Get Mystery Box with random crypto!

የቀድሞው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ህይወታቸው አለፈ ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) የቀድሞው የጣሊያን | AddisWalta - AW

የቀድሞው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ህይወታቸው አለፈ

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) የቀድሞው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ በ86 ዓመታቸው ህይወታቸው አለፈ፡፡

ሲልቪዮ በርሉስኮኒ ጣሊያንን ከፈረንጆቹ 1994 እስከ 2011 በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለዋል፡፡

የጣሊያን ትልቁን የሚዲያ ኩባንያ የፈጠሩ ቢሊየነር ነጋዴ የነበሩት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ከኢንፌክሽን ጋር በተያያዘ በሚላን በሚገኝ ራፋኢል ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቢቆዩም ዛሬ ህልፈታቸው ተሰምቷል፡፡