Get Mystery Box with random crypto!

በዱር እንስሳትና ውጤቶቻቸው ላይ የሚካሄድ ህገ ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ | AddisWalta - AW

በዱር እንስሳትና ውጤቶቻቸው ላይ የሚካሄድ ህገ ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀመረ

ሰኔ 5/2015 (ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካ አገራት የሚሳተፉበት በዱር እንስሳት እና የዱር እንስሳት ውጤቶቻቸው ላይ የሚካሄድ የወንጀል እና ህገ ወጥ ንግድን መከላከል ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና በአዲስ አበባ ተጀመረ።

በዓለም አቀፍ የዱር እንስሳት ደህንነት ፈንድ እና በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን አዘጋጅነት የሚካሄደውን ስልጠና በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራ የዱር እንስሳት ወንጀል ድንበር ዘለል እንደሆነና ከአጎራባች አገራት ጋር መተባበር እና መቀናጀት ወሳኝነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በዚህም ከዓለም አቀፉ የዱር እንስሳት ደህንነት ፈንድ ጋር በመተባበር ከሰባት አገራት ለተውጣጡ ባለሙያዎች እና ኃላፊዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02XFBy14EtkgidUMmwrtCXuhiK6j8LVCoVH6F97ZxcBeKMF7rKcwF997ib4nKMTUSRl