Get Mystery Box with random crypto!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሶማሊያ እና ከኬንያ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተወያዩ ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚ | AddisWalta - AW

ጠ/ሚ ዐቢይ ከሶማሊያ እና ከኬንያ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተወያዩ

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ እና ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር  ገጻቸው ዛሬ ጠዋት ከኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ እና ከኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር ተገናኝቻለሁ ብለዋል።

ብዙ የጋራ ጥቅሞቻችንን እና ሥጋቶቻችንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋራ ተግዳሮቶቻችንን በድል ለመወጣት ኢትዮጵያ ከእያንዳንዱ ሀገር ጋር ተቀራርባ ትሠራለች ሲሉም አመልክተዋል።