ አመራር ቦርድ አባል ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

ግርማ ዋቄ ከፈረንጆቹ 2022 ጀምሮ የአየር መንገዱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል፡፡